2015-02-16 17:22:13

የካርዲናል ሥራ “ከቤተ ክርስትያን የራቁትን አለምንም ቅድመ ሁኔታ መፈልግና ማንንም አለማግለል” ነው፣


RealAudioMP3 ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ቅዳሜ ዕለት የካርዲናልነት ሥልጣን ከሰጥዋቸው 20 አዳዲስ ካርዲናሎች ጋር የምስጋና መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉት ጊዜ የአዳዲስ ካርዲናሎች ዋና ሥራ “ከቤተ ክርስትያን የራቁትን አለምንም ቅድመ ሁኔታ መፈልግና ማንንም አለማግለል” እንደሆነ ገልጠዋል፣
የቤተ ክርስትያን መንገድ አለምንም ቅድመ ሁኔታና ፍራቻ ከእርሷ የራዉት መፈለግ ሲሆን አዳዲስ ካርዲናሎቹም ጌታ ኢየሱስ በዘመኑ በፍራቻና በቅድመ ሁኔታ በገዛ ራሳቸው ተዘግተው ለነበሩ እንዳናወጠ ሁሉ ፈሩን በመከተል በዘመናችን በተለያዩ ምክንያቶች ተገለው ለሚገኙ ሰዎች ማገልገል እንዳለባቸውም አሳስበዋል፣ ምናልባት ይህ ሥልጣን መስሎዋቸው ገዛ ራሳቸውን ከፍ በማድረግና የአንድ ከፍተኛ መኳንንት አባል ከማድረግ ፈተና መጠንቀቅ እንዳለባቸው ምክንያቱም የዚህ ዓይነት አስተሳሰብ ከቤተ ክርስትያን ጋር የሚያገናኝ ምንም የለውምና ብለዋል፣
በላቲኑ ሥር ዓተ አምልኮ መሠረት ትናንትና የተነበበው የወንጌል ክፍል ከማርቆስ የተወሰደ ሲሆን “ከፈልግ ከለምጼ ልታነጻኝ ትችላለህ” በማለት በትሕትና ወደ ኢየሱስ የቀረበው ለምጻም ጌታ ወደ እርሱ ቀርቦ በእጁ ነካ አድርጎ “እፈቅዳለሁ ንጻ” ባለው ጊዜ ከለምጹ እንደነጻ ነገር ግን ጌታ ኢየሱስ ነጻ የሆነውን ለምጻም ሙሴ እንዳዘዘው አስፈላጊውን መባእ ማቅረብና ገዛ ራሱን ወደ ካህን ሄዶ ማሳየት እንዳለበት ነግሮ ለማንም እንዳይነግር ቢያስጠንቅቀውም የነጻው ለምጻም ወሬውን በመላዋ ከተማ ስለነዛው ጌታ ኢየሱስ በከተማው ለመግባት እንዳልቻለና በከተማው በረሃ አከባቢ ቢቆይም ሕመምተኞች ግን ባለበት እየሄዱ ይፈወሱ እንደነብር ወንጌሉ ይገልጻል፣ ቅዱስነታቸውም ይህንን የወንጌል ታሪክ ባለንበት ዘመን ዓይን በመመልከት ያኔ ከኅብረተስቡና ከቤተሰቦቹ ርቆና ማንም ሊቀርበውና ሊነካው የማይችለውን አለምንም ፍራቻና ቅድመሁኔታው ፍርዶችን በመጣስ ለምጻሙን ለመፈወስ ቻለ፣ ራራለት! ርኅራኄውን ለማሳየት ደግሞ ፍራቻም ይሁን ኃፍረት አልተሰማውም፣ አዲሱ ሙሴ የሆነው ኢየሱስ ያ አሮጌው ሙሴ ከሕዝቡ እንዲለይ ማንም እንዳይነካው የከለከለውን ሕግ በማሳደስ ለምጻሙን አነጻው፣ ለምጻሙ ሊፈውሰው በለመነው ጊዜ ጌታ ኢየሱስ አለምንም ማመነታትና ውጣ ውረድ ወዲያውኑ ፈወሰው፣ ለኢየሱስ አስፈላጊው ነገር ርቀው ወዳሉት ደርሶ ማዳን ቍስለኞችን መፈወስና የእግዚአብሔር ቤተሰብን አንድ ላይ ማድረግ ነበር፣ ይህ ነገር ለአንዳንድ ወገኖች ዕንቅፋት ይሆን ነበር፣ ኢየሱስ ግን የዚህ ዓይነት ዕንቅፋት መሆን አያስፈራውም ነበር፣
