2015-04-06 18:24:00

ሐዋርያዊ መልዕክት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ


ትናትና እሁድ ሚያዝያ አምስት ቀን 20015 እንደ ጎርጎርዮስ አቁጣጠር  በሥርዓተ አምልኮ ላቲን በዓለም ዙርያ የሚገኙ የካቶሊዊት ቤተ ክርስትያን ተከታዮች  የጌታን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ከፍ ባለ ድምቀት  አክብረው ውለዋል።ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጨምሮ የጁልየን የቀን መቁጠርያ የሚከተሉ የምስራቅ አብያተ ክርስትያናት ፊታችን እሁድ  በተመሳሳይ  የጌታችን መድኀኒታችን ትንሳኤ እንደሚያከብሩ የሚታወስ ነው ።ይሁን እና ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ  ትናትና በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ከትገኙ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ምእመናን በተገኙበት  በብዙ ካርዲናላት ጳጳሳት እና ካህናት ተሸኝተው  መስዋዕተ ቅዳሴ  አስርገዋል።ከሥርዓተ ቅዳሴ  ፋጽሜ በኃላ  በየቅዱስ ጰጥሮስ ማእከላይ  ሰገነት ብቅ ብለው ለሮም ከተማ እና ለመላ ዓለም Urbi et Orbi የትንሳኤ  ሐዋርያዊ መልዕክት   አስተላልፈዋል  ባርከዋልም። ቅድስነታቸው ባስተላለፉት መልዕት  እነሆ ኢየሱስ ክርስቶስ ተነስተዋል ፍቅር ጥላቻን አሸንፈዋል ፡  ሕይወትም በሞት ላይ  ድል ሁነዋል  ብርሃን ጨለማን አባረዋል ፡ ብለው ካሉ በኃላ ጦርነት እና ግችን የሚጭር ትዕቢት መወገድ አለበት የትህትና ብርታት የምሕረት እና የሰላም ባለቤቶች  መሆን  ይጠበቅብናል  ብለዋል ።በተለያዩ የዓለም ክልሎች በመሰቃየት እና እየተሳደዱ የሚገኙ ክርስትያኖች ዘክረው ሞትን አሸንፎ የተነሳው ኢየሱስ ክርስቶስ ስቃያቸው እንዲቀበልላቸው በተለያዩ ግጭቶች ሕይወታቸው እያጡ እና በእንግልት ላይ የሚገኙ ሰዎች ሰላሙ እንዲያውርድላቸው እንለምንነው ብለዋል  ቅድስነታቸው ።በመካከለኛው ምስራቅ በተለይ  በዒራቅ እና ሲርያ  እየተካሄደ ያለውን ግጭት እንዲገታ የሁለቱ ሀገሮች ህዝቦች በሰላም  ለመኖር እንዲችሉ  የሚመለከታቸው እካላት ሁሉ ግጭቱ እንዲገቱ ተማጽነዋል።

በመላ ዓለም  ሰላም መስፈን ሲገባ የዓለም ህዝቦች ሲሰቀዩ በጽንፈኞች ሕይወታቸው ሲያልፍ ሲሰደዱ ሲነገላቱ ማየት እንዴታ ያሳዝናል ብለው ያሉት  ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ  ሰላም እና ፍትህ እንዲኖር አጽንኦት ሰጥተው  አሳስበዋል።በእስራኤል እና ፍልስጤማውያን  መካከል የመወያየት እና የመቻቻል ባህል እንዲዳብር የሰላም ውይይት ሂደት ዳግም እንዲጀመርም ጠርተዋል።ሊብያ ላይ እየተካሄደ ያለውን ትርጉም አልባ ደም መፋሰስ እንዲቆም ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ  ዕርቅ እና ሰላም እንዲወርድ በማሳሰብ የመን ላይ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት እና የህዝብ ስቃይ እና እንግልት እንዲሁ ሰላማዊ መፍትሔ ያገኝ ዘንድ  ቅድስነታቸው ጠይቀዋል።በምዕራባውያን ሀገራት እና  በየኢራን መንግስት በሲትጸርላንድ ሎዛን ላይ  የተካሄደው የኢራን የኑክኩልየር መርሀ ግብር ትኩረት የሰጠ  ድርድር የተደረሰው ስምምነት አሞግሰው አመስግነዋል  ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ። ከዚህ ሌላ በሰሜናዊ ናይጀርያ  በደቡብ ሱዳን በረፓብሊክ ኮንጎ  የሚታዩ ግጭቶች እንዲቋጩ እና ሰላም  እን ዲሆን  የተቻለ ሁሉ  እንዲደረግ  አደራ ብለዋል ።ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ  ለዓለም ያሳተላለፉት  የትንሳኤ ሐዋርያዊ መልዕክት በማያያዝ  ባለፈው ሐሙስ  በምስራቃዊ ኬንያ በጋሪሳ ከተማ ዩኒቨርሲቲ በአል ሸባብ ዓማጺ እና አክራሪ እስላማዊ ቡድን  ጥቃት ሰንዝሮ  150 ተማሪዎች  ለሕልፈት ማዳረጉ እና ከሰማንያ በላይ  በማቁሰሉ የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን  ገልጠው  ምእመናን እና ባለ በጎ ፈቃድ ሰዎች   በግፍ ስለተገደሉ ተማሪዎች እንዲጸልዩ  አሳስበዋል።የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ ብርሃን በዩክሬይን እንዲያጸባርቅ ያል።ኣቸውን ከፍተኛ ምኞት ገልጠዋል።የዩክሬይን  የርስ በርስ ግጭት እንዲቆም እና በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ጥረት ላካሄዱ  የኤውሮጳ ሕብረት ሀገራት መሪዎችም አወድሰዋል።በተለያዩ  የዓለም ክፍሎች በወንጀለኞች  ተጠልፈው የሚገኙ ሁሉ ነፃነታቸው እንድያገኙም ያላቸውን ከፍተኛ ምኞት ገልጠዋል።  በዚሁ በ21ኛ ምእተ ዓመት ሰዎች ጠልፎ  የባርነት ድርጊት መስራት ምን ያህል እንደሚያሳዝን  ያመለከቱ  ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በተለያዩ ሀገራት እስር ቤት ውስጥ በመሰቃየት ላይ የሚገኙ ሁሉ  ለፍትሐዊ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ እና ሰብአዊ መብታቸው እንዲከበር ተማጽነዋል።ሞትን አሸንፎ የተነሳ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሚሰቃዩ  ከሚሳደዱ እና ከሚንገላቱ ጐን  እንደ ሚገኝ  አሳስበው  በቅዱስ ጰጥሮስ  አደባባይ ለተገኙ  ሁሉ መልካም ትንሳኤ ተመኝተው እና  ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው  ተሰናብተዋቸዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.