2015-02-18 20:35:14

ናሁ ሠናይ ወናሁ አዳም ሶበ ይሄልው አኀው ኅቡረ (መዝ 132፤1)!


RealAudioMP3 የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ!
ውድ ወንድሞችና እኅቶች! ሰላም እንደምን አደራችሁ! ስለቤተሰብ በምናደርገው ትምህርተ ክርስቶስ አባት እናትና ልጆች በቤተሰብ ያላቸውን ሚና ተመልክተን ነበር፣ ዛሬ ደግሞ ስለወንድማማችነት ማለትም ስለ እህትና ወንድም የሚለውን እንመለከታለን፣ እነዚህ ቃላት ክርስቲያኖች በጣም የሚያፈቅሯቸው ቃላት ናቸው፣ ለዚሁ ዓይነት የቤተሰብ መተሳሰር ምስጋና ይግባው፤ እነኚህ ቃላት በተለያዩ ባሕሎችና የታሪክ ዘመናት ሁሉም የሚረዳቸው ቋንቋ ሆነዋል፣
የወንድሟሟችነት መተሳሰር በእግዚአብሔር ሕዝብ ታሪክ ውስጥ ልዩ ቦታ አለው፤ እግዚአብሔር ለሕዝቡ የተገለጠውም በሰው ልጅ ሕይወት ሕያው ታሪክ ነበር፣ ዳዊት በመዝሙሩ ስለ ወንድሞች ሕብረት ይዘምራል ይሕም በመዝሙረ ዳዊት 132፡1 ላይ ወንድሞች በሕብረት ቢቀመጡ እነሆ መልካም ነው፣ እነሆ ያማረ ነው፣ ይላል አየሱስ ክርስቶስም እንደ ሰው ልጅ ሆኖ በመምጣት ለሰው ልጅ በወንሟሟችነትና በእህትነት ፍቅር በመኖር ይህም ፍቅር ከአባት ጋር ያለንን ፍቅር ከማንኛውም የቤተሰብ ፍቅር በላይ ሆኖ ማንኛውንም ግድግዳና ችግር ሊያሸንፍ እንደሚል ያስተምረናል፣
እንደምናውቀው ከወንድሞቻችን ጋር ያለን ሕብረት ሲበላሽ የሕይወታችን ጉዞ በግጭት ክህደትና ጥላቻ የተሞላ ይሆናል፣ ይህንንም በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ በቃኤልና በአቤል ታሪክ ስናገኘው ውጤቱም አሳዛኝ መሆኑን እናውቃለን፣ ቃኤል አቤልን ከገደለ በኋላ እግዚሕቤር ቃኤልን ወንድምህ የት ነው? ብሎ ይጠይቀዋል(ዘፍ 4፡9)፣
የሁለቱም የወንድማማቾች ሕብረት መቋረጥ ጥሩ አለመሆኑንና ለሰው ልጅም መጥፎ ነው በቤተሰብም ውስጥ ወንድሞች ለማይጠቅም ነገር ወይንም በውርሻ ይጣላሉ በመቀጠልም ይኳረፋሉ ሰላም አይባባሉም አይነጋገሩም ይህ መልካምና ተገቢ አይደለም ወንድማማችነት ትልቅ ነገር ነው፣ በተለይም ወንድሞች በአንድ እናት ማህጸን ውስጥ ለ 9 ወራት እንደተቀመጡ ስናስበው ከእናት ስጋ ነው የመጡት ይሕ አይነት ሕብረት መቋረጥ የለበትም እስቲ እናስብ ሁላችንም የተለያዩ ቤተሰቦችና ግንኙነታቸው የተቋረጠና ተጣልተውና ተለያይተው የሚገኙ እናውቃለን፣ እግዚብሔርን ስለነዚህ ቤተሰቦችና ስለኛ ቤተሰቦች እንዲህ አይነት ችግሮች ካሉ የተከፋፈለውን እንዲሰበስብና የተቋረጠውን ሕብረት ከቤተሰቡ እንዲያገናኝ እንለምነው፣
ወንድማማችነት መቋረጥ የለበትም ከተቋረጠም ለአቤልና ለቃኤል እንደሆነው ይሆናል እግዚአብሔር ቃሌልን ወንድምን የት አለ? ብሎ ሲጠይቀው፣ ቃኤል አኔ አላውቅም ስለወንድሜ ምን አገባኝ ብሎ መለሰ፣ እንዲህ አይነት መልስ መስማቱ በጣም አሳዛኝ ጎጂና አስከፊ ነው፣ በጸሎታችን ሁልግዜ በእንደዚህ ሁኔታ ለሚገኙ ወንድሞች ለተከፋፈሉት እንጸልይ፣
የወንድምነት ሕብረት የሚመሰረተው በቤተሰብ ውስጥ በልጆች መሃከል ነው ቤተሰብ ሁሉንም ስርዓትና ለሌሎችም ክፍት መሆን የሚያስተምር የነፃነትና የሰላም ት/ቤት ነው በቤተሰብ ወንድማማቾች አንዱ ከሌላው ጋር መኖርን ሲማር ይህም በሕብረተሰቡ ውስጥ መኖርን ያስተምራል፣
