2015-02-11 16:37:31

የሮማዊት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ የመሥተዳድር መዋቅር ኅዳሴ


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የቅርብ ተባባሪዎች ብፁዓን ካርዲናሎችና ብፁዓን ሊቀ ጳጳሳት በአቢይ ሐዋርያዊ ኃላፊነት አገልግሎት ሥር የሚያቅፈው መላይቱ ቤተ ክርስቲያን የሚመራው በኩሪያ ሮማና የሚጠራው የኩላዊት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ መሥተዳድር የበላይ መዋቅር ኅዳሴ ለማረጋገጥ የወጠኑት ዝክረ ነገር ዙሪያ የሚመክረው ዘጠኝ ብፁዓን ካርዲናሎች የሚያቅፍ በማድረግ ያቆሙት ምክር ቤት በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ ቅዱስ አባታችን በተገኙበት ስምንተኛው ጉባኤ እ.ኤ.አ. ከካቲት 9 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ እያካሄደ መሆኑ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ጉዳይ ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አሥተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ አስታወቁ።
ይኽ ዛሬ የተጠናቀቀው የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የበላይ ሐዋርያዊ መሥተዳድር ህዳሴ ጉዳይ የሚከታተለው የብፁዓን ካርዲናሎች ስምንተኛው ጉባኤ ያጠናቀረው የኅዳሴ ሰነድ እ.ኤ.አ. ከየካቲት 11 ቀን እስከ የካቲት 13 ቀን 2015 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን የሲኖዶስ አዳራሽ በሚካሄደው የብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ በማቅረብ መግለጫ እንደሚሰጥበት የገለጡት አባ ሎምባርዲ አክልው የኅዳሴው ጉዳይ የሚከታተለው 9 ካርዲናሎች በአባላት የሚያቅፈው ምክር ቤት ለሚያካሂደው መዋቅራዊ ኅዳሴ ሥራ ምካሄጃ መመሪያና የምክር ቤቱ የእስከ አሁን ድረስ ፍጻሜዎች ዙሪያ በምክር ቤቱ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ማርቸሎ ሰመራሮ አማካኝነት ልዩ መግለጫና ማብራሪያ እንደሚሰጥበት ገልጠው፣ ምክር ቤቱ እ.ኤ.አ. የካቲት 10 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀትር በፊት ባካሄደው ስብሰባ የቫቲካን የመገናኛ ብዙኃን የሚከታተለው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያቆሙት ልዩ ድርገት እስካሁን ድረስ ያከናወናቸው ፍጻሜዎች ዙሪያ በመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ቲገ በሰጡት መግለጫ የተወያየ ሲሆን ከቀትር በኋላ ባካሄደው ውሎው የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ክርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ ይኽ በሳቸው የሚመራው የባህል ጉዳይ ተንከባካቢው ጳጳሳዊ ምክር ቤት በዚህ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን በኩሪያ ሮማና የሚጠራው ሐዋርያዊ የበላ የብፁዓን ካርዲናሎችና ብፁዓን ጳጳሳት መሥተዳድር ኅዳሴ ሂደት የሚኖረው መደላደልና የባህል ጉዳይ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ልዩና ዓይነተኛ አገልግሎት ዙሪያ ትኵረት ሰጥቶ መወያየቱ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.