2015-02-13 19:31:25

የካርዲናሎች ጉባኤና ምክርቤት በቫቲካን ከተማ ውስጥ፤


RealAudioMP3 በቫቲካን ከተማ የሲኖዶስ አዳራሽ ለሁለት ቀናት የተካሄደው የካርዲናላት ምክር ቤት ዛሬ መፈጸሙ ቫቲካን ላይ የወጣ መግለጫ አስታውቀዋል።
ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዚሁ ምክር ቤት ተሳታፊ በሆኑበት ግዜ እናዳመለከቱት የቅድስት መንበር የምህደራ በአዲስ መልክ ማዋቀር ተሐዶሶ ለክርስትና ምስክርነት ሁነኛ መሳርያ እንደሆነ ማስገንዘባቸው መግለጫው አክሎ አመልክተዋል።

ይህ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የተመሰረተ በዘጠኝ ካርዲናሎች የቆመ ምክር ቤት አዲስ ሐዋርያዊ ሕገ ቆኖና ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን እንድያረቅ እንደሚጠበቅ የሚታወስ ነው ።
ይሁን እና የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የካርዲናሎች ምክር ቤት ውሎ በየግዜው ለጋዜጠኞች መግለጫ እና ማብራርያ የሰጡ ሲሆን የቅድስት መንበር ምህደራ መዋቅሮች እደሳ በአጭር ግዜ የሚጠናቀቅ እንዳልሆነ እና ግዜ እንደሚወስድ አስታውቀዋል።
በማያያዝም የተሐድሶ ሰነዱ በሕገ ቀኖና እና በሥነ መለኮት አኳያ በዝርዝር በደንብ መጠናት ስላለበት ረጂም ግዜ መፍጀቱ አይቀሬ ነው ነበር ያሉት ።
በሌለ በኩል ደግሞ ይላሉ የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ የቫቲካን ራድዮ ስራ አስኪያጅ እና የቫቲካን ክፍል ማኀትም ዳይረክተር አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ፡ ህንጸተ ሕገ ቆኖና ከተጠናቀቀ በኃላ የሕገ ቆኖና እና የሥነ መለኮት ጠበብት ተጠርተው ይመለከቱታል።
የቅድስት መንበር ተቋማት ማለት የምእመናን የቤተ ሰብ የፍቅር እና የሕይወት ተቋሞች እንዲመሰረቱ ይታሰባል ብለው ያሉት ቃል አቀባዩ የጳጳሳት ምክር ቤቶች በነሱ የታቀፈ ሊሆን እንደሚችል ገልጠዋል።
በአሁኑ ወቅት ከዓለም ዙርያ የተሰባሰቡ 165 ካርዲናሎች ቫቲካን ውስጥ እንደሚገኙ እና ባለፉት ሁለት ቀናት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ያሳተፈ በየሲኖዶ አዳራሽ መሰብሰባቸው እና የቅድስት መንበር ተቋሞች እደሳ ትኩረት ሰጥተው ንግግር ማድረጋቸው አስገንዝበዋል።
ነገ የካቲት 14 ቀን 20015 እንደ ጎርጎርዮስ አቁጣጠር በቅዱስ ጰጥሮስ ባሲሊክ ጥዋትላይ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ 20 አዲስ ካርዲናሎች እንደሚሰየሙ እና ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እጅ የአሳ አጥማጅ ቀለበት እንደሚቀበሉ የሚታወስ ነው ።
ካርዲናሎች ከሚሰየሙ አንዱ በኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን ኢትዮጵያ የጳጳሳት ጉባኤ ፕረሲዳንት እንዲሁም የምስራቅ አፍሪቃ የጳጳሳት ሕብረት ሊቀ መንበር ብጹዕ አቡነ ብርሃነየሱስ ሱራፊኤል ናቸው።
በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ታሪክ ብጹዕ አቡነ ብርሃነየሱስ ሱራፊኤል ሁለተኛ ካርዲናል ሲሆኑ የመጀመርያ ካርዲናል በ2003 እንደ ጎርጎርዮስ አቁጣጠር ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ብጹዕ ካርዲናል ጳውሎስ ጻድዋ እንደሆኑ የሚታወስ ነው
ካርዲናል መሰየማቸው ትኩረት በመስጠት በራድዮ ቫቲካን የጣልያን ፕሮግራም ላቀረበላቸው ጥያቄ ብጹዕ አባታችን መልስ የሰጡ ሲሆን፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ካርዲናል ሲሰዩሙን፡ በእውነቱ እኔ አላወቅኩም ነበር
ግርምት

ሆኖብኛል ተደነቅሁኝ እኔ ብቻ ሳይሆን በርካታ ሰዎች ተደንቀዋል ነበር ያሉት።
ለአንድ ሀገር ስብከት መስራት ራሱ ዓቢይ ስራ ነው እና አሁን ከሱ የበለጠ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለመስራት ስለ ሆነ እና ሐውርያዊ ስራውን በመልካም አኳኅን እንዲወጣ እግዚአብሔር እንድያግዘኝ፣

ለጸሎት ተቀመጥኩኝ ምእመናንም እንዲጸልዩልኝ ጠይቅያለሁ ብለዋል ነገ ካርዲናል የሚሰየሙ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን ኢትዮጵያ እና የጳጳሳት ጉባኤ ፕረሲዳንት ብጹዕ አቡነ ብርሀነኢየሱስ ሱራፊኤል።
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን አናሳ ብትሆንም ሐለፊነቱ ግን ዓቢ ነው ብለው ያሉት ብጽዕነታቸው እሷ ሀገሪቱ ውስጥ ለሚገኙ የተለያዩ አብያተ ክርስትያናት እና የእስላም ሃይማኖት ድልድይ በመሆን ትቀጥላለች በሕብረተ ሰቡም አዎንታዊ ሚና እየተጫውተች እንደምትገኝ አመልክተዋል፣
ፊታችን ወርሀ ጥቅምት ቫቲካን ውስጥ የቤተሰብ ሲኖዶ እንደሚከናወን እና ለአፍሪቃ ምን ያህል አስፈላጊነት እንዳለው ተጠይቀው ሲመልሱ አፍሪቃውያን ቤተ ሰብ ወዳድ ስለሆኑ ሲኖዶሱ ለአፍሪቃ እጂግ አስፈላጊ እንደሆነ ጠቅሰው የአፍሪቃ ቤተ ስቦች የተለያያ ችግር እንደሚገጥማቸው እና ችግሩ ለመቅረፍ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን አፍሪቃ ከቤተ ሰቦቹ መተባበር እንደሚጠይቃት ብጹዕ አቡን ብርሃነ የሱስ ገልጠዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.