2015-04-27 16:39:00

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን፦ ጦርነት ሰላም ለማረጋገጥ ለሰላም የውይይት መድረክ ጥሪ ነው


እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. በላቲን ሥርዓት የወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ  ዓመታዊ በዓል ምክንያት በኢጣሊያ ቨነዚያ ርእሰ አድባራት ቅዱስ ማርቆስ ባዚሊካ ያረውገው መሥዋዕተ ቅዳሴ የመሩት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ባሰሙት ስብከት፦ “በዓለም የሚታዩት ግጭቶች ውጥረቶች እጅግ የሚያሳስብ ነው። የመጨረሻው የዓለም ጦርነት በሕዝቦች ሰላምና መግባባት እንዲጸና ለማድረግ ሁሉም በጋራ ስለ ሰላምና ስለ መግባባት እንዲተጋና እንዲተባበር አነቃቅቷል፣ ስለዚህ በአሁኑ ወቅት የሚታዩት ጦርነቶች ሰላም ለማረጋገጥ እንዲቻል ወደ የሰላም የውይይት መድረክ የሚገፋፉ ናቸው” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይላኒ አስታወቁ።

ዛሬም እንደ ትላትና፣ አድልዎና አመጽ

በእምነት በጎሳ በምትከተለው ርእዮተ ዓለም ምክንያት ለስደት ለአድልዎ የመዳረጉ ተግባር ዛሬም እንደ ትላትና በዓለማችን የሚታይ አሳዛኝ ጸረ ሰባአዊ ተባር ነው። ስለዚህ ይኽ ታሪክ የነበረ ብቻ ሳይሆን ዛሬም በተለያዩ የዓለማችን ክልሎች የሚፈጸም እንዳውም እጅግ በተራቀቀ መንገድ የሚፈጸም መሆኑ ብፁዕነታቸው ከዚህ ዕለት ጋር ተያይዞ በኢጣሊያ የሚከበረው 70ኛው የነጻነት ቀን ዓመት ተዘክሮውንም በማስታወስ ያ ሁለተኛው የዓለም ጥርነት ያበቃለት ዕለት በኢጣሊያ እ.ኤ.አ. ከ 1943 እስከ 1945 በርእዮተ ዓለም በመከፋፈል የታየው አሰቃቂው ግጭት የሚያስታውስ ብቻ ሳይሆን ሰላም ያለው የላቀው ክብር የተረጋገጠበት ወንድማማችነት መቀራረብና መደጋገፍ ማእከል ያደረገ ኅብረተሰብ እንዲጸና ማድረጉንም እንዳሰመሩበት አኩይላኒ ገለጡ።

ያለፉት 70 የነጻነት ዓመታት ለኢጣሊያ የእድገት ዓመታት ምልክት ነው

በኢጣሊያ 70ኛውን ዓመት እያስቆጠረ ያለው የነጻነት በዓል የኢጣሊያ የእድገትና የልማት ታሪክ የመቀራረብ የመተባበር ታሪክ የሚያወሳ አቢይ ቀን ነው፣ 70 የሰላም አመት ሲከበር በተልያዩ የዓለማችን ክልሎች ዛሬም በሃይማኖት በምትከተለው ርእዮተ ዓለም በጎሳ በተለያየ ጸረ ሰባአዊ ድርጊት አማካኝነት ለሞት የመዳረጉ ተግባር ይታያል፣ ሁኔታውም እጅግ አሳሳቢም ነው፣ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ሁሉም ለሰላም በመተባበር እንዲነቃ ገፋፍተዋል፣ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት የሚይታዩት ግጭቶችም ወደ የሰላም መድረክ የሚገፋፉ መሆናቸው ያብራሩት ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን አክለው፦ በእምነት በሃይማኖት በጎሳ በሚከተሉት ርእዮተ ዓለም ምክንያት ለስደትና ለመፈናቀል አደጋ ለሚጋለጡት ቅርበትና ድጋፍ ማቅረብ ብቻ ሳይሆን ይከንን ሁኔታ ለመተባበርና ለመቀራረብ የሚደገፍ አጋጣሚ መሆን አለበት ብለው፣ የሚሰደደውና ከለላ ለማግኘት የሚፈናቀለው ለአገርና ለባህል ስጋታ ነው ከሚል ጸረ ሰባአዊ አስተሳሰብ እንቆጠብ አደራ፣ ባንጻሩ ፍትህና ነጻነት ማነቃቃት ያስፈልጋል እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ አስታወቁ።

ብፁዕነታቸው ወንጌላዊው ማርቆስን ጠቅሰው፣ ቅዱስ ማርቆስ ሞትን አሸንፎ የተነሳውን የክርስቶስ ህላዌው በማቅረብ የተነሣው ክርስቶስ ከፍርሃት ነገ ምን ይሆን ከሚለው መጻኢን በስጋት ከመጠባበቁ ሁነተ ነጻ እንዳወጣንና ጨለምተኛነትን ጸረ እምነት የሆነውን አስተሳሰብ ሁሉ ጥንት የነበረ አሁንም ያለ ነው። በሞት ላይ ድል የነሣው ክርስቶስ ከዚህ ሁሉ ነጻ እውጥቶናል፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በታማኝነት መከተልን ከቅዱስ ማርቆስ እንማር፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በመምስል ሰብአዊነትንና ምኅረትን እንዝራ፣ እንዲህ በማድረግም የጌታን ቃለ እውነትን እናበስራለን፣ የእምነት ጸጋ ለሰጠን ጌታ እናመስግን፣ እምነት አቅበን በእኛና በአካባቢያችን እንዲያብብ ለማድረግ በሁሉም ልብ ፍሬ እንዲሰጥ በቃልና በሕይወት ለሚሰጠው ምስክርነት ያበረታን እንዳሉ አኵይላኒ ገለጡ።

የቨነዚያ ሥነ ጥበብ ባህልና ቅርስ

ብፁዕነታቸው በቅርቡ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮና በኢጣሊያ ርእሰ ብሔር ማታረላ መካከል የተካሄደው ክልአዊ ግኑኝነት አስታውሰው፣ የክርስትናው ባህል በኢጣሊያ የሰጠው አቢይ አስተዋጽኦ በኢጣሊያ ያኖረው ሥነ ጥበባዊ ባህል የሥነ ጥንት ቅርስ ሃብት ወደር የማይገኝለት ኢጣሊያ በዓለም ለጎብኝ መስኅብ ባህል ቀዳሜ ሥፍራ እንድትይዝ ያደረጋት እውነት ያበከረ ግኑኝነት እንደነበር ገልጠው፣ ሁሉም ለጋራ ጥቅም እንዲተጋ የመተባበር የመደጋገፍ ብርታት እንዲኖር መንግስት የሁሉም ጥቅም በማረጋገጥ ሂደት እንዲተጋና ዜጎች ስለ የሁሉም ጥቅም መረጋገጥ በሚደረገው ጥረት አስተዋጽኦ በመስጠት የሁሉም ጥቅም መረጋገጥ ኃሴት እንዲሰማቸው አደራ በማለት ያስደመጡት ስብከት እንዳጠቃለሉ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.