2015-03-11 19:08:00

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፤


 

ውድ ወንድሞችና እኅቶች! በዛሬው ትምህርተ ክርስቶስ ስለ አያቶች የጀመርነውን አስተንትኖ እነሱ በቤተሰብ ላይ ስላላቸው ዕሴትና አስፍላጊነት ላይ በማትኮር እንቀጥላለን፣ ይህን ሳደርግ እኔንም ጭምር በማካተት ነው ምክንያቱም እኔም በአያቶች ዕድሜ ክልል እገኛለሁና፣ ለሐዋርያዊ ጉብኝት ፊሊፒንስ በሄድኩበት ጊዜ የፊሊፒንስ ነዋሪዎች “ሎሎ ኪኮ” እያሉ ሰላምታ አቀረቡልኝ፤ ትርጉሙም አያታችን ፍራንቸስኮ ማለት ነው፣

እዚህ ላይ አንድ ነገር ለማብራራት እወዳለሁ! እውነት ነው ኅብረተሰባችን ሊያገለን ይሞክራል እግዚአብሔር ግን እንደዛ አይደለም፣ እግዚአብሔር በምንም ተአምር ማንንም አይገልም፣ እርሱ በማንኛው ዕድሜ የሚገኙትን እንዲከተሉት ዘወትር ይጠራል፣ በዕድሜ መግፋት ራሱ የቻለ ግርማ ሞገስና ሐዋርያዊ ተልእኮ ያለው ሆኖ እውነተኛ የጌታ ጥሪ ነው፣ ሽምግልና የጌታ ጥሪ ነው፣ ገና መሣርያን የመጣል ጊዜ አይደለም፣ ይህ የሕይወት ዘመን ከቀደሙት ዓመታት የተለየ መሆኑ የማያጠራጥር ነው ነገር ግን ማኅበረሰቦቻችን በመንፈሳዊ መንገድም ይሁን በግብረ ገብ ሊቀበሉት ዝግጁ ስላልሆኑ ለዚሁ የሕይወት ዘመን የሚገባውን ክብርንና ዕሴትን በማልበስ እንደገና አዲስ ትርጓሜ ልንሰጠው ያስፈልጋል፣ ባለፉት ዘመናት እንደዘመናችን  የዕድሜ ባለጠግነት አልነበረም ዛሬ ግን ብዙ ነው፣ በመንፈሳዊው የክርስትና ጉዞም ለረዥም ዕድሜ የሚያገልግል ዝግጅት ስላልተደረገ አሁን የሽማግሌ መንፈሳዊ ጉዞ የሚረዳ ትምህርት ያስፈልጋል፣ ያም ሆነ ይህ እግዚአብሔር ይመስገን የብዙ ቅዱሳንና ቅዱሳት ሽማግሌዎች ምስክርነት አለ፣

ባለፈው ዓመት በዚሁ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የአዛውንቶች ዓለም አቀፍ ቀንን ለማስታወስ ያደረግነው በዓል ትዝ ይለኛል አደባባዩ ከጠርዝ  እስከ ጠርዙ አዛውንቶች ባየሁ ጊዜ እጅግ ደስ አለኝ፣ ብዙ አዛውንቶች ለሌሎች የሚሰጡት አገልግሎት ሲተርኩ እንዲሁም በትዳር ያሉትን  ምስክርነትና በተለይ  ሰላምታ ስንለዋወጥ አንዳንዶቹ ዛሬ የትዳራችን አምሳኛ ዓመት እናከብራለን  ሌሎች ደግሞ ስልሳኛ ብለው ሲተርኩ እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነበር፣ እኔም በበኩሌ እባካችሁ ይህንን ነገር ለዘመኑ ወጣቶች በትዳር ወዲያው ለሚደክሙት ባለትዳሮች  ንግርዋቸው አልኩኝ፣ ወጣቶቹ ከአዛውንቶቹ ቃል ኪዳን በታማኝነት የመኖር ምስክርነት መሆኑን ይመልከቱ ይማሩ፣ ቃል ኪዳን በታማኝነት የመኖር ምስክርነት በአዛውንቶቹ ሲታይ እንዴት ደስ ያሰኛል፣ ይህንን ጉዳይ በቤተክርስትያንም ይሁን በኅብረተሰባዊ አመለካከት ማስተንተን አለብን፣ በሉቃስ ወንጌል ስለኢየሱስ ሕጻን ሕይወት በሚተርከው ክፍል ውስጥ ስለ ሁለት አዛውንቶች ማለት ስለ ስምዖንና ሃና ይተርካል፣ ሁለቱም ሽማግሌዎች ነበሩ አረጋዊው ስምዖንና የ 84 እድሜ  ነቢይቱ ሐና ነበሩ፣ የሐና ዕድሜን አልደበቀውም  ወንጌሉ እንደሚነግረን ይህች አዛውንት ሴት የጌታን መምጣት በታልቅ ታማኝነት ለረዥም ዓመታት በየዕለቱ ትጠባበቅ ነበር ይላል፣

