2015-04-29 16:45:00

ሱዳን፦ አል ባሺር ለአራተኛ ጊዜ ለርእሰ ብሔር ኃላፊነት ተሾሙ


እ.ኤ.አ. ከ 1997 ዓ.ም. የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በሱዳን በሚታየው ዓመጽ የሰብአዊ መብትና ክብር ረገጣ ከአሸባሪያን ቡድኖች ጋር ትብብር አላቸው በሚል ክስ ምክንያት የኤኮኖሚ ማዕቅብ የደንገገችባቸው በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት በሰው ዘር ላይ ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ምክንያት ክስ የተመሰረተባቸው

የሱዳን ርእሰ ብሔር ኦማር አል ባሺር እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 13 እና 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በተካሄደው ሕዝባዊ ምርጫ ባሸናፊነት ለአራተኛ ጊዜ የአገሪቱ ርእሰ ብሔር እንዲሆኑ መሾማቸው የተሰጠው ዜና በዓለም አቀፍ ማኅበርሰብ ዘንድ የውይይት ርእስ መሆኑ ሲታወቅ፣ እ.ኤ.አ. ከ 2011 ዓ.ም. የደቡብ ሱዳን ነጻነት ወዲህ በአል ባሺር የምትመራው ሰሜን ሱዳን በተፈጥሮ ሃብት ከታደለው ክልል ውስጥ እርሱም 75% በነዳጅ ማዕድን የታደለውን በማጣትዋ ምክንያት አቢይ የኤኮኖሚ ግሽበት የተጋረጠባት አገር ከመሆንዋም ባሻገር 30% የአገሪቱ ሕዝብ በሥራ አጥነት ችግር የተጠቃ መሆኑ ይነገራል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.