2015-03-23 14:46:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በናፖሊ ክፍለ ከተማ ስካምፒያ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም. በኢጣሊያ ካምፓኒያ ክፍለ ሃገር  በሚገኘው ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ በመቀጠልም በናፖሊ ከተማ ሐውፆተ ኖልዎ ማካሄዳቸው ሲነገር፣ በዚያ በማኅበራዊ ሰብአዊ እንዲሁም በተለያየ ዘርፍ እጅግ የተጠቃው አደገኛና ውጣ ውረድ የተሞላው በናፖሊ በሚገኘው ክፍለ ከተማ ስካምፒያ ተገኝተው መሪ ቃል መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጓራሺ ገለጡ።

ቅዱስነታቸው የናፖሊ ሐውፆተ ኖልዎ በዚያ ሃይማኖተኛ ተብሎ በሚነገርለት የናፖሊ ከተማ ሕዝብ መለያ በሆነው በኃሴት መንፈስ የተመራ እንደነበርና፣ በክፍለ ከተማ ስካምፒያ በብዙ ሺሕ በሚገመቱ ሕፃናት በክልሉ ነዋሪ ሕዝብ በቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸው በለገሱት ምዕዳን፣ የናፖሊ ሕዝብ መጻኢን በተስፋ እንዲመለከት በማሳሰብ ብሩህ መጻኢ የሚገነባው ቅንና ግብረ ገብ ሕጋዊንትና ፍትሕ በሚኖርበት የአሁኑ ጊዜ መሆኑ ገልጠው፣ “የጥፋት የኢፍትሃዊነትና የሕገ ወጥነት በጠቅላላ በፈቃዱ የክፋት መንገድ የሚመርጥ አንድ የተስፋ ጨረፍ እንዲሰረቅ ያደርጋል፣ ከገዛ እራሱና ከሌላው ከዚያ ቅን ታታሪ ከሆነው ሕዝብ ሁሉ ከሚኖርበት ክልል ካለው ቅን ኤኮኖሚ፣ በክልሉ በተስተካከለ ቅን ሕይወት ከሚኖረው ስደተኝኛ ዜጋ ተስፋ እንዲሰረቅ ያደርጋል። ስደተኛው የኅብረተሰብ ክፍል በሁለተኛ ደረጃ የሚቀመጥ ዜጋ ነውን? እንዲህ መሆን የለበትም ሁላችን እንደ የአንድ አባት ልጆች ወንድማምቾች ነን፣ ስለዚህ መጻእተኛ የለም፣ ሁላችን በዚህች ምድር መጻእተኞች ነን” እንዳሉ ጓራሹ አስታወቁ።

ቅዱስነታቸው በለገሱት ምዕዳን በናፖሊ በተለይ ደግሞ በስካምፒያ ክፍለ ከተማ የሚታየው የሥራ አጥነት ችግር በማስመልከትም፦ “አቢይ ችግር አለ መመገብ አይደለም፣ አስከፊው ችግር ወደ ቤት የላብ ወጤት የሆነውን የዕለት እንጀራ ይዞ አለ መግባት ነው። ዕለታዊ እንጀራ የወዝ ውጤት ካልሆነ ሰብአዊ ክብር ይጠፋል፣ ሕዝብ የሚከፋፍል ሌላውን እንደ ጥራጊ የሚመለከት የሚበዘብዝ የኤኮኖሚ ስልት መቃወም አለብን። ስንቱ ካለበት ችግር አንጻር ለተለያየ የብዝበዛ አደጋ ተጋልጦ ይገኛል፣ በቀን 11 ሰዓት ሠረቶ በወር 600 ኤውሮ ተከፋይ መሆን፣ የሥራ አጥነት ችግር ለዚህ ዓይነት ችግር ያጋልጣል፣ ለተበዝባዥነት አደጋ ያጋልጣል፣ ስለዚህ ሰብአዊ ክብራችንን እናስከበር፣ ስለ ሰብአዊ ክብራችን እንቁም፣ ሕግ አለ ማክበር ለመጻእተኞች በር መዝጋት፣ ሥራ የማግኘት መብትና ክብር መርገጥ፣ ሙስናና ምግባር ብልሽት ያስከትላል፣ ሕግ አለ ማክበር ለሙስና ይዳርጋል፣ ስለዚህ ጉቦ ተቀባይና ሰጭ እንዲወለድ ያደርጋል፣ ማንም እኔ ከሙስና ነጻ ነኝ የሚል ያለ አይመስለኝም። ከተሞቻችን የምግባረ ብልሽትና የሙስና ጠረን የተሞሉ ሆነዋል” ያሉት ቅዱስ አባታችን ይኸንን ሁሉ ጸረ ሰብአዊ መብትና ክብር የሆነው ተግባር ለመዋጋት ብሎም ለማጥፋት፦ “መልካም ፖሊቲካ ሥነ ምግባር የተካነ ቅን ፖሊቲካ ያስፈላጋል። ፖሊቲካ የላቀ የፍቅር መግለጫ ነው። ለፍቅርና ስለ ፍቅር የሚፈጸም አገልግሎት ነው። ቅን ፖሊቲካ  ስለ ሁሉም ለሁሉም እርስ በእርሳችን ቅን ፖሊቲካ መኖር ይገባናል” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጓራሺ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.