2015-02-09 16:22:56

የወሲብ ዓመጽ ሰለባ ለሆኑት ዓለም አቀፍ የጸሎት ቀን


RealAudioMP3 የሕፃናትና ታዲጊ ወጣቶች ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ የሚከታተለው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. መጋቢት ወር 2014 ዓ.ም. ያቆሙት ጳጳሳዊ ድርገት ምሉእ ጉባኤው በአገረ ቫቲካን ማካሄዱ የሚታወስ ሲሆን፣ ስለ ተካሄደው ጉባኤ በማስመልከትም የድርገቱ ኃላፊ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የቦስቶን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ሲን ፓትሪክ ኦ መለይ በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ተጠሪ በቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ተሸኝተው እ.ኤ.አ. የካቲት 7 ቀን 2015 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መገልጫ መስጠታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፋውስታ ስፐራንዛ አስታወቁ።
ብፁዕ ካርዲናል ኦመለይ ይኽ በሳቸው የሚመራው ድርገት የወሲብ ዓመጽ ሰለባ ስለ ሆኑት ዜጎች ሁሉም በመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በጋራ ጸሎት የሚያሳርግበት ዓለም አቀፍ የጸሎት ቀን ለማዘጋጀተ እቅድ እንዳለ ገልጠው፣ ድርገቱ ባክሄደው ስብሰባ የሕፃናት ሰብአዊ መብትና ክብር ዘርፍ ተገቢ ጥበቃ ለማርጋግጥ የሚያግዝ እቅድ መወጠኑና ለዚህ የሚበጅ ስለ ጉዳይ በተመለከተ መግለጫና መረጃ ለመለዋወጥና ስለ ሕፃናት ሰብአዊ መብትና ክብር ጥብቃ ጉዳይ በተመለከተ የተለያዩ ዓውደ ጥናቶችና ጉባኤዎችም እንዲከናወኑና በሕፃናት ላይ የሚፈጸመው የወሲብ ዓመጽ ጸያፍ ተግባር አደገኛነቱ በማበከር በዚህ ብቻ ሳይታጠር የሕፃናት ዜጎች ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ የሚደረገው ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ጥረት ዙሪያ ሃሳብ ለሃሳብ ለመለዋወጥ ያለው አስፈላጊነት ጉባኤው እንዳሰመረበት ገልጠው፣ በሕፃናት ላይ የሚፈጸመው የወሲብ ዓመጽ ለመግታት የሚደረገው ጥረት ዙሪያ የድርገቱ የሥራ ጉባኤዎች መካሄዳቸውና ይኽ ደግሞ የዚህ ጳጳሳዊ ድርገት ለሚያከናውነው ተጨባጭ የሥራ ሂደት አቢይ ድጋፍ እንዳለውም አስታውሰው፣ ከአፍሪቃ ኤሺያ፣ ላቲን አመሪካና ሰሜን አመሪካ ከአቻይና የተወጣጡ በሕፃናት የሰብአዊ መብት ጥበቃና ክብር ዓላማ አቢይ አገልግሎት የሚሰጡት የዛምቢያ ተወላጅ እናቴ ካልያ እግሊዛዊው የወሲብ ዓመጽ የሆኑትን ሕፃናት የሚደግፍ ማኅበር ያቋቋሙት ፐተር ሳንደርስ የሚገኙባቸው በጠቅላላ 17 አባላት ያቀፈ መሆኑም እንደገለጡ ስፐራንዛ አስታወቁ።
በመጨረሻም ብፁዕ ካርዲናል ኦመለይ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ስለ ድርገቱ በማመልከት ለሁሉም አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት አቢያተ ምክር ለጠቅላላ የመንፈሳዊና ገዳማት የካህናትና ደናግል ማበራት ጠቅላይ አለቆች ባስተላለፉት መልእክት ባንዳንድ የመንፈሳዊ ማህበር አባላት በሕፃናት ላይ የሚፈጸመው የወሲብ ዓመጽ ጨርሶ እንዳይኖር በሚደረገው ጥረት ተግተው እንዲገኙና በዚህ ዘርፍ የማያወላውል ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባቸውም ማሳወቃቸው አስታውሰው የካቲት 2 ቀን ኩላዊት ቤተ ክርስቲያን በምታከብረው በዓለ አስተርእዮ ዘእግዚእነ የወሲብ ዓመጽ ሰለባ ለሆኑት ሕፃናት ዓለም አቀፍ የጸሎት ቀን እንደሚሆን ማሳወቃቸው ስፐራንዛ ገለጡ።







All the contents on this site are copyrighted ©.