2015-02-09 16:10:31

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፦ በቤተ ክርስቲያንና በኅብረተሰብ ለሴቶች ተጨማሪ ቦታ መስጠት


RealAudioMP3 ጳጳሳዊ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ምክር ቤት እ.ኤ.አ. ከየካቲት 4 ቀን እስከ የካቲት 7 ቀን 2015 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የሴቶች ሥነ ባህል፦ የሴቶች ባህል፣ በእኩልነትና በልዩነት (መሆናዊ መለያ)” በሚል ርእስ ሥር የተመራ ይፋዊ ጉባኤ አገረ ቫቲካን በሚገኘው የሲኖዶስ የጉባኤ አዳራሽ ማካሄዱ ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ ጉባኤው ዓለማችን አካባቢያችን ሕይወት ባጠቃላይ ፍጥረትና ወቅታዊ የዓለማችን ሁኔት በሴቶች አይነ እይታ ምን ተመስሎው የዳሰሰ ሲሆን፣ በዚህ አጋጣሚም የሥነ ሴት ባህል ጉዳይ የሚመለከት በዚሁ ጳጳሳዊ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ምክር ቤት ሥር የሚታቀፍ አንድ ቀዋሚ የጥናትና የምርምር ኮሚቴ ለማቆም ሃሳብ እንዳለም በተካሄደው ዓውደ ጥናት መገለጡ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ሲቻል፣ ጉባኤው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በለገሱት ምዕዳን መጠቃሉም ገልጠው፣ ቅዱስነታቸው፦ ለሴቶች ከፍ ያለ ተጨማሪ ቦታ በቤተ ክርስቲያንም ሆነ በኅብረተሰብ ዘንድ መስጠት” ያለው አስፈላጊነት በለገሱት ምዕዳን አሳስበው፣ “ጊዜው ሴቶች እንደ እንግዳ ማየት አብቅቶለት በቤተ ክርስቲያንና በኅብረተሰብ ዘንድ አቢይ ሙሉ ተሳትፎ የሚሰጡበት እድልና ቦታ መስጠት የሚጠይቅ ነው፣ ስለዚህ ይህ ተጋርጦ ይቆይ የማይባልበት ሁሉንም ካህናት መጋብያን ዓለማውያን ምእመናን የፖለቲካው ዓለም የባህልና የኤኮኖሚው ዓለም የሚመለከት እጅግ አንገብጋቢና ዓቢይ ተጋርጦ ነው” ብለው የተካሄደው ዓደ ጉባኤ የተወያየበት ርእሰ ጉዳይ እርሱም፦ “የሴቶች ባህል፣ በእኩልነትና ልዩነት (መሆናዊ መለያ)” በማተኮር ርእዮተ ዓለም ዓይነ ጠባብ በመሆኑ ተጨባጩን ሁነት በሙላት እንዳይታይ የሚያደርግ ነው፣ ስለዚህ ዓውደ ጥናቱ የተወያየበት ርእሰ ጉዳይ በርእዮተ ዓለም ሥር የሚተነተን አይደለም” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አመለከቱ።
“የበላይነት ሳይሆን በእኩልነት ላይ የጸና የጋራ ግኑኝነት ማነቃቃት ያስፈልጋል፦ ምዕርቡ ዓለም ሴቶች የወንዶች የበታች የሚለው ማኅበራዊ አመለካከትና ተግባር ያገለለ ነው፣ ሆኖም ግን ይኽ ዓለማዊ ንድፍ ያስከተለው አሉታዊ ገጽታው አሁንም ጨርሶ አልጠፋም፣ ምክንያቱም እኩልነት የሚለው አነጋገር መለያነት ያጠቃ በመሆኑም ነው፣ ሌላው ተራና ግልጽ እኩልነት የሚለው እርሱም እኩልነት ብዙ ሳይብሰለሰልና አለ ምንም እሳቤ ሊተገበር በመሞከሩም ነው፣ ሌላው ደግሞ እኩልነት በጋራ ግኑኝነትና ተሟይነት ላይ በጸና በሁለቱ ጾታዊ መሆን ያለው ልዩነት የሚያከበር አመለካከት የሚከተል አመለካከት ለትክክለኛ መንገድ እድል የሰጠ ነው።