2015-03-30 16:07:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.ፍራንቸስኮ፦ ቅድስት ተረዛ ዘኢየሱስ ቆራጥ ወንጌላዊት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቀረመሌሳውያን መነኮሳት ማኅበር መሥራች ቅድስት ተረዛ ዘኢየሱስ የተወለደችበት 500ኛው ምክንያት ለማኅበሩ ጠቅላይ አለቃ ባስተላለፉት መልእክት፦ “ቅድስት ተረዛ ዘኢየሱስ ልዩ የጸሎት መምህር” በማለት እደገለጧት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።

በ 16ኛው ክፍለ ዘመን ቤተ ክርስቲያንን ያገለገለች ይህች የስፐይን ተወላጅ ቅድስት ታላቅ የሰቂለ ኅሊና መምህር፣ ዓለም በነበልባል እሳት ውስጥ ነውና ጥቅም የሌለው አናሳ እርባና ባላቸው ነገሮች ከእግዚአብሔር ጋር በመደራደር ጊዚያችሁን አታጥፉ በማለት ለማኅበሩ ደናግል ባንዴ ወቅት የለገሰቸው ምዕዳን ቅድስት ተረዛ ዘኢየሱስ የተካነቸው ሰብአዊና መንፈሳዊ ታላቅነት የሚያስገነዝብ መሆኑ ቅዱስነታቸው ገልጠው፣ ተረዛ ዘአቪላ የነበረችበት የገዳማውያን ማኅበር ይኖረው የነበረው የቸልተኛነት፣ ጽናት የሌሽ ገዳማዊ ሕይወት፣ በመመልከት ያች በሉተር  በኤውሮጳ ውስጥ በነበረው ጦርነት፣ እንዲሁም የኦታማን ግዛት ወረራ በጥንታዊት ኤውሮጳ  መስፋፋት ምክንያት መከፋፈል ባጋጠማት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጭምር ኅዳሴ እንዲረጋገጥ አቢይ ጥረት ያደረገች መሆንዋ ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት ማስታወሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።

ቅዱስት ተረዛ በነበረችበት ዘመን ይታይ በነበረው የቤተ ክርስቲያና የዓለም ሁኔታ ፊት ታዛቢ ሆና በመገኘት ሳይሆን፣ የነበራት የጤና መጓደል ምክንያት ሳትሰናከል ሰለቸኝ ደከመኝ ሳትል ወንጌል አብሳሪ ለሁሉም የጸሎት መምህር በመሆን የሰጠቸው የቃልና የሕይወት ምስክርነት ያስታወሱት ቅዱስ አባታችን አክለው ቅድስት ተረዛ ጸላይነቷ በጊዜ በቦታ ሳይታጠር ሁለመናዋ ጸሎትና አገልግሎት በማድረግ በሁሉ ሥፍራና ሁኔታ ፈተና ባለበት ሁሉ ግላዊና ማኅበራዊ ችግር ቢያጋጥምም ጽኑዎች ታማኞች ሆኖ መገኘት ያለው የላቀ ክብር በሕይወቷ አሳስባችለች፣ የቀርመሎስ ገዳማውያን ማኅበር በማደስ ዳግም በማነቃቃት እያንዳንዱ ለሌላው ጸጋ መሆኑ በቃልና በሕይወት በማስተማር ዓይናፋርነት ሳይሆን እወተኛ ትሕትና በመኖር የእያንዳንዱ እግዚአብሔር የሰጠውን ችሎታ ዓቢይ ግምት በመስጠት፣ የምቀኝነት የቅናት የሐሜት ምንጭ የሆነውን የአስመሳይነት እንዲሁም የሃሰት አክብሮት ሁሉ በመንፈስ ጽናት አለ ምንም አይናፋርነት በመቃወምና በትህትና በማውገዝ ሁለ-መናዋ ለጌታ ያስረከበች መሆንዋ እንዳሰመሩበት ደ ካሮሊስ ገለጡ።

ይኸው ቅድስት ተረዛ ዘኢየሱስ ሁለ መና ለጌታ መስጠት ለሚለው ውፉይነት አብነት በመሆንዋም ምክንያት የተወለደችበት 500ኛው ዓመት በዚህ የውፉያን ዓመት ማክበር አቢይ ትርጉም ያሰጣዋል፣ 500ኛው ዓመተ ዝክረ ልደትዋ ለውፉያን ዓመት ዓቢይ ጸጋ ነው። ዓለምን በኢየሱስ ክርስቶስ ዓይን በማየት እርሱ የሚፈልገውንና የሚያፈቅረውን ሁሉ እንፈልግና እናፈቅር ዘንድ ለሚያበቃ መንገድ ታነቃቃን በማለት ያስተላለፉት መልእክት እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.