2015-04-20 16:17:00

የንግሥተ ሰላም ጸሎት ጉባኤ አስተንትኖ፦ በሰው ልጅ ላይ የሚከሰተው አሰቃቂ አደጋ ያብቃለት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. እኩለ ቀን በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ከተገኘው በብዙ ሺሕ ከሚገመተው ምእመናን ጋር ሆነው ጸሎት ንግሥተ ሰማይ መርተው ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ የዕለቱ ምንባብ አስደግፈው ባስደመጡት ስብከት እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. በሜዲትራኒያን ባህር በመጓዝ ወደ ኢጣሊያና በኢጣሊያ ወደ ኤውሮጳ ለመግባት ከሊቢያ የተነሱት ስደተኞች ያሳፈረች ትንሽ ባለ ሞተር ጀልባ በመገልበጧ

ምክንያት ከሰባት ሞት እስከ ዘጠኝ መቶ የሚገመቱት ስደተኞች የሞት አደጋ እንዳጋጠማቸው የተሰማው ዜና ልብን በሃዘን የሚነካ መሆኑና የተሻለ ሕይወት ሲፈልጉ ሞት ያጋጠማቸው ናቸው በማለት ሲገልጡዋቸው የተሰማው ድምጻቸው ጥልቅ ሐዘን የሚያስተግባ እንደነበር የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አያይዘው፣ የዚህ ዓይነቱ አሰቃቂው አደጋ ዳግም እንዳይከሰት የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አለ ምንም ግብዝነትና ማመንታት ሰብአዊነት የተካናነው ምላሽ እንዲሰጥበትና የዚህ ዓይነቱ አሰቃቂው የሞት አደጋ ፊት ማንም በግዴለሽነት እንዳይመላለስ የአደራ ጥሪ አስተላልፈው፣ የሞት አደጋ ባጋጠማቸው ዜጎች ምክንያት የተሰማቸው ጥልቅ ሐዘን ገልጠው፣ ለሟች ቤተሰቦች ጸሎታቸው በማረጋገጥ፣ የዚህ ዓይነት አሰቃቂው የሞት አደጋ እንዳያጋጥም የዓለም አቀፍ ማኅበረ ሰብ ቀልጣፋና ውጤታማ የድጋፍና የትብብር ተግባር ያከናውን ዘንድ አደራ ብለው፣ የሞት አደጋ ያጋጠማቸው እንደኛ ሰዎች ናቸው ወድሞቻችንንና እህቶቻችን ናቸው፣ ከእርሃብ ከእንግልት ለማምለጥ በሃይማኖትና በፖለቲካ በጦርነት ችግር ምክንያት ተገደው የበለጠ ሕይወት ተስፋ በማድረግ የሚጓዙ ናቸው፣ ሁሉም ፍትህና ሰላም የተካነው ሕይወት ሊኖር ይገባዋል። ሁላችን ስለ እነዚህ ወንድሞቻችን አብረን ጸጋ የሞላሽ ማርያም ሆይ ጸሎት እንድገም እንዳሉ ገልጠዋል።

ሁሉም ክርስቲያኖች የክርስቶስ ምስክሮች ሊሆኑ ይገባቸዋል፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያጋጠመው የሞት አደጋ ምክንያት መልክት ከማስተላለፋቸው ቀደም በማድረግ ከሞት የተነሣውን ክርስቶስ ያዩና ከእርሱ ጋር የተገናኙ ደቀ መዛሙርት ሊመሰክሩ ግድ ነው፣ ከክርስቶስ ጋር መገናኘት መስክር መስክር የሚል ነው። በመሆኑም ሁሉም ማኅበረ ክርስቲያን ለምስክርነት የተጠራ ነው። ኑና እዩ ለማለት የተፈጸመውን ለማስታወስና ለመመስከር የተጠራን ነን እንዳሉ ጂሶቲ ገለጡ።

መስካሪ ያየውን በእምነት አይን ያየውን እንጂ በግዴለሽነት የተመለከተው አይደለም የሚመሰክረው፣ ያየውን ተጨባጭ ታሪኪዊ ሂደቱና ያጋጠመውና የሆነውን በዝርዝር የሚያወሳ ያየውን ያጋጠመውን ሕይወቱን ያልነካው የማይመለከተው እንደሆነ የሚገልጥ ታሪክ ነጋሪ ማለት አይደለም፣ ያጋጠመው ያየው ሕይወቱን የነካውን የለወጠውን ተመክሮ ያደረገውን እምነት የሚመሰክር ማለት ነው። ታማኝ ለመሆን ደስተኛና መኃሪ ምስክርነት ማቅረብ ያስፈልጋል፦ የክርስትና ምስክርነት ይዞታ የርእዮተ ዓለም ቀመር ወይንም አድርግ አታድርግ የሚል የሕግ ስብስብ ግብረ ገባዊነት ሳይሆን የድህነት መልእክት ነው፣ ተጨባጭ በአንድ ሰው የተኰነ ታሪክ ነው፣ እርሱም ከሞት የተንሣው ክርስቶስ ብቸኛው የሁሉም አዳኝ ማለት ነው፣ ሁሉም ክርስቲያኖች ይኸንን ለመመስከር የተጠሩ ናቸው። ምስክርነቱ አሳማኝ ለመሆን የሚያበቃው በደስታ በመኃሪነት ግልጽ ጥበብ ሰላም የተካነ ሲሆን ነው። ምቾት ብኩንነት ለእኔ ባይነት ስግብግብነት የሚኖር ሲኮን ክርስትናው የማይሰማና አይነ ስውር ይሆናል፣ ከሞት ለተነሣው ክርስቶስ ለብዙ ወንድሞች ጥያቄ የማያይ ዓይነ ስውርና የማያዳምጥ ጆሮ ያለው ይሆናል። እንዲህ ከሆነ እንዴት ህያው ክርስቶስን መመስከር ይችላልን? እንዴት አድርጎ ነጻ አውጪው ክርስቶስ የዋህና ርህሩህ ክርስቶስ ሊያበስር ይችላልን? የሚል ጥይቄ አቅርበው እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምንም’ኳ ፍጹማን ባንሆንም በእምነት ጸጋ አማካኝነት ከሞት የተነሣው ክርስቶስ መስካሪያን እንድንሆን ትደግፈን፣ የፋሲካ ጸጋ የሆነው ሕይወት ሰላምና ደስታ ለምንገናኛቸው ሁሉ እናደርስ ዘንድ ታብቃን።

የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ከፈን የዚያ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጠው የእግዚአብሕር ምሕረት እንድናይ ያበቃናል። በዚህ አጋጣሚም ቅዱስነታቸው እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 21 ቀን 2015 ዓ.ም. በቶሪኖ የሚፍጽሙት ሐውጾተ ኖልዎ አስታውሰው፦ ሁሉም በቅዱስ መግነዝ የተገለጠው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱም ከእግዚአብሔር መሃሪነት ጋር ለመገናኘት እንዲቻልና በወንድሞቻችንና እህቶቻችን ፊት ከሚግለጠውን ኢየሱስ ጋር ለመገናኘት የሚያበቃን እንዲሆን ተመኝተው ለሁሉም ሰላምታን አቅርበው ጸሎት ንግሥተ ሰማይ አሳርገው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.