2015-04-03 16:13:00

የዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ዝክረ 10ኛው ዓመት ልደት በሰማያዊ ቤት


እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 2 ቀን 2015 ዓ.ም. ከ 70 ሺሕ በላይ የሚገመቱ ከውስጥና ከውጭ የመጡ ምእመና በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ በተሰበሰቡበት ዕለት ብፁዕ ካርዲናል ሊዮናርዶ ሳንድሪ ልክ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 9 ሰዓት ከ 37 ደቂቃ፦ “ተወዳጁ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ልክ በዚህች ሰዓት ምድራዊ ሕይወታቸውን አጠናቀው ወደ እግዚአብሔር ቤት ተመለሰዋል፣ ስለ እሳቸው እንጸልይ”  በማለት የዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ዜና ዕረፍት

ማሳወቃቸው የሚዘከር ሲሆን፣ ይኽ የተሰጠው ዜና ረዥም የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ብቻ ሳይሆን ረዥም ኵላዊ ታሪክ ምዕራፍ የዘጋ ዕለት በማለት የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ተንትነውታል። ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የእኚህ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ቅዱስ ብላ ያወጀችላቸው የቤተ ክርስቲያን ልጅ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በሰማያዊ ቤት የተወለዱበት ዝክረ 10ኛው ዓመት በተለያየ መልኩ ማክበሯ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።

እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 2 ቀን 2005 ዓ.ም. የሳቸው በሰማይ ቤት መወለድ የዓለም የነገሮች በጠቅላላ የሰው ሁሉ ሂደት ቆም ፀጥ ያለበት ዕለት፣ የጊዜ ተከትሎአዊ ሂደት ሳይቀር ቆም ዘገም ያለበት ዘለዓለማዊነት የሰው ልጅ ሕይወት ቀርቦ የጎበኘበት ጊዜ በአለ ጊዜ እርሱም በፍጹም ዘለዓለማዊ ጊዜ የተነካበት፣ አላፊው ጊዜ ቆም ብሎ ለዘለዓለማዊነት ቦታ የለቀቀ የሚያስመስል ሁኔት የታየበት መሆኑ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ያንን ዕለት እንደገለጡት የሚታወስ ሲሆን፣ ሁሉም ሕዝብ “ጌታ ሆይ መንፈሴን ባርክ፣ እግዚአብሔር ሆይ ምንኛ ታላቅ ነህ፣ በመጎስና በብርሃን ተከበህ፣ ሰማይን እንደ ድንኳንህ በምድር ላይ የዘረጋህ….” የተሰኘው መዝሙር አዚሟል፣

የር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ዜና ዕረፍት በሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ አለ አባት የቀሩ ጠባቂ እንደሌላቸው ያስመሰለ ሆኖ ቢታዩም፣ መቁጸሪያ በእጃቸው በመያዝ ለእኚህ 27 ዓመት ቤተ ክርስቲያንን በአቢይ እምነት ለመሩት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በመጸለይ ያሳየው ጥልቅ መንፈሳዊነት የሰው ልጅ ሕይወት በሞት የሚደመደም አለ መሆኑ መስክረዋል። በተለይ ደግሞ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ “አትፍሩ … ቦሮቻችሁ ለክርስቶስ ክፈቱለት… እትፍሩ” በማለት ያሰሙት የነበረው ቃል በዚያች ቀንና ሰዓት ተስተጋብቶ በሁሉም ልብና አእምሮ ጸሎት ሆኖ ተደምጠዋል።

ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ከምድራዊው ዓለም ከስቃይ ሁሉ ተሰናብተው ዛሬ በእያንዳንዱ ሰው ልጅ ልብ ውስጥ አትፍሩ…ልባችሁ ለክርስቶስ ክፈቱለት የሚለው ቃላችው እያስደመጡ ናቸው። ባንዴ ወቅት ቅዱስ ዎይትይላ “ክርስቶስ ሆይ…የአንተ የብቸኛውና ልዩ ሥልጣን አገልጋይ አድርገኝ፣ የአንተ ሥልጣን አገልጋይ፣ አገልጋይ አድርገኝ፣ የአገልጋዮች አገልጋይ አድርገኝ” ሲሉ ያሰሙት ጸሎት በዚያች በሰማያዊ ቤት በተወለዱባት ቀን በመላይቱ ቤተ ክርስቲያን እየተደመጠ ነው።

ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ለሁሉ ለእያንዳንዱ የኅብረተሰብ ክፍል ተናግረዋል። የመልክአ ምድር ርቀት የሃይማኖት የባህል የቋንቋ ልዩነት የሚፈጥረው መራራቅ የማይበግረው ቃላቸው በሁሉም አገሮችና ባህሎች ሃይማኖቶች ተስተጋብተዋል። ሲያነቡ ታይተዋል። እንባቸው የተሸናፊነት ምልክት ሳይሆን ሁለ መና ለጌታ የማስረከብ ምልክት ሲሆን፣ ምንም’ኳ ጦርነት ግጭት በምድር ቢፈራረቅም በጌታ ተስፋ የማድረግ የእማኔ ምልክት ነበር።

“በዚህ ገሚሱ የሚባላው አጥቶ በረሃብ ሲቀጭ ሌላው በጦርነት በሥራ እጥነት ምክንያት ለተለያየ አደጋ ሲጋልጥ፣ በዓለም ገና በመሃይምነት የሚሰቃይ ሕዝብ የሚታይ ቢሆንም ቅሉ፣ ሁሉም ሕይወትና የተስተካከለ ተቀባይነት ያለው ልማት በመከላከል በሙሉ ኃይላችን የምንኖርባት ምድር የሕይወትና የመልካምነት ፍሬ አፍሪ ለማድረግ ከመታገል ወደ ኋላ አንበል” የሚለው ፍትህ እኩልነት ነጻነት ሰላም ማእከል ያደረገ መልእክታቸውም በዚያች ቀን ተስተጋብተዋል።

ሁሉንም ለተፈቀረችው ቅድስት እናት ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ለማርያም የነበራቸው ፍቅር አብነት ናቸው። “በቅድስት ተፈቃሪቷ እናት ማርያም አማካኝነት ገዛ ርእሴ እነሆኝ በማለት ለጌታ ያቀረብኩበት ቃል በአንቺ እጅ አድሳለሁ፣ ያለፈው የአሁኑ የመጻኢው ፍሬ በጠቅላላ በአንቺ እጅ አቀርባለሁ፣ በሁሉም የጌታ ፈቃድ ይገለጥ፣ ከአንቺ ጋር ሆኖ ወደ አብ ቤት መራመድ እንዴት ታላቅ ዋስትናና ጽናት ነው፣ አሜን፤ በማለት የደረሱት ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ ማእከል ያደረገ ማርያማዊ መንፈስ የሚያጎላም ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.