2015-02-11 16:32:42

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የሚፈልገንን እግዚአብሔር መፈለግ


RealAudioMP3 እግዚአብሔርን ፈልጎ ለማግኘት ከእርሱ ጋር ለመገናኘት ተጋድሎ የሚጠይቅ ሳንከኛ እንዲሁም መጓዝን የሚጠይቅ መሆኑና ተደላድሎና ለግሞ የሚቀመጠው ክርስቲያን የእግዚአብሔር አባታዊ ገጽ ለማግኘት እንደማይችል ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. የካቲት 10 ቀን 2015 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ሁሌ ማለዳ የሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ በመቀጠል፣ የዕለቱ ምንባብ ተንተርሰው ባስደመጡት አስተንትኖ እንዳሰመሩበት የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
አንድ መለያውን ለይቶ ለማወቅ የሚሻ ክርስቲያን በተደላደለ መቀመጫ አረፍ ብሎ የዚህ ዓለም ጠቅላላ የዝርዝር መዝገብ በማገለበጥ ይባስም ከእግዚአብሔር ጋር ምንም አይነት ግኑኝነት የሌላቸው ጽኑ ሕጎች ጭምር በማክበር የእግዚአብሔርን መልክ የሚሻ ከሆነ መለያውን አያውቅም የእግዚአብሔርንም ገጽ ለይቶ ለማወቅ የሚሳነው እንደሚሆን የገለጡት ቅዱስ አባታችን፣ የዕለቱ ከኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 1፣ 20-24 የተወሰደው ምንባብ ተንተርሰው ሰው በእግዚአብሔር አርአያና አምሳያ ተፈጠረ የሚለውን እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠው ጥልቅ መሆናዊ መለያ ሰው መለያውን ለማወቅ ለሚያደርገው ጥረት በር መሆኑ ያብራርቱ ቅዱስ አባታችን ይኸንን የእግዚአብሔር አምሳያና አርአያ በተገቢ ሥፍራው ካልፈለግነው ልናገኘው አንችልም ስለዚህ ይኸንን ጥልቅ መለያ ፈልጎ ለማግኘት መጓዝ ያስፈልጋል፣ ካልሆነ ግን የእግዚአብሔር መልክ ለማወቅ አይቻለንም፣ የተሸበረ የሠጋ ጥልቅ መጓጓት የሚኖር ሰው መሆን ያሰልጋል። እግዚአብሔር ፈልገን እንድናገኘው የሚያነቃቃን የተሸበረና የሚጓጓ መንፈስ በልባችን አሳድሮልናል፣ ይኽ ደግሞ እርሱን ፈልጎ በማግኘት በእርሱ የሚያርፍ ልብ ማለት ነው” እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አያይዞ፦ “መጓዝ ማለት በእግዚአብሔር ወይንም በሕይወት ለመፈተን ገዛ እራስ መፍቀድ ማለት ነው፣ ምክንያቱ መጓዝ ሥጋት ጭምር ነውና። ድካም የእማኔ እጦት፣ ኤሊያስ ኤርሚያስ ኢዮብ የመሳሰሉት ታላላቅ ነቢያቶችን እናስታውስ ዘንድ ይገፋፉናል” ያሉት ቅዱስ አባታችን የዕለቱ ምንባበ ወንጌል ማርቆስ ምዕ. 7፣ 1-17 ያለውን ጠቅሰው ፈሪሳውያንና የሕግ ሊቃውንትና መምህራን ኢየሱስን “ደቀ መዛሙርት ሥርዓት አያከብሩም” በማለት ይወቅሱታል፣ በዚህ ወንጌል ኢየሱስ መጓዝን የሚፈራ ሕዝብ ጋር ለመገናኘት መጓዙን እናስተውላለን፣ ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራት ተደላድለው የተቀመጡ እግዚአብሔርን በሕግ ውስጥ የለዩ ነገር ግን እግዚአብሔር የዘነጉ ናቸው፣ ጉጉታቸው ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት ሳይሆን ከሕግ ጋር ለመገናኘት ነው። የዛሬው ምንባብ እውነተኛው የማንነት መለያችን ያቀርብልናል፣ በምንባባቱ ተጓዝ እግዚአብሔርን ፈልግ የሚልና ሌላው ደግሞ ሕግን ፈጽም ሕግን ፈልግ እግዚአብሔርን ታገኛለህ የሚል ጥሪ ያቀርብልናል፣ እግዝአብሔር መፈለግ እርሱን መሻት ጸጋ እንጂ ሕግ አይደለም፣ ስለዚህ እርሱን ለመፈለግ ብርታት ታንግበን ወደ ፊት ማለት ይጠበቅብናል፣ የእግዚአብሔርን ገጽ እንፈልግ” ያሉት ቅዱስ አባታችን፦ “በጉዞ ለመገኘት የእግዚአብሔር ጸጋ ያስፈልገናል፣ የተቆራረጠ የፈረቃ ተራምዶ ጉዞ ወይንም መራመድ ሊሆን አይችልም፣ ተደላድሎ በተመቸ መቀመጫ የተቀመጠ ሰው መሆን አይገባም፣ የዛሬው ሊጡርጊያ ስለ ሁለት መለያዎች ያወሳናል፣ የእግዚአብሔር አምሳያን አርአያ ነህና ተጓዝ መለያህን ታውቃለህ የሚልና አይ ሕግን በመፈጸም ብቻ አረፍ ብለህ ተቀመጥ የሚል ነው። የእግዚአብሔርን ገጽ መፈለግ መለያችን ነው። በመፈለጉ መለያችንን እናገኛለን” በማለት ያስደመጡት አስተንትኖ እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.