2015-04-29 16:24:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፦ አለ መንፈስ ቅዱስ እውነትን ለመረዳት አይቻለንም


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንደ ተለመደው ዘነግህ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት የሚያሳርጉት መስዋዕተ ቅዳሴ  እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. በመቀጠል ቤተ ክርስቲያን ወደ ፊት ለመራመድዋ ዕለት በዕለት ህያው ለመሆንዋ መንፈስ ቅዱስን ታመሰግናለች፣ በሚል ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ ስብከት መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አስታወቁ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በላቲን ሥርዓት ከግብረ ሐዋርያት ምዕ. 11 ከቁጥር 19 እስከ 26 የተወሰደውን የዕለቱ ምንባብ ጠቅሰው ክርስቲያናዊ ሕይወት የቤተ መዘክር ክርስትና ሆኖ እንዳይቀር ሐዋርያዊ ብርታት ያስፈልጋል። የጌታን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት በአንጽዮኪያ ስብከተ ወንጌል በመጀመር ለይሁድ ብቻ ሳይሆን ለግሪካውያን ለአረማውያን ጭምር አበሰሩ። ቅዱስነታቸው ከዚህ ጥልቅ ሃሳብ በመንደርደር ለመንፈስ ቅዱስ ገዛ እራስ ክፍት ማድረግ መንፈስ ቅዱስ ለሚያመጣው ኅዳሴ ክፍት ሆኖ መገኘት ያለው አስፍላጊነት በማሳሰብ ደቀ መዛሙርት ወንጌል ያበስሩበት በነበረው ዘመን ብዙዎች ወንጌል ለአይሁዳውያን ለአረማውያን ጭምር በመሰበኩ ምክንያት ቅር ተሰኝተዋል፣ ባርናባስ አንጽዮኪያ በደረሰ ጊዜ አረአማውያን ተለውጠው ወንጌልን ተቀበልው ባየ ጊዜ ደስ ተሰኘ፣ ይክ የእግዚአብሔር ሥራ ነው።

ለእግዚአብሔር አስደናቂነት አንፍራ፣ ሳናስበውና ሳናልመው እግዚአብሔር የሚገልጠው ሁነት የሚያስከትለው የመደነቅ ስሜት ሊያስፈራን አይግባም፣ በነቢይ ኢሳያስ ምዕ. 60 ተመልክቶ እንደሚገኘውም እግዚአብሔር የሁሉም ሕዝቦች አዳኝ ጌታ ነው። ብዙዎች ይኸንን ለመገንዘብ ያዳግታቸው ነበር፣ ስለዚህ ለእግዚአብሔር አስደናቂነት እንፍራ፣ እግዚአብሔር ገና ያስደንቀናል፣ እግዚአብሔር የኅዳሴ እግዚአብሔር መሆኑ አላስተዋሉም ነበር፣ እርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ሁሉ ያድሳል ሲል ተናግረዋል። ለዚህም ነው ሰው ሆኖ በመካከላችን የተገኘው፣ እኛን ለማደስ። በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የተመለከትን እንድሆን መንፈስ ቅዱስ ለሚያነቃቃው ኅዳሴ የታየው ፍርሃት እናስተውላለን፣ እግዚአብሔር አምላካችን የድንቅ ሥራ አምላክ ነው እንዳሉ ጂሶቲ ገለጡ።

አንዳንድ ኅዳሴዎች ተረጋግጠው፣ ከእግዚአብሔር የሆነ ኅዳሴ ግቡን ይመታል፣ አንዳንድ ኅዳሴዎች ተጀምረው ሳይረጋገጥ ቀርተዋል፣ ምክንያቱ ከእግዚአብሔር አይደሉምና፣ ሁሉም ለማወቅ እንችል ይሆናል የድህነት ታሪክ የሚያውቁ መላ ቲዮሎጊያን የሚያውቁ ልንሆን እንችላለን፣ አለ መንፈስ ቅዱስ እውነትን ለማወቅ የሚቻል አይደለም፣ መንፈስ ቅዱስ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድምጽ ለይተን እንድናወቅ ያበቃናል። ኢየሱስ በጐቼ ድምጼን ይሰማሉ እኔም ለይቼ አቃቸዋለሁ፣ እነርሱም ይከተሉኛል ሲል እንደተናገረውም ነው።

ቤተ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ኅዳሴ አማካኝነት ወደ ፊት እያለች ነው

የቤተ ክርስቲያን ወደ ፊት መራመድ የዚያ የጌታን ድምጽ ለይተን እናውቅ ዘንድ የሚያበቃን የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው። የማዳምጠው ድምጽ የጌት ከጌታ መሆኑና አለ መሆኑ ለመለየት የሚያበቃ መሣሪያም ጸሎት ነው እንዳሉ የገለጡት ጂሶቲ አክለው፦ አለ ጸሎት ለመንፈስ ቅዱስ ቦታ ለመስጠት አይቻልም፣ በማስተዋል የሚበጀውን ለመከተልና ለመኖር ይቻለን ዘንድ መንፈስ ቅዱስን እንጸልይ፣ ባርናባስና ጴጥሮስን እንመለክት፣ አማኞች በአንጽዮኪያ ክርስቲያን ተባሉ ይኽ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው። ሌላው የተቀበለውን ምሥጢረ ጥምቀት የምክደው እኔ ማን ነኝ?

ክርስትያናዊ ሕይወት በቤተ መዘክር የሚኖር ዝክረ ታሪክ አይሁን

መንፈስ ቅዱስ ከእኛ የሚጠይቀውን የሚፈልገውን ሆነን የምንኖር ስንሆን በእኛ ውስጥ የክርስትናው ሕይወት ህያው ይሆናል፣ ስደት መከራ ቢያጋጥምም በጸሎትና በትህትና በመኖር ኅያው ክርስትና ለመኖር የተጠራን ነን ያሉት ቅዱስ አባታችን ጌታ ሥጋዮን ብሉ ደሜንም ጠጡ ብሎናል፣ የዕለቱን ቅዳሴ ጌታ ሆይ አንተ በቅዱስ ቁርባንህ አማካኝነት በመካከላችን አለህ በእኔ ልብ አለህ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አድለን አድለኝ ወደ ፊት እንድል መንፈስ ቅዱስ ለኅዳሴ ሲጠራኝ ፍርሃት የሌለኝ ሆኜ እገኝ ዘንድ አብቃኝ በሚል መንፈስ እንኑር በሚል ጸሎት ያስደመጡት ስብከት ማጠቃለላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ ገለጡ።    








All the contents on this site are copyrighted ©.