2015-04-27 16:26:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኔፓል በርእደ መሬት አደጋ ሳቢያ ሕይወታቸው ላጡት ጸሎት አሳረጉ


እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. በነፓል በተከስተው ከባድ ርእደ መሬት ሳቢያ ለሞት የተዳረገው ቁጥር ብዛት ከፍ እያለ መምጣቱ ሲገለጥ፣ እስካሁ ድረስ የሟቹ ቁጥር ብዛት 3 ሺሕ 350 መድረሱ ከክልሉ የሚሰራጩ ዜናዎች ሲያመልክቱ፣ ከዚህ ጋር በማያያዝም ይኽ ርእደ ሜሬት በኔፓል ጎረቤት አገሮች ጭምር መሰማቱና በሕንድ ለ 66 ሰዎች በቻይና ለ 17 ሰዎች ሞት ምክንያት መሆኑ ያስታውቃሉ።

ለተጎዳው ሕዝብ የሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በተለያዩ የእርዳታ መዋቅሮቹ አማካኝነት በሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እየተረባረበ መሆኑ ሲታወቅ፣ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እኩለ ቀን በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ከተሰበሰበው በብዙ ሺሕ ከሚገመተው ምእመናን ጋር ሆነው ጸሎት ንግሥተ ሰማይ ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ፣ በተከሰተው ርእደ መሬተ ሳቢያ ሕይወታቸው ላጡት ስለ ተጎዱት ቤትና ንብረታቸው ስላጡት ወድሞቻችንና እህቶቻችን ጸልየው፣ ለአገሪቱ ሕዝብ ቅርበታቸውና የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ትብብር እንዳረጋገጡ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ባርቢ ገለጡ።

ይኽ በተከታታይ የተሰማው ርእደ መረት ከኔፓል አልፎ በህንድ ቻይና ፓኪስታንና ባንግላድሽ ሳይቀር መሰማቱ ሲገለጥ በዓለም አቀፍ የትምህርት የሥነ ምርምርና የባህል ድርጅት የሰው ዘር ቅርስ ብሎ በገለጣት ከተማ አቢይ ጉዳት ማስከተሉና ሕንጻዎች ቤቶችና የአየር ማሪፊያዎች በጠቅላላ የመገናኛ አውታሮችና መንገዶች ጭምር በማውደም በሰውን በንብረት ላይ ያስከተለው ጉዳይ እጅግ ከፍ ያለ መሆኑ በካሪታስ ለሚጠራው የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበር በኔፓል ለሚገኘው ቅርንጫፍ ተጠሪ ኣባ ፒዩስ ፐሩማና በስልክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ ወደ ተጎዳው ክልል ደርሶ የሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ አዳጋች መሆኑ ጠቅሰው፣ የተፈናቀለው ቤቱና ንብረቱ ያጣው ሕዝብ ብዛት እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ገልጠው፣ ለተጎዳው ሕዝብ የመጀመሪያ እርዳታ ለማቅረብ የአቢያተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበራት የተለያዩ አገሮችና የዓለም አቀፍ የተራድኦ ማኅበራት እርዳታ በማቅረቡ ረገድ እየተጣደፉ ናቸው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.