2015-03-30 16:25:00

የሐዘን መግለጫ መልእክት ስለ ነፍሰ ኄር ፓትሪያርክ ብፁዕነታቸው ማር ዲንክሃ አራተኛ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ፓትሪያርክ ብፁዕነታቸው ማር ዲንክሃ አራተኛ ምክንያት እ.ኤ.አ. መጋቢት 28 ቀን 2015 ዓ.ም. በህንድ የአሲሪ ሥርዓት ለምትከተለው ምሥራቃዊት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ለምስራቃዊት የአሲሪ ሥርዓት ለምትከለው ቤተ ክርስትያን ሥዩም ሜጥሮፖሊታ ፓትሪያርክ ብፁዕነታቸው ማር አፕረም ሙከን የሐዘን መግለጫ መልእክት ማሰላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ የተለግራም መልእክት፦ ነፍሰ ኄር ብፁዕነታቸው ማር ዲንክሃ አራተኛ የስደተኞች ክርስትያን ለስቃይና ለችግር ለተዳረጉት ክርስቲያን ድምጽ በመሆን ያገለገሉ፣ ጽኑና ጥበብ የተካናቸው ታማኝ የቤተ ክርስቲያንና የሕዝበ እግዚአብሔር አገልጋይ በማለት እንደገለጡዋቸው ያስታወቀው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ በመካከለኛው ምስራቅ በተከስተው ግጭት ባለው ሁከት እንዲሁም በኢራቅና በሶሪያ ተከስቶ ባለው ግጭት ሳቢያ ለስደትና ለስቃይ የተዳረገው ማኅበረ ክርስቲያንና የሌሎች የተለያዩ አናሳ ሃይማኖት ተከታዮች ላጋጠማቸው ችግርና ስደት ቅርብ በመሆን ያገለገሉ፣ ግጭቶች ሁሉ በውይይት እንዲፈቱ በማሳሰብ በመጸለይ ስለ ሰላም ያሳዩት ጥረት ዘክረው፣ በቅርቡ በአገረ ቫቲካን ሐዋርያዊ ጉብኝት አካሂደው እንደነነበርም አስታውሰው ለሰጡት አስተዋጽዖና አገልግሎት እግዚአብሔርን ማመስገናቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ገለጠ።








All the contents on this site are copyrighted ©.