የጌታን መምጣት በጣም ይመኙና ምልክቱን ማየትና ማውቅ ይፈልጉ ነበር ምናልባት በውስጣቸውም ከእድሜ መግፋት የተነሳ ተስፋ ቢቆርጡም ግን በሕይወት ዘመናቸው ቀዳሚነት ቦታ የነበረው የጌታ መምጣት ምልክት ነበር ጌታን መጠበቅ ማለት ጸሎት ማለት ነው፣ እርግጥ ማርያምና ዩሴፍ ሕጉን ለመፈጸም ሕፃኑን ወደ ቤተመቅደስ በወሰዱት ግዜ አረጋዊው ስምዖንና ሐና በመንፈስ ቅዱስ ምሬት ወደ ቤተ መቅደስ እንደወሰዳቸው (ሉቃስ ም2ቁ27) ይገልፃል፣ ለረጅም ግዜ የጠበቁት የግዜ መራዘም ባንዴ ጠፉ፣ ምክንያቱም በመጽሐፉ እንደተጻፈው ሕፃኑን ኢየሱስ ወደ ቤተመቅደስ በአስገቡት ግዜ እርሱ ደግሞ ተቀብሎ በክንዱ ታቀፈው ይላል፣ እግዚአብሔርንም አመሰገነው እንዲህም አለ አቤቱ እንደ አዘዝህ ዛሬ ባርያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ፣ ዓይኖቼ ትድግናህን አይተዋልና በወገንህ ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን ለአሕዛብ ብርሃንን ለወገንህ ለእስራኤል ክብርን ትገልጥ ዘንድ ይላል ሉቃ (ም2ቁ29-6-32)

ስምዖን ስለ እየሱስ ክብር ሲናገር በወቅቱ ገጣሚ ሲሆን ሐና ደግሞ የመጀመሪያዋ የክርስቶስ ነቢይ ነበረች፣ ያንግዜ ተነሥታ እግዚአብሔርን አመሰገነች የእየሩሳሌምንም ድኅነት ተስፋ ለሚያደርጉ ሁሉ ስለ እርሱ ተናገረች፣ (ሉቃ 2፤38)

የተወደዳችሁ አዛውንቶች ዛሬ በነዚህ ልዩ የሆኑ አዛውንቶች ቦታ እስቲ ለመገኘት እንሞክር እኛም እንደነሱ የጸሎት ገጣሚዎች እንሁን፣ ስንጸልይ የራሳችንን ቃላት እየተጠቀምን የእግዚብሔር ቃል እምደሚያስተምረን እንጠቀምባቸው፣ የአያቶችና የአዛውንቶች ጸሎት ለቤተክርስቲያን አቢ ስጦታና ሐብት ነው፣ አዛውንቶች ለመላው ሕብረተሰቡ የጥበብና የእውቀት አስተማሪዎች ናቸውና በተለይም ለአሁኑ ትውልድ ሁሌ በስራ ለሚራወጠውና ግዜ ለሌለው። ለነዚህ ወጣቶችም ቢሆን የእግዚብሔርን ምልክትና ስለ እግዚአብሔር ማስተማርና መመስከር እንዲሁም መጸለይ በጣም ያስፈልጋል፣

