2015-02-18 17:18:31

በጽንፈኞች በዓመጽ የተገደሉትን የግብጽ ክርስትያን
እ/ር እንደ ሰማዕታት ይቀበላቸው ር.ሊ.ጳ. ፍራንሲስ ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በቅድስት ማርታ ቤተ ጸሎት መስዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ግዜ ኢሲስ በተባለ ጽንፈኛ እስላማዊ ቡድን ሊብያ ላይ ሀያ አንድ የግብጽ ክርስትያኖች በአሰቃቂ መንገድ እንደገደላቸው በማስታወስ የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጠው ከሃሌ ኩሉ እግዚአብሔር በመንግስተ ሰማያቱ እንደ ሰማዕታት እንዲቀበላቸው ጸልየዋል። በማያያዝም ለቤተ ሰቦቻቸው ጥናቱ እንደሰጠታቸው እንደሚጸልዩ አገንዝበዋል ቅድስነታቸው እግዚአብሔር የዓመጸኞች ልቦች እንዲቀይር በመካከለኛው ምስራቅ ሰላሙ እንድያወርድም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሰማይ እና ምድር የፈተጠረ እግዚአብሔርን እንልመን ብለዋል።ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሊብያ ላይ በሚያሳዝን ሁኔታ በስለት የተገደሉ ክርስትያን በመሆናቸው ብቻ ነው ኦ እግዚአብሔር እንደ ሰማዕታት በመንግስተ ሰማያት ተቀበላቸው በማለት አክለው ተናግረዋል። የኢሲስ እስላማዊ ጽንፈኛ እና ጨካኝ ቡድን ሰዎች ጥቁር ለብሰው ሰለባዎቹን ወረፋ አሲዘው ብጫ ቱታ አልብሰው አምበርክከው ለ21 የግብጽ ዜጎች ክርስትያን አንገታቸው ለመቁረጥ ሲዘጋጁ ላየ ሰው እንዴት አስደንጋጭ መኖሩ የሚካድ አይደለም ። ራት ደቂቃ የፈጀው ዘግናኝ ክስተቱ ለአራት ደቂቃዎች በቪደዮ የተመለከቱ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ልብ የሚሰብር ፍጹም ኢ ሰብአዊ ድርጊት እንደሆነ እና የተሰማቸው ሐዘን ገልጠዋል። እሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ለግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያሪክ ብጹዕ ወቅዱስ ተዎድሮስ ስልክ በመደወል እግዚአብሔር ጽናቱ ይስጥዎት ማለታቸው እና የተሰማቸውን ከባድ ሐዘን እንደገለጡላቸው በቅድስት መንበር የተሰጠ መግለጫ አስታውቀዋል።
የግብጽ መራሄ መንግስት ፕረሲዳንት ዓብደል ፋታሕ አል ሲሲ ወደ መንበረ ፓትርያሪክ ብጹዕ ወቅዱስ ተዎድሮስ ተጉዘው የተሰማቸውን ሐዘን እንደገለጡ ተያያዞ ተወስተዋል።
በግብጽ አለሳንድርያ ወድብ ከተማ ካቶሊካዊ ፓትርያሪክ ኢብራሂም ኢሳቅ ሲድራክ የጂሃዳውያን ሰለባ ለሆኑ ቤተ ሰቦች የጽናቱ ይስጣችሁ መልዕክት ማስተላለፋቸው ተመልክተዋል ።በጂሃዳውያን በግፍ የተገደሉ የክርስትና እምነት የሚከተሉ 21 የግብጽ ዜጎች የዚሁ ዓመት ግልጽ ሰማዕታት መሆናቸው ፓትርያሪክ ኢብራሂም ኢሳቅ ሲድራክ በላኩት መልዕክት ማስገንዘባቸው ተገልጠዋል።የግብጽ አልዛሀር ዩኒቨሪሲቲ የሃይማኖት ላዕላይ ባለ ስልጣን ሊብያ ላይ ጂሀዳውያን በግብጽ ዜጎች ላይ የፈጸሙት ግድያ ከአስላም ሃይማኖት ግንኙነት የሌለው የሽበራ ተባር መሆኑ መግለጫ መስጠቱ ከቦታው የደረስ ዜና አስታውቀዋል። ህ በዚህ እንዳለ የግብጽ አየር ኀይሎች በሰሜናዊ ምስራቅ ሊብያ ደርና በተባለ ቦታ መሽገው የሚገኙ ጂሃዳውያን መጥቃታቸው እና 50 ጂሃዳውያን እና ሶውስት ሲቪሎች መገደላቸው ተገልጸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.