2015-04-29 16:29:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በርእደ መሬት እጅግ ለተጎዳው ለነፓል ሕዝብ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. እኩለ ቀን ጸሎተ ንግሥተ ሰማይ ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ነውጡ እስከ ህንድ ቻይና ባንግላድሽ ድረስ የተሰማው በነፓል በተከሰተው ርእደ መሬት ለተጎዳው ሕዝብ ጸልየው ለቶጎዳው ቤቱንና ንብረቱን ላጣው ሁሉ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ቅርበት ማረጋገጣቸው የሚታወስ ሲሆን፣ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ቅርበት ካሪታስ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበር ነፓል በሚገኘው ቅርንጫፉ አማካኝነት የተለያዩ አገሮች የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች አማካኝነት እየተመሰከረ መሆኑ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጋብሬላ ቸራሶ ገለጡ።

ቅዱስነታቸው በጳጳሳዊ ኮር ኡኑም - ውሁድ ልብ ምክር ቤት አማካኝነት ለተጎዳው ሕዝብ መርጃ የሚውል 100 ሺሕ ዶላር መለገሣቸው ቸራዞ ገልጠው፣ በነፓል ያለው ወቅታዊው ሁኔታ አሳሳቢ ከመሆኑም ባሻገር የሞት አደጋ ያጋጠመው ሕዝብ ብዛት እስከ 5 ሺሕ ሊደርስ እንደሚችል ሲነገር፣ በጠቅላላ የተከስተው ርእደ መሬት ከ ስድስት እስከ ስምንት ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ መንካቱና አንድ ሚሊዮን አለ መጠለያ ማስቀረቱንም ከነፓል የሚሰራጩት ዜናዎች መሠረት በማድረግ አስታውቀዋል።

ለማልታ ፈረሰኞች ማኅበር ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ኢንጎ ራድትከ በነፓል የማኅበሩ የአስቸኳይ እርዳታ ጉዳይ አባላት በማሰማራት ለአገሪቱ ሕዝብ በተለያየ መስክ ድጋፍ እያቀረበ መሆኑ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ የነፓል አየር ማረፊያ አቅሙ ጠባብ ከመሆኑ የተነሳ እርዳታ አሳፍረው የሚጓዙት ፕሌኖች በደልሂ አየር ማረፊያ እንዲቆዩ ተገዷል፣ ወደዚያ ርእደ መሬቱ እምብርት በሆነው ክልል ለመግባት አጅግ አስቸጋሪ ከመሆኑም የተነሳ በዚያ ክልል ተገኝቶ የደረሰው ጉዳት በተመለከተ ግምገማ ለመስጠት ያዳግታል ቢሆንም ወደዚያ ክልል የሰብአዊ እርዳታ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

ድንበር የለሽ የሓኪሞች ማኅበር አባል በዚህ ማኅበር አማካኝነት ወደ ነፓል የሚላከው የሰብአዊ እርዳታ አስተባባሪ ስተፋኖ ዛኒኒ በበኩላቸውም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በነፓል የሚገኙት ሕክምና ቤቶች የጤና ጥበቃ ጣብያዎች ችምር እጅግ በተጎዳ ሕዝብ የተጨናነቁ በመሆናቸው አሳሳቢ የወረርሽኝ በሽታዎች መዛመት ከወዲሁ ለመግታት በሚል እቅድ ድንበር የለሽ የሓኪሞች ማኅበር እገዛው እያፋጠነ መሆኑ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.