እስቲ ቅዱስ አባታችን የነበሩትን ቤኔዲክቶስ 16 እንመለክት የመጨረሻውን የሕይወት ዘመናቸውን በጸሎትና እግዚአብሔርን ቃል በባሕታዊነት ለመኖር ወሰኑ ይህ ደስ የሚያሰኝ ነው፣

የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ የታወቁት ኦሊቨሪ ክሌሜንቴ የሕብረተሰብ እድገት ምልክት በጸሎት ሲያስቀምጡት ይሕም ጸሎት የሌለበት እድገት ለአዛውንቶች ቦታና ዋጋ የማይሰጣቸው ነው ይላሉ። ይሕ በጣም ያሳዝናል እኛ በሕብረተሰባችን በቀዳምነት አዛውንቶች ያስፈልጉናል። የነሱ ጸሎት ያስፈልገናል የአዛውንቶች ጸሎት ያማረና ለሕብረተሰባችን  በጣም አስፈላጊ ነው።

እኛ እግዚአብሔር ስላደረገልን መልካም ነገር ሁሉ ልናመሰግነው ይገባናል በጸሎት በውስጣችን ያለውን ባዶነት ልንሞላ እንችላለን። በጸሎት ለሚመጣው ትውልድ ልጆች መለመንና እንዲሁም ያለፈውን ትውልድ ኽብር ታሪክና መስዋዕትነትን እናስታው።

ወጣቶች ያለ ፍቅርና የደረቀ ሕይወት ለገንዘብና ስልጣን ብቻ እንዲሆን አንፈልግም። በተለይም ለአሁኑ ወጣቶች የወደፊቱን ሕይወታቸው አስመልክቶ ፍርሃትና ጭንቀት የተሞሉት ማሸነፍ እንደሚቻል እናስተምራቸው። ወጣቶችን ራስ ወዳጅ የሆኑትን ሌሎችን መርዳት የሚሰጠው ደስታ ከሁሉም የሚበልጥ መሆኑን እናስተምራቸው። አዛውንቶች አንድ ሕብረተሰብን በስራና በሕይወት ትግል የሚረዱና የሚንከባከቡ ለቤተክርስቲያንም የጸሎት ድጋፍ ናቸው።

ጸሎት በመጨረሻ ልባችንን ያነፃል። እግዚአብሔርን ማመስገንና መለመን የልባችንን ደንዳናነትና ከእኛ ራስ ወዳድነት ነፃ ያወጣናል፣

የሕይወት ትርጉምን ያጣ አዛውንትና ወጣቶችን የሚጠላ እንዴት ያሳዝናል እንዲሁም ወጣቶችን የሚንከባከብና አይዞህ አያለ የጸሎትና የሕይወት ትርጉም እያበረታታ የሚደግፍ አዛውንት እንዴት ያስደስታል፣ ይህ ነው እውነተኛ የአዛውንት ጥሪና ተልእኮ። አያቶች ያሉት ለወጣቶች ልዩ ትዝታና ትምህርት ሆኖ ይቀራል እኔ ካህን ስሆን አያቴ የሰጠችን ደብዳቤ እስካሁን ድረስ አለ ብዙ ግዜ ኣነበዋለሁኝ ይደግፈኛል፣

ምኞቼ የዘመኑን አመለካከት መለየትና መገለል የሚቃወም ቤተክርስትያን ሁሉንም በሕብረት ወጣትና አዛውንት በደስታ የምታቅፍና የምታጣምር ቤተክርስቲያን ነው ስለዚህ ዛሬ ለእግዚአብሔር ይህንን በመተቃቀፍ እንጠይቀው፣








All the contents on this site are copyrighted ©.