2015-02-23 16:53:25

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ (እ.ኤ.አ. የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም.)
ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ዓቢይ ጾም ፊት ለፊት ጸረ የክፋት መንፈስ የምንታገልበት ወቅት ነው


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ “ዓቢይ ጾም ጸረ የዲያብሎስ ወጥመድ የምታገልበትና ከዚህ ጥብቅ ትግል የልብ መለወጥ የሚፈልቅበት ወቅት ነው” በሚል ቅዉም ሓሳብ ላይ ያነጣጠረ አስተንትኖ እ.ኤ.አ. የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም. እኩለ ቀን ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ ሁሌ እንደተለመደው በላቲን ሥርዓት የዕለተ ሰንበት ምንባብ ተንተርሰው የሚለግሱት ስብከት እንዳቀረቡ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አክለው፣ ቅዱስ አባታችን የለገሱት ስብከት አጠቃለው ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር አሳርገው እንዳበቁም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከውስጥና ከውጭ ለተሰበሰበው ምእመን ሁሉ በዚህ የዓቢይ ጾም ወቅት ለግል አስተንትኖ የሚደግፍ አንድ አነስ ያለ የአቢይ ጾም የአስተንትኖ መጽሓፍ መለገሳቸው አስታውቀዋል።
ከክፋት መንፈስ ጋር እጅ ልእጅ የምንገጥምበት የምንታገልበት ሁነት የጸጥታና የዲያብሎስ ወጥመድ ለይተን የምናውቅበትና በእግዚአብሔር እርዳታ ድል የምንነሣበት ጊዜና ቦታ እንደሚያስፈልግ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በለገሱት ስብከት አብራርተው፣ ልክ ጌታችን ኢየሱስ በአሕዛብ ዘንድ ተልእኮው አንድ ብሎ ከመጀመሩ በፊት ገዛ እራሱን ሰብሰብ ለማድረግ በሱባኤ መልክ ምድረ በዳ እንደ መረጠ አስታውሰው ይኸንን መሠረት በማድረግ ከነፍሳችን ውጭና ውስጥ ምድረ በዳ ያለው አስፍፈላጊነት ገልጠው “ኢየሱስ በዚያ የጽሞናና የብቸኝነት አረባ ቀንና ሌሊት ሰይጣንን ፊት ለፊት ገጥሞ የዚያ የክፋት መንፈስ ፈተና ሁሉ በማጋለጥ ድል ነሣ፣ ሁላችን ድል ባደረገው ኢየሱስ ድል አድርገናል፣ ስለዚህ በዕለታዊ ሕይወታችን ያንን ድል የመከላከል ኃላፊነት አለብን፣ ቤተ ክርስቲያን ይኸንን ሁሉ በዓቢይ ጾም መግቢያ ወቅት ታስታውሰናለች፣ ምክንያቱም የክፋት መንፈስ የምንገጥምበት ወቅት በመሆኑም ነው። በምድረ በዳነት የሚኖረ ጽሞና የሚሰማ የእግዚአብሔር ድምጽ ነው። ጽሞና የእግዚአብሔር ድምጽ ሲሆን፣ የዲያብሎስ ድምጽ ጭምር የሚሰማበት ሁነት ነው፣ ወደ ጥልቀታችን በመግባት ሕይወት ወይም ሞት የተሰኘው እጣ እድላችን ግጥሚያ የሚያካሂዱበት ሁነት ነው፣ የእግዚአብሔር ድምጽ እንዴት ለመስማት እንችላለን? የእርሱ ድምጽ ከቃሉ ነው የምንሰማው፣ እንዲህ በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ ማወቅ ማንበብ ያስፈልጋል፣ እንዲህ ካልሆነ ግን የክፋት መንፈስ ለሚደቅንብን ፈተና የተገባ መልስ ልንሰጥበተ አንችልም፣ ወንጌል ታነቡ ዘንድ አደራ እላችኋለሁ፣ በየዕለቱ ወንጌልን ቢያንስ ላንድ አስር ደቂቃ ማንበብና ማስተንተን ፣ ዓቢይ ጾም ለዓለም መንፈስና ጣዖቶቹ ሁሉ እምቢ እንድንል ያግዘናል፣ ከወንጌል ጋር የሚስማማ ጽኑ ምርጫ እናደርግ ዘንድ ብርታት ይሰጠናል፣ ከወንድሞቻችን ጋር እንተባበርም ዘንድ ይረዳናል” እንዳሉ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቀጥለውም እ.ኤ.አ. ጥር 23 ቀን 2015 ዓ.ም. እሳቸውና የሮማዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የቅርብ ተባባሪዎች አበይት አካላት ብፁዓን ካርዲናሎችና ጳጳሳት የሚያሳትፈው በዚህ በዓቢይ ጾም ወቅት የሚካሄደው መንፈሳዊ ሱባኤ የሚጀመርበት ቀን መሆኑ አስታውሰው፦ በዚህ ምድረ በዳ እኔና የቅርብ ተባባሪዎቼ አበይት አካላት ብፁዓን ካርዲናሎችና ብፁዓን ጳጳሳት የኢየሱስ ድምጽ ለማዳመጥ የምንችልበትና ሰው እንደ መሆናችንም መጠን ግድፈቶቻችን ሁሉ ለማረም የምንበቃበትና ዕለት በዕለት የሚጋረጥብንን ፈተና ፊት ለፊት ገጥመን የምናሸንፍበት ወቅት ይሆንልን ዘንድ ስለ እኛ ጸልዩ፣ በጸሎታችሁ ሸኙን አደራ” ብለው በዚህ የዓቢይ ጾም ወቅት እምነትን እንዲኖርና የእምነት መልካሙን ትግል በሚገባ በመኖር ይወጣም ዘንድ ለሁሉም በዚያ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት ከተለያየ ክልል ለመጡት ምእመናን አደራ ብለው ሰላምታን አቅርበው በዓቢይ ጾም ወቅት ለግል አስተንትኖ የሚደገፍ “ልብን ተንከባከብ” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ትንሽ የአስተንትኖ መጽሐፍ ለግሰው በዚያች ትንሽየ መጽሐፍ የእምነታችን ይዞታ የካቶሊካዊ ትምህርተ እምነት የምናገኝበት መሆኑም ገልጠው “ይኸንን የእምነት ሃብት በልባችሁ አቅቡ” ያሉት ቅዱስ አባታችን ሁሉም ከልብ የሚጀምር መሆኑና እርሱም በዕለታዊ ሕይወታችን ክፉውንና ደጉን ዓለማዊነትና ወንጌላዊነት ግድየለሽነትና ተካፍሎ ተሳስቦ መኖር የሚለውን ምርጫ ለይተን ተገቢውን ለይቶ ለመምረጥ በሚደርገው ጉዞ የሚደገፍ መጽሐፍ መሆኑ ገልጠው፦ የሰው ዘር ፍትህ ሰላም ፍቅር ተጠምተዋል፣ ጥማቱንም ለማርካት የፍትህ የሰላምና የፍቅር ሁሉ ምንጭ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር በሙሉ ልቡ ሊመለስ ይገባዋል” ብለው ጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር ኣሳርገው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጠው መሰናበታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አመለከቱ።







All the contents on this site are copyrighted ©.