2015-04-13 15:49:00

የምኅረት ኢዮቤል፦ የቅዱስ አባታችንና የቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ራእይ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያወጁት የምኅረት ኢዮቤልዩ ዓመት እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 11 ቀን 2015 ዓ.ም. በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኋላ አምስት ሰዓት ተኩል በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ እ.ኤ.አ. በ 2000 ዓ.ም. ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ድንጋጌ መሠረት ሚያዝያ 12 ቀን የሚከበረው የመለኮታዊ ምኅረት ዓመታዊ መዓል ምክንያት ባረገው አንደኛ ጸሎት ዘሠርክ የአዋጅ ሰነድ በይፋ መቅረቡና ድንጋጌው መነበቡ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይላኒ አስታወቁ።

መለኮታዊ ምኅረት የፍቅር ሁለተኛ ስም ወይንም መግለጫ መሆኑ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. 1980 ዓ.ም. ኤፈሶን ምዕ. 2 ቍ. 4 “እግዚአብሔር በምኅረት ባለ ጸጋ” መሆኑ የሚያበሥር የእግዚአብእሔር ምኅረት የተሰየመው በደረሱት ዓዋዲ መልእክት ዘንድ በማብራራት ከ 20 ዓመት በኋላ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 30 ቀን 2000 ዓ.ም. ፋውሳታ ኮዋልስካ ቅድስና በማዋጅ የቅድስናዋ መሠረተ ሃሳብ በእግዚአብሔር ምኅረት ላይ የነበራት እምነት መሆኑ በመግለጥ፣ “በስቁል ክርስቶስ ልብ አማካኝነት የእግዚአብሔር መለኮታዊ ምኅረት ለሰዎች ተገለጠ፣ ልጄ ሆይ እኔ ፍቅርና ምኅረት መሆኔ ለሰዎች አብስሪ” ሲል ኢየሱስ የሰጣት የተልእኮ ቃል ጠቅሰው በጽርሃ ጽዮን ለሰው ልጅ የተገለጠው ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ጌታ መሆኑ ተገለጠ በማለት ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ከበዓለ ፋሲካ ቀጥሎ የሚውለው ሁለተኛው እሁድ መለኮታዊ ምኅረት እንድታከብር መደንገጋቸው ጃዳ አኵይላኒ አስታውሰው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መለኮታዊ ምኅረት ኃጢአትን የሚምር ብቻ ሳይሆን የሁሉም ሰዎች ፍላጎት ግምት የሚሰጥ የሰው ልጅ የሚያፈልገው ሁሉ አስቀድሞ የሚያስተውል ፍቅር እግዚአብሔር በኢየሱስ አማካኝነት ገዛ እራሱ ለሰው ልጅ ዝቅ በማድረግ የሰው ልጅ የሚያስፈልገውን መንፈሳዊና ሰብአዊ ነገር ሁሉ የሚለግስ መሆኑ የሚያሳስብ የእግዚአብሔር አሳቢነት የሚያጎላ መሆኑ ባወጁት የመለኮታዊ ምኅረት ዓመት የድንጋጌ ሰንድ ዘንድ አንዳሰመሩበት መነበቡ አስታውቀዋል።

ቅዱስነታቸው እ.ኤ.አ. መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ሥርዓት ንስሓ መርተው ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ምኅረት አብሳሪ በማለት ገልጠው ይኽ የቤተ ክርስቲያን አይነተኛው ተልእኮ በመለወጥ ጎዳና የሚከናወን መሆኑ በማብራራት የምኅረተ እዮቤል አውጀዋል፣ ይኽ ቅዱስ ዓመት ኢየሱስ “በሰማይ እንዳለው አባቴ መኃሪዎች ሁኑ” ሲል በተናገረው ቃል የሚመራ ነው።

ይኽ የምኅረት ኢዮበልዩ ዓመት እ.ኤ.አ. ታህሳስ 8 ቀን 2015 ዓ.ም. በሚከበረው በንጽሕት ድንግል ማርያም በዓል ተጀምሮ እ.ኤ.አ. ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚጠናቀቅ መሆኑ ያስታወሱት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ አክለው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በድንጋጌው፦ “እግዚአብሔር ሁሉን ዘወትር ይምራል መኃሪ ነው፣ ስለዚህ ምኅረቱን ከመለመን አንቦዝን፣ መላ ቤተ ክርስቲያን የእርሱ የምኅረት ጸጋ ያስፈልጋታል፣ ምክንያቱም ሁላችን ኃጢአተኞች ነንና። በዚህ ቅዱስ የኢዮበል ዓመት የምኅረቱ ኃሴት እናገኝ ዘንድ፣ ምኅረቱ ፍርያማ በማድረግ ሁሉን ለማጽናናት ተጠርተናል” እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.