2015-03-25 14:11:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ.፦ እያንዳንዱ ሰው ለእግብዚአብሔር የተቀደሰ ነው


በፐሩ በምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እ.ኤ.አ. መጋቢት 24 ቀን 2015 ዓ.ም.  የሕይወት ባህል ለማነቃቃት ማንኛውም ዓይነት የሞት ባህል የሆነውን ተግባርና አስተሳሰብ ለመቃወም ዜጎች ለሕይወት ባህል ማነጽ በሚል ዓላማ ሥር ስለ ሕይወት የእግር ጉዞ መርሃ ግብር መከናወኑ ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በፐሩ ርእሰ ከተማ ሊማ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ኹዋን ልዊስ ቺፕሪያኒ ቶርነ አማካኝነት በእግር ጉዞ ለተሳተፉ ሁሉ መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን በዚህ ሕይወት ይኑር የሚል መርህ ቃል በማስተጋባት ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት የሰው ልጅ ሕይወት መከላከልና የሕይወት ባህል ማነቃቃት በሚል ዓላማ በተጠራው  የእግር ጉዞው መርኃ ግብር በመንፈስና በጸሎት ተሳታፊነቸው በማረጋገጥ፣ ሁሉም በእግዚአብሔር አርአያና አምሳያ የተፈጠረው በክርስቶስ መስቀል የዳነው የሰው ልጅ ሕይወት ያለው የተቀደሰ ባህርዩ እንዲመሰክሩና ይኽንን ሕይወት ለእግዚአብሔር ቅዱስ መሆኑ በጽናት ያውጁም ዘንድ አደራ ማለታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.