2015-02-06 15:34:09

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ቤተ ክርስቲያን ድኻ ነች፣ ወንጌል የሥነ ሃብት ድለባ ቲዮሎጊያ አይደለም


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሁሌ ማለዳ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ የሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ እ.ኤ.አ. ጥር 5 ቀን 2015 ዓ.ም. በመቀጠል፦ ቤተ ክርስቲያን ወንጌልን በድኽነት የምታበሥር መሆን ይገባታል፣ ወንጌልን የሚያበሥር የሚፈጽመው አገልግሎት የመንፈስ ቅዱስ ሥራ እንጂ በገዛ እራስ ሰብአዊ ኃይል የሚከውነው አለ መሆኑ ታምኖና ሊኖረው የሚገባው፣ በድኽነት ጫንቃ ሥር የተጠቁት የተነከሩበት ስቃይ ቀለል ለማድረግ የሚል ብቸኛው ግብ ያለው ነው። ስለዚህ የስቃይ ተካፋይ በመሆን የሌላው ሥቃይ መፈወስ የወንጌል አብሣሪ ተልእኮ መሆኑ የሚያብራራ አስተንትኖ መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።
መፈወስ የወደቀውን ማንሳትና ነጻ ማውጣት ዲያብሎስን መገሰጽ ይኸንን ሁሉ ከፈጸሙ በኋላ ትሁት ድኻው የእግዚአብሔር መንግሥት አገልጋይ ነኝ ማለት ያስፈልጋል፣ አንድ የክርስቶስ አገልጋይ በዚያች በጦርነት አውድማ መሃከል የምትገኝው ፈዋሽ ቤተ ክርስቲያን ዙሪያ የሚገኙት ድኾችና በተለያየ ምክንያት የደሙትን የቆሰሉትን ቁስላቸውን ፈውሶና ጠግኖ ይኸንን ሰብአዊው ክብራቸው ዳግም ማረጋገጥ ይኖርበታል ያሉት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባሰሙት ስብከት ያንን እጅግ የሚወዱት የሚኖሩት ቤተ ክርስቲያን በጦርነት አውድማ የምትገኝ ሕክምና ቤት ተምሳይና እንዲሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጠራቸው 12 ሐዋርያት ወንጌልን ያበሥሩ ዘንድ የታመሙትን ይፈውሱ ዘንድ የዲያብሎስ መንፈስ ይገስጹም ዘንድ ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው የሚለውን ከዕለቱ የማርቆስ ወንጌል ምዕ. 6 ከቁጥር 7 እስከ 13 ያለውን ጠቅሰው፦ የልብ ቁስሎች መፈወስ፦ ለመንገዳችሁ ከበትር በቀር እንጀራም ሆነ ከረጢት ገንዘብም በመቀነታችው እንዳይዙ አዘዛቸው፣ ይኽ ደግሞ የተጠራው ወንጌል የሚያበሥረው ሊክተለው የሚገባው ሕይወት የሚገልጥ ቃል ነው። ወንጌል በድኽነት ማበሰር፣ ወንጌል ለማበሰር ሌላ የተሰጠ አማራጭ መንገድ የለም፣ ምክንያቱም ድህነት በሃብት የመደለብ የንዋታዊ ሃብት ቲዮሎጊያ ማለት አይደለም፣ ስለዚህ የብሥራት ቃል የአርነት ቃል ነው። የተጨቆኑትን ነጻ የሚያወጣ ነው፣ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮም ይኽ ነው። ሌላ ተልእኮ የላትም። ፈዋሽነት ነው ጥሪዋ። በጦርነት አውድማ እንደ ሚገኝው የህክማ መስጫ ድንኳን ነች፣ ዓለም በቆሰሉት በደሙት በታመሙት የተሞላ ነው፣ ቤተ ክርስቲያን የቆሰለውን ልብ ለመፈወስ የተዘጉ በሮችን ለመክፈት ነጻ ለማውጣትና እግዚአብሔር መልካም መሃሪ መሆኑ ለመመስከር። ሁሉን የሚምር መሆኑ ለማረጋገጥ። እግዚአብሔር አባት ነው ለማለት፣ የዋህና ዘወትር የሚጠባበቀን መሆኑ የምትመስከር ነች። አዎ ይኽንን ለማበሰር ነው ቤተ ክርስቲያን የተጠራችው” እንዳሉ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።
ሐዋርያዊ ቀናተኛነት መንግስታዊ ያልሆኑት የሰብአዊ ማኅበራት ሠራተኛ መሆን ማለት አይደለም፣ ቤተ ክርስቲያን የሰብአዊ የግብረ ሠናይ ማኅበር ድርጅት አይደለችም፣ ብዙውን ጊዜ ልኡካነ ወንጌል የታመሙትን በመፈወስ ሰብአዊ አገልግሎት ብቻ ተጠምደው ይታያሉ፣ አዎ ክርስቶስን ወደ ድኾች ወደ ታመሙት ወደ ታወሩት በእስር ወደ ሚገኙት ማድረስ የሚለው ተእልኮ የዘነጉ፣ እውነት ነው ሰብአዊ እርዳታ ማቅረብ ያስፈልጋል፣ በዚህ ዘርፍ የሚደግፉን ድርጅቶች እንዲኖሩ ማድረግና ማቀናጀት ያስፈልጋል፣ እግዚአብሔር የተለያዩ ሥጦታዎች አድሎናልና፣ ነገር ግን ተልእኮአችንና ለድኽነት መጠራታችን የዘነጋን ስንሆን ሐዋርያዊ ቀናተኛነትን እንዘነጋለን፣ ተስፋችንን በሰብአዊ አገልግሎት በሚደግፉ መገልገያ መሣሪያ ላይ እናኖራለን፣ ይኽ መንገድ ደግሞ ቀስ በቀስ ቤተ ክርስቲያንን ወደ አንድ የሰብአዊ ድርጅትና ተቋም ይለውጣታል፣ ደስ የምትል ኃያል አቢይ ሥልጣን ያላት የሰብአዊ ማኅበር ትሆናለች፣ ወንጌላዊነቷን ታጠፋለች፣ ምክንያቱም ያ ኃያሉ ሚፈውሰው የድኽነት መንፈስ ይጎድልባታልና። ይኽ መንፈስ ሲጎድል ቤተ ክርስቲያን ማንነቷን ተእልኮዋን ትስታለች” እንዳሉ የግለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠና ደ ካሮሊስ አያይዘው፦ ሐዋርያት የእግዚአብሔር መንግሥት ሠራተኞች ናቸው። ሐዋርያት በድኽነት ከብሥራተ ወንጌል አገልግሎት ሲመለሱ ኢየሱስ በእርሱ ዙሪያ አረፍ እንዲሉ ያደርጋል እንጂ አቢየት እንዴት ታላላቅ ሰዎች ናችሁ በማለት ለሚቀጥለው አገልግሎት ስትወጡ ተልእኮውን እንዴት ለመፈጸም በሚል ጉዳይ በመወያየት በሚገባ አዘጋጁ የሚል ሳይሆን፣ ያንን ሁሉ አገልግሎት ከፈጸማችሁ በኋላ የማንጠቅም አገልጋዮች ነን፣ የፈጸምነውም ግዳጃችንን ብቻ ነው በሉ ሲል ይመክራቸዋል፣ ሐዋርያዊነት እንዲህ ነው። የአንድ ሐዋርያ ደስታው የእግዚአብሔር መንግሥት አገልጋይ መሆን ነው፣ ኢየሱስ ፣ የብሥራት ቃል አቅቡ አውጁ የጸጋ አመት ንገሩ፣ ህዝብ የእግዚአብሔር አባትነት ዳግም እንዲጎናጸፍ በልቡ ሰላም እንዲያገኝ አድርጉ ነው የሚለን” በማለት ያደመጡት አስተንትኖ እንዳጠቃለሉ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.