2015-02-06 15:47:37

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፦ አሰቃቂ ቅትለት በሴቶችና በሕፃናት ላይ


RealAudioMP3 ጀነቭ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብትና አስከባሪው ድርጅት ገዛ እራሱን እስላማዊ አገር ብሎ የሰየመው እስላማዊው አሸባሪው ኃይል በኢራቅ በሴቶችና በሕፃናት ላይ እንዲሁ በውሁዳን የአገሪቱ ዜቶች ላይ የሚፈጽመው ዘግናኝ አሰቃቂው ቅትለት በተመለከተ ባወጣዋ ልዩ ሰንድ ባሰፈረው ዘገባ ሕፃናት ለአጥፍተትህ ጥፋ የሸበራ ተግባር መገልገያ መሣሪያ በማድረግ ይኽ አልበቃ ብሎት የሌሎች ሃይማኖት ተከታዮች ውሁዳን የኅብረተስብ ክፍል ቤተሰቦች በሕይወት እያሉ ቀብሮ ለሞት በመዳረግ በመስቀል ቸንክሮ አንገታቸውን በመቅላት ለሞት በመዳረግ ላቅመ አዳም የደረሱትና ያልደረሱት ውሁዳን የኅብረተሰብ አባላት ሴቶች በመድፈር ብሎም ባሰቃቂ ሁኔታ ለሞት እየዳረገ መሆኑ ያመልክታል።
ሰነዱ ያጠናቀረው ይህ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዩ ኮሚቴ የኢራቅ መንግሥት ይኸንን ጸያፍ ጸረ ሰብአዊ ተግባር ለመግታትና የዜጎቹ ጸጥታና ደህንነት ሰብአዊ መብት ለማስከበር እንዲተጋ አደራ በማለት፣ እስላማዊው ሃገር በሚቆጣጠረው ክልል ያለው የሚፈጽመው ጸረ ሰብአዊ ተግባር በእውነቱ እጅግ የሚያሰደነግጥ ነው ሲሆን፣ ይህ በእንዲህ እንዳለ እስላማዊ አገር ለሞት የዳረገው የአማን አየር አብራሪው ወጣት ሕይወት ለመበቀል የአማን መንግሥት አክራሪው እስላማዊው ኃይል በሚቆታጠረው ክልል በአየር ኃይል የተሸኝ የጥቃት ግብረ መልስ እየሰነዘረ መሆኑ ከኢራቅ የሚሰርጩ ዜናዎች ሲያመልክቱ፣ የአማን መንግሥት ጸረ እስላማዊው ሃገር ጥቃት ለማሳየል ልዩ የምድር ጦር ኃይል አባላት አሸባሪው ሃይል ወደ ሚቅጣጠረው ክልል ለማሰማራት እቅድ እንዳለውም ይጠቁማሉ።







All the contents on this site are copyrighted ©.