2015-03-27 14:36:00

ቅድስት መንበር፦ ዓለም አቀፍ ሕግና የኡክራይን ሉኣላዊው ድንበር ማክበር


ጀነቭ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብና ክብር በሚከታተለው ማኅበር ቋሚ የቅድስት መንበር ታዛቢ ብፁዕ አቡነ ሲልቫኖ ማሪያ ቶማዚ ማኅበሩ ባካሄደው ክፍለ ጉባኤ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር፦ ለዚያች በጦርነት ለተጠቃቸው ኡክራይንና ለአገሪቱ ሕዝብ በጠቅላላ የቅድስት መንበር ቅርበትና ትብብር በማረጋገጥ ቅድስት መንበር አሁንም ደግማ የዓለም አቀፍ ሕግና የኡክራይን ሉኣላዊው ድንበር ይከበር ዘንድ ጥሪ በማቅርብ፣ በብሔራው ደረጃም ይሁን በክልላዊ ደረጃ የአገሪቱ ሉኣላዊነትና መረጋጋት ተገቢ ዋስትና ለማረጋገጥ የሚያበቃ የዓለም አቀፍ ድንበራዊ ሕግና የሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ መሠረት ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

በውይይትና በገላጋይነት አማካኝነት ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲገኝ ለሚደረገው ጥረት የቶክስ አቁም ስምምነት ማክበር ወሳኝና ቅድመ ሁኔታም መሆኑ ብፁዕ አቡነ ቶማዚ ገልጠው፣ በክልሉ ያለው ውጥረት ለማስወገድ የተባበሩት መንግሥታት፣ የኤውሮጳ የደህንነትና የትብብር ማኅበር  የሚንስክ የስምምነት ውል እግብር ላይ እንዲውል ያካሄዱትና እያካሄዱት ያለው ጥረት እውቅና መስጠት ያለው አስፈላጊነት እንዳሰመሩበት የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

በዚያ ግጭት በሚታይበት ክልል ያለው የሰብአዊ ጉዳይና እንዲሁም የሰብአዊ መብት ጥበቃ እንዲሻሻል የተደረሰው ስምምነት ማክበር መሠረት ነው። በተጨማሪም አመጽ እንዲሁም የሰው ልጅ ሕይወት እልቂት ሁሉ እንዲወገድ የሚያግዝ መንገድ መሆኑም አብራርተው፣ ለዚያ ክልል የሰብአዊ እርዳታ ማቅረብና በሁለቱ ተቀናቃኝ ኃይሎች እጅ የሚገኙት ምርኰኞች ነጻ መልቀቅ ወደ ሰላም ማቅናት ማለት ነው እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ ውጥረት ባለበት ክልል የሚኖረው ሕዝብ ያጋጠመው ድኽነት ጸጥታናና ደህንነት እጦት የተሟላ የሕክምና አገልግሎት እጥረት በሚያስከትለው ማኅበራዊ ችግር እጅግ ለዘርፈ ብዙ አደጋ የተጋለጠ ሲሆን፣ ለስደትና ለመፈናቀል አደጋ ለተጋለጠው የመቁሰል አደጋ ላጋጠመው ዜጋ ሁሉ ቅድስት መንበር በተለያዩ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበራት አማካኝነት ቅርብ በመሆን ድጋፍ ከማቅረብ ወደ ኋላ እንደማትል በማረጋገጥ፣ በዚሁ ዘርፍ የዓለም አቀፍ ማኅበርሰብ ሱታፌ ላይ እማኔው አላት እንዳሉ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.