2015-04-08 16:19:00

የእርዳታ ተግባር፦ እርሃብ ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት ኢጣሊያ ታማኝ ሆና ትገኝ


በቅርቡ በኢትዮጵያ ርእሰ ከተማ አዲስ አበባ ተቀባይነት ያለው የልማት እቀድ ለይቶ የሚገልጥ ብሎም መላ ዓለም መመገብ በሚል ርእስ ዙሪያ የሚመክር ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ ሊካሄድ በተቃረበበት በአኑ ወቅት፣ እንዲሁም በእቅድ ተይዞ ያለው በኒው ዮርክ በተመሳሳይ ርእስ ዙሪያ የሚካሄደው ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ ቀደም ብሎ በተመሳሳይ ርእስ ዙሪያ በኢጣሊያ የእርዳታ ተግባር የተሰየመው የትብብርና የድጋፍ ማኅበር የተለያዩ ዓውደ ጉባኤዎችና የትርኢት መግለጫዎች መርሃ ግብር

እያካሄደ መሆኑ ሲገለጥ፣ ይኽ እ.ኤ.አ. እስከ 2030 ዓ.ም. ባለው የጊዜ ገደብ ውስጥ ከምድረ ገጽ እርሃብ ጨርሶ ለማጥፋት በሚል እቅድ ሥር የኢጣሊያና የኤወሮጳ  ድኅረ እ.ኤ.አ. ከ 2015 እቀድ ምን ተመስሎው የዚህ የእርዳታ ተግባር ማኅበር ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ማርኮ ደ ፖንተ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ የዛሬ 15 ዓመት ቀደም ብሎ ሁለት ሺሕኛው ዓመት በሚል መጠሪያ በዓለም የሚታየው እርሃብ ለመዋጋት የተወጠነው ሚለኒዩም የልማት እቅድ እ.ኤ.አ. 2015 ዓ.ም. 17 እቅዶች በማስቀመጥ የተወጠነው በሚቀጥሉት 15 ዓመታት ግቡም ተጨባጭ ለማድረግ ጥረት የሚደርግበት የልማት እቅድ የሁሉም አገሮች መንግሥታት እንዲሁም በጠቅላላ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት የድጋፍ የትብብር ማኅበራት ተቀዳሚ ኃላፊነት ነው ብለው፣ ለዚህ ርእስ ጉዳይ ተገቢ ትኵረት ሰጥተው እንዲመክሩበትም ይኽ በሳቸው ጠቅላይ ዋና ጸሓፊነት የሚመራው የእርዳታ ማኅበር ጥሪ ማቅረቡ ገልጠው፣ እስከ 2015 ዓ.ም. ባለው የዓመታት ገደብ ውስጥ ይጨበጣል የተባለው የልማት እቀድ ሙሉ በሙሉ የተጨበጠ ነው ብሎ ለመናገር ቢያዳግትም፣ በአሁኑ ወቅት የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር የሆነው ምግብ የማግኘት መብቱ ቅድሚያ ተሰጥቶበት፣ በዚሁ እቅድ ብዙ ጥረት እየተደረገ ነው። የልማት እቀድ ተፈጥሮ የሚያከብር ተቀባይነት ያለው ሁሉም አገሮች በእኩል የሚያሳትፍ የእርሻው መስክ ማሻሻል የእርሻ ኤኮኖሚ፣ ምግብ የማግኘት ሰብአዊ መብት ዋስትና እንዲሁም በአሁኑ ወቅት ከዚህ ቀድም በዓለም የሚታየው እርሃብ በግማሽ ለመቅረፍ በሚል እቅድ የተጀመረው ጥረት በአዲስ እቅድ ከዓለም እርሃብ ጨርሶ ለማስወገድ በሚል እቅድ ቀጣይነቱ  ማረጋገጥ ያፈልጋል ብለዋል።

ኢጣሊያ በዚህ እቅድ ታማኝ ሆና መገኘት ይኖርባታል፣ ኢጣሊያ ብቻ ሳትሆን በጠቅላላ የበለጸጉ አገሮች ሁሉ ታማኝ መሆን ይገባቸዋል። በተጨማሪም ድኾች አገሮች ተብለው የሚገልጡት መንግሥታት የሚከተሉት የልማት እቅድ የውጭ አገር ጫና የሌለበት መሆን እንዳለበት የእርዳታ ተግባር ማኅበር በተለያየ መልኩ ለሁሉ አገሮች ጥሪ እያቀረበ ነው። ርሃብ ማስወገድ በልማት እቀድ ብቻ ሳይሆን በጠቅላላ በህሉም የሕንጸት መስክ ጭምር መደገፍ የሚገባው አቢይና አንገብጋቢ እቅድ ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.