2015-04-27 16:31:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ቅብአ ምኅረት እሩቅ ወደ ሚገኙት ማድረስ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሮማ የኢጣሊያ የካቶሊክ ተግባር ማኅበራት ሊቀ መናብርትና የመስተዳዳር አባላት ተጨባጩ ሁነት አግርሞት ለአይነተኛው አርአያ በሚል ርእስ ሥር እያካሄደው ወዳለው ዓውደ ጉባኤ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ፊርማ የተኖረበት መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ይኽ የካቶሊክ ተግባር ማኅበር ወንጌላዊ ልኡክነት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በደረሱት በወንጌላዊ ኃሴት ሐዋርያዊ መልእክት አማካኝነት ዳግም ለማነቃቃት ዓልሞ ለወጠነው ዓውደ ጉባኤ ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት፣ የሕዝብ ሕይወት በሚያፈቅር የሕይወት ባህል ላይ የጸና ለሕዝብ ቅርብ በሆነ ወንጌላዊ ሕይወት አማካኝነት ሐዋርያዊ ልኡክነት በማደስ ማኅበረሰብ እንዲታደስና የሁሉም ጥቅም ባቀና ዓላማ ማኅበርሰብ እንዲተጋ ለማድረግ የካቶሊካዊ ተግባር ማኅበር ተልእኮ የሚሰጠው አስተዋጽኦ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ያመለክታል፣ ስለዚህ ይኽ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. የተጀመረው ከመላ ኢጣሊያ የተወጣጡ በጠቅላላ 700 ተጋባእያን እያሳተፈ ያለው ዓውደ ጉባኤ፣ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. የኢጣሊያ 70ኛው ዓመት ያከበረው የነጻነት በዓል ዙሪያ የካቶሊክ ተግባር ማኅበራት አባላት የክርስትናውን እሴት መሠረት በማድረግ ለአገርና ለሕዝብ ጥቅውም የከፈሉት ወንጌላዊ መሥዋዕትነት በማስታወስ ለአገር ለሕዝብ ለጋራ ጥቅም ለሕዝብና ለአገር ነጻነት ሕይወታቸውን የሰዉት የመሰከሩት ወንጌላዊ እሴት ዘወትር ሕያው እንዲሆንና ይኽ ማኅበር በማኅብራዊ ሕይወት አማካኝነት በሚሰጠው አስተዋጽኦ እንዲመሰክረውም የተጠራ መሆኑ ተጋባእያኑ እንዳሰመሩበት ከኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.