2015-04-06 15:31:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የመስቀል መንገድ ስለ እምነታቸው ለሚገደሉት ክርስቲያን


ኃጢአታች፣ የሚሰደዱት ክርስቲያኖች መራራው ስቃይ ለብቻቸው የተተዉት የሚኖሩት የሕይወት ጫና በግዴለሽነታችን እያየን እንዳላየን የምናልፋቸው መላ ሁነት የጨለመባቸውና ግርማ መጎስ የለሽ ሆነው የሚታዩት በስቁል ኢየሱስ ያሉ ናቸው። በጠቅላላ ለስቃይ የሚዳረጉት በስቁል ኢየሱስ መሆናቸው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 3 ቀን 2015 ዓ.ም. እንደ ተለመደው ዓርብ ስቅለት በሮማ ኮሎሰዮም አደባባይ የሚቀርበው የመስቀል መንገድ ከውጭና ከውስጥ የመጡት በብዙ ሺሕ የሚገመቱት ምእመናን በተገኙበት መርተው በፍጻሜ ባቀረቡት ጸሎት አስታውሰው፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጎልጎታው ጉዞ ትርጉም በጥልቅ የሚገልጥ የደገሙት ጸሎት፣ ይኽም የሰው ልጅ ክፋት የዓለም ጭንቀት ሁሉን ያስታወሰ፣ ማለቂያ የሌለው የእግዚአብሔር ምህረት ልባችንን ይለውጥ ዘንድ የተማጠነ እንደነበር የቫቲካን ረዲዮ ልኡክት ጋዜጠኛ ቲዚያና ካምፒዚኒ ገለጡ።

የእኛ የልብ ጭካኔ ባደረሰበት ስቃይና መከራ መልከ ጥፉ ለመሆን በተገደደው ኢየሱስ ክርስቶስ በሕማማት ጎዳና የሚኖረው ስቃይ የእነዚያ ለብቻቸው የተተዉት ቤተሰቦችና ኅብረተሰብ በግዴለሽነታችን በቸል ባይነታችን የሚወርድባቸው ስቃይና መከራ ያለ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባቀረቡት ጸሎት እንዳሰመሩበት የገለጡት ልእክት ጋዜጠኛ ቲዚያና ካምፒዚኒ አክለው በኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይና መከራ የወቅታዊው ሰው ስቃይ ቀጣይ ሆኖ እንደሚታይ የሚያረጋግጥ ጸሎት መሆኑ አስታውቀዋል።

“መለኰታዊ ፍቅር ባንተ ዘንድ ዛሬም በግዴለሽነትና በዝምታ ተባባሪ በሚያስመስል እያየነ እንዳላየን እየሆን ለስደት ለመከራ በሚዳረጉት አንገታቸው በሚቀሉት በእምነታቸው ምክንያት በሚሰቃዩት ሁሉ አለህ፣ ባንተ ስቃይ የእነዚህ ለስቃይ የሚዳረጉት ዜጎች ስደትና መከራ አለ” ያሉት ቅዱስ አባታችን ለዚህ ሁሉ ስቃይ የሚዳረገው ወቅታዊው ኢየሱስ ልባችንና ሕይወታችን ይለውጥ ዘንድ በእርሱ ስም ጸልየዋል።

“እንድትሰቀል ባደረገህ ኃጢአታችን ለመጸጸት አብቃን፣ በልሳናችን ለምደግመው መለወጥ ቃል ብቻ ሳይሆን ሕይወትና ተግባር ይሆን ዘንድ ደገፈን፣ በዓለም አታላይነትና የማይማረክ ተስፋ በእኛ ውስጥ አነቃቃ ተስፋህን ህያው አድርግ፣ በምግባረ ብልሽትና በዓለማዊነት መስኅብ የማይታለል ፍቅር በእኛ ዘንድ አቅብ።” 

“መስቀል የትንሣኤ ጎዳና፣ አርብ ስቅለት የብርሃነ ፋሲካ ጎዳና፣ እግዚአብሔር ልጆቹን የማይረሳ፣ በዘለዓለማዊ ምህረት ይቅረ ሊለን ሊምረን የማይደክም አባት ነው።”

በመስቀል መንገድ ፍጻሜ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ወደ ተሰቀለው ኢየሱስ ያቀና ጸሎት ሲያቀርቡ፦ “የኢየሱስ ሥጋና ደም አድነን፣ የክርስቶስ ደም እኛነታችን ማርክ፣ ከክርስቶስ ጎድን በሚፈሰው ውኃ አንጻን፣ የኢየሱስ ሕማም አጽናን፣ መልካሙ ኢየሱስ ሆይ ስማን፣ በስቃይህ ውስጥ ደብቀን” የሚለውን ቅዱስ አባታችን የደገሙት ጸሎት ጥልቅ የመስቀል መንገድ ትርጉም የሚገልጥ፣ የነበረ ያለፈ ታሪክ ሳይሆን በዚህ በምንኖርበት ዓለም ለስቃይና ለመከራ ለስደትና ለሞት በሚዳረጉት ዜጎች የሚደገም መሆኑ የመስቀል መንገድ ወቅታዊነት ላይ ያነጣጠር እንደነበር የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ካምፒዚኒ ገልጠው፣ የመስቀል መንገድ የእግዚአብሔር ፍቅር ሚሥጢር ነው። ፍቅሩ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ አሳልፎ እስከ መስጠት የሚያፈቅር ፍጹም ፍቅር ነው። ስቁል ኢየሱስ የምህረት ድኻ የድኾች ወዳጅ የሆነች ቤተ ክርስቲያንና ይጠራል፣ ያጸናል፣ የክርስቶስ በመስቅል ላይ መሞት እግዚአብሔር ብርታት መሆኑ የሚያረጋግጥ እግዚአብሔር ፍጹም መልስ መሆኑ የሚያረጋግጡ ጥልቅ መሠረታውያን ጥያቄዎች የሚያነቃቃ፣ ታሪክ በትንሣኤው እንዳደሰና እንደሠራ ያረጋግጥልና ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.