ምናልባት ብዙዎን ግዜ ይህንን አናስተውል ይሆናል ግን በሕብረተሰባችን የወንድማማችነት ፍቅር እንድንኖር የሚያዘጋጀን የቤተሰብ ሕይወት ነው፣ በመጀመሪያ በቤተሰብ አብሮ መኖርን በወንድማማችነት ፍቅርና ሕብረት ተነስተን የቤተሰብ ስርዓትና የወንድማማችነት ሕብረት በመላው ሕብረተሰብና አንዱ ከሌላው ሕዝብ ጋር ያለውን ግኝኙነት ያጠናክራል፣
የዚሁ የወንማማችነት ሕብረት እግዚአብሔር በልጁ በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የሰጠንን አለም ከማታስበው በላይ ዘር ሃይማኖት ቋንቋን ባሕልን ሳይል ሁሉንም ጥሶ ያለፈ ነው፣
እስቲ በተለያዩ ሰዎች ያለው ግንኙነት ሲጠብቅና አንዱ ሌላውን ይሕ እንደ ወንድሜ ነው፤ ይሕች እንደ እሕቴ ናት፤ ሲባል እንዴት እንደሚያስደስት ታሪክ እንዲህ አይነት ክስተቶችን መስክሮልናል በተረፈ ያለ ወንድማማችነት ሕብረት ነፃነትና እኩልነት የግል ጥቅም ምቾትና ሊባሉ ይችላሉ፣
ወንድማማችነት በቤተሰብ ውስጥ የሚያበራው በፍቅርና ትዕግስት ነው ይሕም በተለይ ለደካማ ለታመሙና እንዲሁም አካለ ስንኩላን ወንድሞችና እሕቶች ቤተሰብ ስለሚያደርግላቸው ልዩ እንክብካቤ ነው፣ እንዲህ አይነት ወንድሞችና እሕቶች ያሏቸው ቤተሰቦች በዓለማችን ብዙዎች ናቸው፣ ለነዚህም ቤተሰቦች ለሚያደርጉት በጎ አስተዋጾ እንደሚገባው አናመሰግናቸውም፣ በተለይም በአንድ ቤተሰብ ብዙ ወንድሞች ሲኖሩ ዛሬ 9 ልጆች ያላቸውን ወላጆች አግኝቼ ነበር ታላላቆቹ አባትና እናታቸውን እንዲሁም ታናናሽ ወንድሞቻቸውን እንደሚረዱ ነገሩኝ ይሕ በእውነቱ ደስ የሚያሰኝ ነው የሚወድህና የሚንከባከብህ ወንድምና እሕት ሲኖር ደስ የሚያሰኝ ወደር የሌለውና ሊተካ የማይችል ነው፣
በክርስቲያኑም ማሕብረሰብም እንዲሁ ነው ታናናሾች ደካሞችማ ድሆች እንድንራራላቸው ይገባል ከልባችንም ልናገለግላቸው መብት አላቸው ይገባቸዋል እነሱ ወንድሞች ከሆኑ እንደሚገባው ልናፈቅራቸውና ልናከብራቸው ይገባል ይሕ በሕይወታችን ከተከሰተ ድሆች አንደ ቤታቸው ከተሰማቸው የክርስትና ወንድሞች ሕይወት መዓዛ ይኖረዋል ክርስቲያኖች ደካሞችና ድሆችን መርዳት ያለባቸው ስነ ሐሳባዊ ፕሮግራም ለመታዘዝ ሳይሆን ግን የእግዚአብሔር ቃልና የክርስቶስ ምሳሌ ሁላችንም ወንድሞች እንደሆንን ስለሚገልጽልን ነው፣ ይህ የመጀመሪያው የእግዚአብሔር ፍቅርና ፍትሕ በሰው ልጆች ነው፣ አንድ ነገር ልንገራችሁ እስቲ ለወንድሞቻችንና ለእሕቶቻችን በጸጥታ ከልባችን እንጸልይላቸው በዚህ በጸሎት በሃሳባችንና በልባችን ወንድሞቻችንና እሕቶቻችንን በዚህ አደባባይ ቡራኼን እንዲያገኙ አድርገናል፣ዛሬ ከምን ግዜም የበለጠ ቢሮክራሲና ቴክኖሎጂ በመላው ሕብረተሰባችን ወንድማማችነትን ማዕከል ማድረግ አለብን፤ እንዲህ ከሆነ ነፃነትና እኩልነት የራሳቸውን ድርሻ ሊኖራቸው ይችላል፣ ስለዚህ ቤተሰቦቻችንን ቸል ከማለት እንጠንቀቅ አንዳንዴ ከመፍራት ይሁን ከቁጥጥር በልጆችና በቤተሰብ ያለውን ግንኙነት በቸልተኝነት እንዳናጣው በመጠንቀቅ ተስፋችንንም በእግዚብሔር በረከት በበራው እምነታችን በማስደገፍ ከተጓዝን ሰፊውን የወንድማማችነት ፍሬ ለመቅሰም እንችላለን፣







All the contents on this site are copyrighted ©.