የእግዚአብሔርን ርኅራኄና ምሕረት በንጹሕ ልብ ለሚያስፈልገው መቸር ያስፈልጋል፣ ይህን ማድረግ ቀላል አይደለም፣ ሁለት አደጋዎችም ሊያጋጥሙ ይችላሉ፣ ሩቅ ያሉትን ለማቅረብ ሲጣር አማኞችን መክሰር ይቻላል እንዲሁም ካንተ ጋር ያሉትን ላለማጥፋት ስትልም የቀሩትን መርሳት ይቻላል፣ የዚህ ዓይነት ችግር በኢየሱስ ጊዜ ብቻ ሳይሆን አሁንም አለ፣ የሊቃውንቱ ሕግ በሽተኛውን የመተውና የመራቅ ሲሆን የእግዚአብሔር ሕግ ግን በምሕረትና ርኅራኄ መጥፎውን ነገር ፈውሶ መቀበልና ማቀፍ ነው፣ በዚህም ውግዘቱ ደህንነት ማግለሉም የምሥራች ያደርገዋል፣ ቤተ ክርስትያንም የመምህርዋን ፈለግ በመከተል ማንንም ለዘለዓለም ለመኰነን አትሻም፣ የጠፋውን ልጅ መቀበል ማለት መንጋውን ተኵሎች እንዲበትኑት መፍቀድ እንድላሆነ በመረዳት ተጸጽቶ ወደ ቤቱ የሚመለሰውን ልጅ በምሕረት አይቶ መቀበል ያስፈልጋል፣ ለዚህም ነው ጌታ ኢየሱስ በወንጌለ ሉቃስ “ሓኪምን የሚፈልጉ ጤነኞች ሳይሆን የታመሙ ናቸው የሰው ልጅ የመጣውም ጻድቃንን ለመጥራት ሳይሆን ኃጢአተኞችን ለመጥራት ነው የመጣው” (ሉቃ 5፤31) ይላል፣
የቤተ ክርስትያን መንገድ ከእርሷ የራቁትን አለምንም ፍራቻና ቅድመ ሁኔታ መፈለግና ወደ ቤታቸው መመለስ ነው፣ ጌታ ኢየሱስ ለመጻሙን በማንጻት በጤነኞች ላይ ምንም ጉዳት አላደረስም እንዲያው ከፍርኃት ነጻ ያወጣዋል፣ ሕግን ሳይቃወም እግዚአብሔር ሕጉን ለሰራለት የሰው ልጅ ያድናል፣ ፍቅር ያለው ሰው ጥጉን ይዞ ተመልካች ብቻ ሆኖ አይቀርም ኢየሱስ እንዳደረገው የተገለለውን ያቅፋል ይነካል ይህ ነው የፍቅር ቋንቋ፣ የቤተክርስትያን መንገድም ይህ ነው፣ በርዋን ለሚያንኳንኩ ብቻ ቁጭ ብላ መጠበቅ ሳይሆን ከገዛ ራስዋ በመውጣት የተገለሉትንና የቆሰሉትን መፈለግ ያስፈልጋል፣ “ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት አለኝ የሚል ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳደረገው ማድረግ አለበት (1ዮሓ 2፡6)” ይላልና፣
የእግዚአብሔር አገልጋዮች ልዩ የክብር ሥልጣንም ይህ ነው፣ የሚሰቃየውን ወገን መርዳት፣ ጌታ ኢየሱስንና እመቤታችን ድንግል ማርያምን በመከተል ቤተክርስትያንን ስናገለግል ምስክርነታችን ምሳሌና አርአያ በመሆን ሁሉን ሊገነባና ሊያንጽ ይችላል፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ባጠፉ በሚመስሉም ይሁን እኛ አናምንም በሚሉም አለ፣ ለምጽና የተለያዩ በሽታዎች የነበራቸውን ሰዎች ለማቀፍና ለማገልገል ቆርጦ እንደተነሳው እንደ ቅዱስ ፍራንቸስኮስ የተነሳን እንደሆነ የተናቁትና የተረሱት ሰዎች ወንጌል ለመስበክ እንችላለን በዚህም ስብከታችን መተማመኛ ነጥብ ያገኛል ሲሉ ስብከታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.