2015-02-09 16:17:24

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ክርስቲያን በየአካባቢው ሐዋርያዊነት ለመኖር የተጠራ ነው


RealAudioMP3 ማኅበረ ክርስቲያንና እያንዳንዱ አማኝ በዚያ በአሁኑ ሰዓት ግድ የለሽነት ተዘጋግቶና ተለያይቶ ካለ መተዋወቅ መኖር አንዱ ለሌላው ያልታወቀ ሆኖ መኖር እየተስፋፋ ባለበት ክፍለ ከተማ የእግዚአብሔር ፍቅር ለመመስከርና የዚህ ፍቅር ሐዋርያዊ ልኡክ ሆኖ ለመኖር የተጠራ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ የዓለማውያን ምእመናን ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት በጠራው ምሉእ ይፋዊ ጉባኤ የተሳተፉትን ተቀብለው በለገሱት ምዕዳን እንዳሰመሩበት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አመለከቱ።
የምንኖርበት የአካባቢያችን ክትመት የከተሞች መስፋፋት የለውጥ ክስተት ሁሉ በጠቅላላ በዓለም ደርጃም ሳይቀር ብዙ የዓለማችን ሕዝቦች የሚነካ አቢይና ብዙ ዕድል የሚፈጥር ክስተት ቢሆንም ቅሉ ስጋትም ጭምር ነው። ከተማ ባለበት ሥፍራ ጸረ ከተማ የሆነ ክልል አብሮት ይታያል፣ የመጀምሪያው ውበት ቅንጅትነት የተስተካከለ ሂደት የሚታይበትና የሚኖርበት ሲሆን ሁልተኛው ደግሞ ከዚያ የተዋበና የተስተካከለ ከተማ በስተ ጀርባ እንዳውም በከተማይቱ ማእከል ሊባልም ይችላል፣ እንደ ጥላ ማንም የማያያቸው ተነጥለው ተዘንግተውና ተረስተው ምንም አይነት ግኑኝነት የሌላቸው ለብቻቸው የተተዉ ዜጎች የሚኖርበት ጨርሶ ክትመት ያልነካው ሁነት አለ። ይኽ ሁነት ደግሞ ተፈላጊነትና ግኑኝነት የሌለው ሰብአዊ ሁኔታ የሚያመለክት ነው። ማንም የማያያቸው ቀርቦ እንደምን አደርክ ብሎ ሰብአዊ ቅርበት የማይገልጥበት በእርሱ ፍላጎት ሳይሆን የሚያያቸው እንዳላቸው ሆኖ ስለ ሚኖር እየታዩ እንዳልታዩ የሆኑ ዜጎች የሚኖሩበት ነው። የማይታዩ ብቻ ሳይሆን ጸረ ሰው ሆነው ይታያሉ፣ እግዚአብሔር በከተሞቻችን ይኖራል፣ እግዚአብሔር ከተሞችን ለብቻቸው አይተውም፣ መዘንጋትና ጥድፍያ በተሞላባቸው ከተሞቻችን እግዚአብሔር ይኖራል፣ ሆኖም ይኽንን በከተሞቻችን የሚኖረውን እግዚአብሔር ለመምልከት ልባችንና አይናችንን መክፈት ይኖርብናል፣ ለጨለምተኛነትና ለአፍራሽነት እጃችን ሳንሰጥ በከተሞቻችን ከሚኖረውን እግዚአብሔር ጋር እንገናኝ፣ እግዚአብሔር ከልባችን ፈጽሞ ያልጠፋ በመሆኑም በከተሞቻችን አለ፣ ከከተሞቻችንም አልተለየም ገዛ እራሱን ከከተሞቻችን አልሰወረም። እንዲህ በመሆኑም ከተሞቻችን ለሐዋርያዊ ግብረ ኖሎው አገልግሎት ምቹ ሥፍራ ናቸው፣ ስለዚህ በዚህ ዘርፍ ዓለማውያን ምእመናን የሚኖራቸው ሚና አቢይ ነው። ከተሞቻችንን በእግዚአብሔር ዓይን ለማየት የሚያግዝ ሐዋርያዊ ግብረ ኖሎዎ ያስፈልጋል፣ በከተማና በከተማ ውስጥ እያለ ክትመት የሌለው ሆኖ የማይታይ ተገለውና ተነጥለው የሚኖረውን ለማየት በሚችል በእግዚአብሔር ዓይን ለማየት የሚያበቃ ሐዋርያዊ ግብር ኖልዎ ያስፈልጋል” እንዳሉ ደ ካሮሊስ አመለከቱ።
ወንጌላዊው መሠረተ ነገር ማካፈል፦ በሚለው ሃሳብ ሥር ቅዱስ አባታችን የለገሱት ምዕዳን ሲያጠቅላሉ፦ የዓለማውያን ምእመናን ዓመታዊው ምሉእ ጉባኤ ‘ወንጌላዊ ኃሴት’ ዙሪያ እንዲያስተነትን መወሰኑም አመስግነው “የዓለማውያን ምእመናን ተልእኮ ወንጌልን በኃሴት ማበሰር ነው፣ ደስተኛ አስፍሆተ ወንጌል በሚኖሩበት ኅብረተሰብ ሲያበስሩ ወንድሞቻቸውን ወደ እምነት ይማርካሉ፣ በትህትና የቤተ ክርስቲያን ልኡካንና ተወናያን ናቸው፣ ለሚኖሩበት ከተማ የክርስትያናዊ ሕይወት እርሾ ናቸው፣ በመሆኑም ልኡካነ ወንጌል በከተሞች በማነቃቃት በሚደርገው አገልግሎት ከቆሞሶቻቸው በመተባበር ለዜጎች የወንጌል መሠረተ ነገር ማካፈል ይችላሉ” እንዳሉ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.