2015-02-27 16:23:30

የ “Centesimus Annus-Pro Pontifice-መቶኛው ዓመት ደጋፊ ር.ሊ.ጳ. ማኅበር”


RealAudioMP3 በየሁለት ዓመት “Centesimus Annus-Pro Pontifice-መቶኛው ዓመት ደጋፊ ር.ሊ.ጳ. ማኅበር” ኤኮኖሚና ኅብረተሰብ ሰይሞ የቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ ትምህርት ከኤኮኖሚና ቁጠባ ሂደት ጋር በማጣመር ለኤኮኖሚው ዓለምና ኅብረተሰብ አቢይ አስተዋጽኦ ከሚሰጡት ሊቃውንትና ምሁራን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱት መርጦ የሚሰጠው ሽልማት በመቀጠል እ.ኤ.አ. የ 2015 ዓ.ም. ሽልማትና ብቁ ብሎ የመረጣቸው በማስደገፍ በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ መሰጠቱ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።
የንግድ ድርጅት ፖሊቲካና የኤኮኖሚ ፖሊቲካና የቤተ ክርስቲያን የማኅበራዊ ትምህርት የሚያቀርበው መሠረተ ሃሳብ በመከተልና ይኽ ትምህርት ፈጣን ድርጊት የሚጠይቅ በሎና ለይቶ የሚያስቀምጠው መርኅ ጋር ማገናኘት ይቻላል? ጦቢያነትና የንግድ ድርጅት የኤኮኖሚ እድገት ብሎ የሚያስቀምጠው ይፋዊ አዝማሚያ ከሥነ ምግባር መሠረታዊ መመሪያ ጋር ተያይዞ እንዲሄድ የሚለው አመለካከት ለረዥም ዓመታት ሳይሳካ መቅረቱ ለምን ይሆን? በተለይ ደግሞ ይኽ ግኑኝነት ሊኖር አይችልም የሚለው በተለያየ መስክ የሚነዛው አስተያየት “Centesimus Annus-Pro Pontifice-መቶኛው ዓመት ደጋፊ ር.ሊ.ጳ. ማኅበር” የማይስማማበትና ተቀባይነት የሌለው ብሎ የሚያምንበት ጉዳይ ሲሆን፣ ይኽ ደግሞ እ.ኤ.አ. ከ 1993 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ር.ሊ.ጳ. ሊዮነ አስራ ሦስተኛ የደረሱት የቤተ ክርስቲያን የማኅበራዊ ትምህርት ጉዳይ በተመለከተ የመጀመሪያው ዓዋዲ መልእክት ተብሎ የሚነገርለት አዳዲስ ነገሮች የተሰኘው ዓዋዲ መልእክት ዝክረ መቶኛው ዓመት ምክንያት መቶኛው ዓመት በሚል ርእስ ሥር በደረሱት ዓዋዲ መልእክት ክርስቲያናዊ ግብረ ገብ በኤኮኖሚውና ቁጠባው ዓለም እንዲኖር ለማድረግና ይኽ ዓይነት ግኑኝነት ተቻይ መሆኑ በተካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ ንግግር ያስደመጡት የዚህ Centesimus Annus-Pro Pontifice-መቶኛው ዓመት ደጋፊ ር.ሊ.ጳ. ማኅበር ሊቀ መንበር ዶሚንጎ ሱግራንየስ ቢከል እንዳሰመሩበት የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜኛ ደ ካሮሊስ አያይዘው፦ ሊቀ መንበር ቢከል በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ለተሰበሰቡት ጋዜጠኞች፥ “በአሁኑ ወቅት በዓለም የሚታየው ድኽነት ለመቅረፍ የሚቻልበት መንገድ ለማፈላለግ ብዙ ጥረትና ውይይት ሲከናወን እናያለን፣ ድኽነት መቅረፍ የሚለው ፍላጎት በተጨባጭ ለመተርጎም እንዴት ይቻላል” የሚል ጥያቄ አቅርበው፦ “ይኽ በሳቸው የሚመራው ማኅበር 18 ነጥብ ያካተተው የዱብሊን ሰነድ ተብሎ የሚጠራው ባንኮች ወደ ኤኮኖሚው ለማቅረብና ሙስና ምግባረ ብልሽት እንዴት ለመዋጋትና ብሎም ለማጥፋት እንዲሁም የተገልጋይ ሕዝብ መብትና ክብር ጥበቃ ለማረጋገጥ የሚደገፍ ነው፣ ስለዚህ ይኽ ሁሉ ሃሳብ ተጨባጭ ለማድረግ የንግድ ኤኮኖሚው ማደስ ያስፈልጋል፣ በመሆኑም የቤተ ክርስቲያን የማኅበራዊ ትምህርት ከኤኮኖሚው ዓለም ጋር ማገናኘት ጦቢያ ነው ብሎ መግለጥ አቢይ ስህተት ነው” እንዳሉ አስታውቀዋል።
በተካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ የተሳተፉት የዘንድሮ ሽልማት የመራጭ ዳኞች ምክር ቤተ አባል ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮ ስኮቲ “ሌላውን ማግለልና ተጠቅሞ መጣል የሚል አመለካከት፣ ለያይና አግላይ የኤኮኖሚ ሂደት፣ ቁጠባና ኤኮኖሚ የገበያና የገንዘብ ሃብት ክብረ መለኪያ አገልጋዮች ማድረግ መወገድ አለበት የሚል ነው። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ወደ የከተሞቻችንና የህልውና ጥጋ ጥግ ማቅናት በማለት የሚሰጡት ሥልጣዊ ትምህርት መሠረት ያደረገ ሃሳብ ነው። ቅዱስነታቸው ‘ነጣይ ባህል’ በማለት የሚገልጡት ሃሳብ በዓለማችን የሚታየው የተጠቅሞ መጣል ምርጫ እያዛመተ ነው፣ ሰው ሳይቀር ትጠቀምበትና ከተጠቀምክበት በኋላ አታስፈልግም ብሎ መለየት፣ እንደ ጥራጊ መመልከት የሚያስከትለው አልቦ ፍትህና እኩልነት የለሽ አካሄድ ለማስወገድ የሚደረገው ጥረት የዘንድሮው ሽልማት ይኸንን አቢይ ነጥብ ግምት የሰጠ ነው” ሲሉ ቀጥለው ንግግር ያስደመጡት የመራጭ ዳኞች ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ፕሮፈሰር ሚካኤል ኮንራድ ነጻው ኤኮኖሚ በሥነ ምግባር የተመራ ሲሆን ፍትሃዊ ይሆናል በሚል እሳቤ አዲስ የኤኮኖሚ ሂደት የተነተኑት የሥነ ባንክና ሥነ ቁጠባ ሊቅ ፈረንሳዊ ፒየር ደ ላኡዙን የ 2015 ዓ.ም. ሽልማት ብቁ ተብለው እንዲመረጡ አድርገዋል። ገበያ እንደ ስፖርት ነው። ሕግና ደንብ ያስፈልገዋል፣ ስለዚህ ውድድር እየተካሄደ ባለበት ወቅት ሕግ የውደራው አይደነገግም፣ ግጥሚያው ከመጀመሩ በፊት የውድድሩ መርህ ሕግ ይሆናል የሚባለው ቀድሞ መደንገግ ያስፈልጋል፣ ሕጉ ደግሞ ግብረ ገብና ሥነ ምግባር መሠረት ያደረገ መሆን አለበት” ብለው በተጨማሪም የቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ ትምህርት አጥኚ የኡሩጉዋይ ተወላጅ 34 ዓመት ዕድሜ ያለው ወጣት አርቱሮ በሎክ ሞንታኖ የቤተ ክርስትያን ማኅበራዊ ትምህርት ሥነ ምርምራዊ ገጽታው በማጉላት እየሰጡት ላለው አስተዋጽኦ ግምት በመስጠት እንዲሁም አለክሳንደር ስቱምቮል የኦስትሪያ ተወልጃ 32 ዓመት ዕድሜ ያላቸው የቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ ትምህርት በዓለምእ አቀፍ ግኑኝነቶች ርእሰ ጉዳይ ልዩ ጥናት በማካሄድ በዓለም አቀፍ ግኑኝነቶች ትግባሬው እንዴት ማረጋገጥ እንደሚቻል ልዩ ጥናት በማድረግ የሰጡትና እየሰጡት ያለው አስተዋጽኦ ሦስተኛው ለዚህ ሽልማ ብቁ ተብለው መመረጣቸው ብፁዕ አቡነ ስኮቲ ባስደመጡት ንግግር እንደገለጡ ደ ካሮሊስ አስታውቀዋል።
በዓለማችን ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ በቤተ ክርስቲያን የማኅበራዊ ትምህርት ሥር በተለይ ደግሞ ወንጌላዊ ኃሴት” በሚል ርእስ ሥር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያስተላለፉት የቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ ትምህርት ሥር በመተንተን ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ ኤኮኖሚና ቁጠባ ለተሟላ እድገት መሠረት ማድረግ በሚለው ራእይ መመራት እንዳለበት ቢከል ባስደመጡት ንግግር አብራርተው ይኽ ደግሞ ለኤኮኖሚውና ለቁጠባው ሂደት ማእከል ሰብአዊ ፍጡር እንጂ ትርፍ መሆን እንደሌለበት የሚያስተምር ነው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጉባኤ ፊት ተገኝተው ያስደመጡት ንግግር የሚያረጋግጥ ሃሳብ ነው እንዳሉ ደ ካሮሊስ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.