2015-03-24 11:27:00

በደቡብ ሱዳን12 ሺ የሚሆኑ ሕጻናት በውትድርና እንዳሉ ተገለጠ፤


የደቡብ ሱዳን መንግስት እና በቀድሞው ረዳት ፕረሲዳንት ሪክ መቸር የሚመራ የዚሁ መንግስት ተቃዋሚ ቡድን በ2013 እኤአ የእርስ በእርስ ጦርነት ከገጠሙ ወዲህ ሁለቱም በየፊናቸው 12 ሺ ሕጻናት ለውትድርና ምልመላ ማቅረባቸው የተባበሩት መንግስታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት Unicef ከሰጠው መግለጫ ለማውቀ ተችለዋል፣

በየምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን ኢጋድ በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ላይ መንግስት እና በዓማጺ ኀይሉ ለማስታረቅ ሲያካሄደው የሰነበተውን የሰላም ድርድር መክሸፉ የጠቀሰ Unicef የተባበሩት መንግስታት የሕጻናት መርጃ ተቋሙ  ሁለቱ ወገኖች ህጻናትን  ለውትድርና  ምልመላ   ሊያጠናክሩት እንደሚችሉ  ያላውን ስጋት ገልጠዋል።

በሱዳን ዳኒኤል ኮምቦኒ ማሕበር የበላይ ሐላ አባ ዳኔኤለ ሞስኮቲ ጦር መሳርያ ያነገቡ ሕጻናት ማየቴ ልምስከር እችላላሁ ብለዋል፣

ደቡብ ሱዳን ከሰሜናዊ ሱዳን ነፃ ለማውጣት በተካሄደው የረጂም ዓመታት ግጭት ከሁለት ሚልዮን በላይ ደቡብ ሱዳናውያን ለሕልፈት የተዳረጉ ሲሆን አሁንም አለ መታደል ሆኖ እነሆ እርስ በርሳቸው መገዳደል ይዘዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.