2015-04-01 16:16:00

ብፁዕ ኣቡነ አውዛ፦ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ሕፃናት ከውትድርና ዓለም ያድን


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታና የደህንነት ምክር ቤት ላቅመ አዳምና አቅመ ሔዋን ያልደረሱት ዜጎች ለውትድርና ዓለም የመዳረጉ አስከፊው የሕጻናትና የታዳጊ ወጣቶች የሰብአዊ መብትና ክብር ረገጣ ርእስ ዙሪያ ባካሄደው ስብሰባ የተሳተፉት በዚህ ዓለም አቀፍ ድርጅት የቅድስት መንበር ቀዋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ በርናርዲቶ አውዛ፦ ዓለም ይኸንን አሰቃቂው በሕፃናት ላይ የሚፈጸመው የመብትና ክብር ረገጣ በዝምታ ማየቱ እስከ መቼ ድረስ ይሆን? ላቅመ አዳምና ላቅመ ሔዋን ያልደረሱ ዜጎች ከዚህ አስከፊው ተግባር ማዳን የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አማራጭ የሌለው ኃላፊነትና ግዴታ ነው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ አድሪያና ማሶቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።

ሕፃናት በውትድርናው ዓለም መገልገያ መሣሪያ ማድረግ፣ ግጭትና ወጥረት በሚታይባቸው ክልሎች ማሰለፍ በዓለም ክልል እጅግ እየተስፋፋ ከመሆኑም ባሻገር፣ ጉዳዩ እጅግ አስከፊና ጸረ ሰብአዊ ተግባር ሆኖ እያለ በዝምታ ማየቱና ሁኔታው ልሙድ አድርጎ መመልከቱ እጅግ አሳዛኝ ብቻ ሳይሆን፣ ዝም ብሎ ማየቱ ተቀባይነት ያለው እንደሚያስመስለውም አብራርተው፣ ይኸንን ጸረ ሰብአዊ ድርጊት ለመዋጋትና ብሎም ለማጥፋት ፖለቲካዊ ፈቃድና ግብር ገባዊ ጽናት ያለ እንደማይመስልም ገልጠው፣ በሕጻናት ላይ የሚፈጸመው አስከፊው በደል ጨርሶ ለማጥፋት የሁሉም አገሮች መንግሥታትና ዓለም አቀፍ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አቢይ ኃላፊነት አለበት ብለው፣ እ.ኤ.አ. 2014 ዓ.ም. ሕፃናት ለተለያየ አደጋ የተጋለጡበት ለዘርፈ ብዙ ዓመጽ የተዳረጉበት ሰብአዊ መብታቸውና ክብራቸው የተረገጠበት ዓመት እንደነበርም ጠቅሰው ሁኔታው ባለበት ጸንቶ እንዳውም እጅግ እየባሰ መምጣቱን በሶሪያ በኢራቅ ያለው ሁኔታ ያረጋግጠዋል በእነዚህ አገሮች ከ 10 ሺሕ በላይ የሚገመቱ ሕፃናት በመካሄድ ላይ ባሉት ግጭቶች መገልገያ መሣሪያ ሆነው እንደሚገኙ ብፁዕ አቡነ አውዛ ባሰሙት ንግግር ጠቅሰው፣ ሕፃናት የጦር መሣሪያ አንግበው በውጊያና በግጭት ዓለም ማካተቱ የጸረ ሰብአዊ መብትና ክብር ተግባር ብቻ ሳይሆን፣ ዓለም አቀፍ የሰው ልጅ መብትና ክብር ውሳኔ የሚጥስ አቢይ ወንጀል ነው። በመሆኑም መንግሥታት ማኅበራውያን የፖለቲካና የሃይማኖት መሪዎች ሁሉም በጋራ አለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ተግባሩን እንዲያወግዙ ጥሪ ማቅረባቸው የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ማሶቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።

ብፁዕ አቡነ አውዛ ባሰሙት ንግግር የተባበሩት መግሥታት ድርጅት የጸጥታና የደህንነት ምክር ቤት በዓለም ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ ተቀዳሚ ተልእኮው በመሆኑም፣ በተለያዩ የዓለማችን ክልሎች ብሔራዊ ዓለም አቀፋዊ ብሎም የመልክአ ምድር ፖሊቲካ አቀማምጥ ጥቅም አንጻር የሚከሰቱት ግጭቶችና ጦርነቶች በግልጽና አለ ምንም ማመንታት በመቃወም የሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ እንዲስፋፋ ካለ መታከት ይረባረም ዘንድ  አሳስበው፣ ግጭቶችና ጦርነቶች ለማቆም ብሎም በውትድርና ዓለም የተዳረጉት ሕፃናትን ከወደቁበት ኢሰብአዊ ተግባር ለማላቀቅ ይኽ ዓለም አቀፍ ድርጅት ተቀዳሚ ዓላምው እንዲያደርግ አደራ እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ አያይዘው፣ ሕፃናት ወታደር ከወደቁበት አስከፊው አደጋ ለማላቀቅ ሕፃናቱ ለውጊያ የተዳረጉባቸው ግጭቶች መፍሔ ያገኙ ዘንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥረት በማድረግ ሕፃናቱ ከወደቁበት አደጋ በማላቀቅና ከኅብረተሰብ ጋር በሰላም ተቀላልቅለው ለመኖር የሚያበቃቸው ዘርፈ ብዙ ሕንጸት እንዲያገኙ በማድረግና ከዚሁ ጋር በማያያዝም በውትድርና ዓለም ተዳረገው የነበሩት ሰብአዊ ስነ ልቦናዊ ሕንጸት እየተሰጣቸው የሚገኙትም የተሟላ ድጋፍ ያገኙ ዘንድ አደራ ብለው። ሕፃናት ለአጥፍተህ ጥፋ መገልገያ፣ የዓመጽና የግጭት መሣሪያ የማድረግ ጸያፍ ተግባር እንዲወገድ ጉዳይ በዝምታ ማየት ያብቃለት እንዳሉ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.