2015-03-26 16:04:00

በዓለም ዙርያ ሕይወታቸው ያጡ ልዑነ ቅዱስ ወንጌል ለማስታወስ ዕለተ ጾምና ጸሎት


ቤተ ክርስትያን ትናትና በዓለም ዙርያ  ሕይወታቸው  ያጡ  ልዑነ ቅዱስ ወንጌል  ለማስታወስ ዕለተ ጾምና ጸሎት በመወሰን አስባ ውላለች፣  ባለፈው ዓመት  20014 እኤአ  ሃያ ስድስት መነኮሳን በዓመጽ ሕይወታቸው እንዳጡ እና  በሰማዕትነት ማለፋቸው  የሚታወስ ነው። 

በያዓመቱ ቅዱስ ወንጌል እያበሰሩ በሰማዕትነት የሚያልፉ የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ልጆች በርካታ እንደሆነ ተመልክተዋል።

ፊደስ የዜና አገልግሎት እንዳመለከተው ከ1980 እንደ ጎርጎርዮስ አቁጣጠር እስካ ላፈው ዓመት  20014 ዓመተ ምሕረት  1062 ልዑካነ ቅዱስ ወንጌል  በሰማዕትነት አልፈዋል።

የሚስዮ ተቋም ዳይረከተር ሚኪኤለ አውቶሮ እንዳስገነዘቡት ፡ ጠቅላላ ቅዱስ ወንጌል እያበሰሩ እና ከድሆች ጐን ቆመው እያሉ ሕይወታቸው ላሰላፉት ሁሉ ለመዘከር ዕለተ ጾምና ጸሎት ተዘክረው መዋላቸው ድንቅ ነው ቤተ ክርስትያን በየዘመናቱ ሰማዕታት ትከፍላለች።

በዚሁ የጾም እና ጸሎት ዕለት ከሳላሳ አምስት ዓመታት በፊት በሳን ሳልቫዶር ርእሰ ከተማ ስላቫዶር በቤተ መቅደስ ቅዳሴ እያሳረጉ እያሉ በዓመጽ የተገደሉ እና የብጽዕናቸው ሂደት እየተካሀደ ያለውን ብጹዕ አቡነ ኦስካር ሮመሮ ከፍ ባለ መንፈሳዊ ሁኔታ ተስታውሰዋል።

ባለፉት ዓመታት በሰማዕትነት ያለፉ ልዑካነ ቅዱስ ወንጌል በላቲን አመሪካ መሆኑ ተያይዞ ተመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.