፣ በወንድና በሴት መካከል ያለው ግኑኝነት ባህርያዊ የማንነት መለያቸውን እንደ የመሆናቸው በመኖር፣ አንዱ ለሌላው አስፈላጊ መሆኑ ያበክራሉ፣ ስለዚህ ይኽ ሂደት የሰብአዊ ምሉእነት ያረጋግጣል” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አያይዘው፦ “ትውልድነትና የህይወት እቃቤ የሴቶችን አድማስ ያሰፋል፣ ይኽንን ሴት ልጅ የታደለቸው አድማስ በቤተሰብ በእምነት በሕንጸት በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በትምህርት ቤቶች በማህበራዊ በባህላዊና በኤኮኖሚያዊ መዋቅር በመሳተፍ አቢይ አስተዋጽኦ የሚሰጡት ሴቶች ማበረታታት ያስፈልጋል። ቤተ ክርስቲያንን ሕይወት የሚያስተናግድና የሚወልድ የሴት ባህርይ አማካኝነት መግለጡ እንዴት ደስ ያሰኛል” እንዳሉ ይጠቁማሉ።
“የሴቶች አካል የሚሸጥና የሚለወጥ የገበያ አቅርቦት አይደለም፦ ያሉት ቅዱስ አባታችን በዚህ ነጥብ ላይ ተንተርሰው፦ የሴት ልጅ አካል በባህልና በሥነ ሕይወት ደረጃ ለስቃይና ለዓመጽ መዳረግ አቢይ ወንጀል ነው። ስለዚህ በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ዓመጽ አለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሊወገዝ እንደሚገባው አሳስበው ሴት የሕይወት ትእምርት ሆና እያለች ብዙውን ጊዜ አካልዋ ለአመጽ ይዳረጋል፣ በአንዳንድ ሴቶች ገዛ ፈቃድም የሴት አካል ለተሳሳተ አገላለጥና አኗኗር ምርጫ ተዳርጎ ይታያል፣ የሴት አካል ለአዳዲስ የባርነት ተግባር መገልገያ፣ ሴቶች የመግረዙ ልምድ ወዘተ የመሳሰሉት በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ጸያፍ ተግባር ሁሉ ማጥፋት የሁሉም ኃላፊነት ነው” እንዳሉ ጂሶቲ አስታወቁ።
ሴቶች በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት ማሳተፍ፦ ያለው አንገብጋቢነት በዓለም በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ጸረ ሰብአዊ ተግባር ሁሉ ዘርዝረው፣ በሴቶች ላይ የሚፈጸመ ጸያፍ ተግባር ለመዋጋት በሚደረገው ባህላዊ ትግል ሴቶች በቅድሚያ ተሳታፍያን ማድረግ ወሳኝ መሆኑም ገልጠው፣ ከዚህ ጋር በማያያዝም ሴቶች በቤተ ክርስቲያን ሕይወት ተሳታፊነታቸው ከፍ ማድርግ ማበረታታት ይጠበቅብናል፣ ሴት እናት ነች በሴት የምትመሰልም ነች ብለው በሴት የማትመሰል ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን መሆንዋ ያጠራጥራል፣ በመሆኑም በቤተ ክርስቲያን በቲዮሎጊያ በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በመሪነት ደረጃ ሁሉ የሴቶች ተሳትፎ ማሳየል ያስፈላጋ፣ ተሳትፎ ብቻ ሳይሆን የሚኖራቸው ኃላፊነት ጭምር ከፍ ማለት ይኖርበታል” እንዳሉ የገለጡት ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አክለው፦ “መተኪያ የሌለው የሴት በቤተሰብ ያላት ሚና በምንም ተአመር ችላ ሊባልም ሆነ ሊዘነጋ የማይገባው ከሴትነት ባህርይዋ ጋር የተቆራኘ መለያ ነው” ብለው በቤተ ክርስቲያንም ሆነ በብሔራዊና በዓለም አቀፍ ደረጃም ሴቶች በኃላፊነት ማስቀመጥ ተገቢ ብቻ ሳይሆን አንገብጋቢ መሆኑ ያስታወሱት ቅዱስ አባታችን፣ ሴቶች ለብቻቸው እንዳይተዉ ከቤተሰብ ሕይወት ጋር ያላቸው ኃላፊነት ጋር በማጣጣም በተለያየ መስክና ተቋም የተገባ ተጨማሪ ሥፍራ መስጠት እንደሚያስፈልግ ዳግም አበክረው ያስደመጡት ምዕዳን እንዳጠቃለሉ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.