2015-02-04 19:01:29

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ!


RealAudioMP3 ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ!
ዛሬ ባለፈው ሳምንት የጀመርነው አባትን የሚመለከት አስተንትኖ ሁለተኛውን ክፍል እንመለከታለን፣ ባለፈው አስተንትኖ በቤተሰብ ሕይወት ውስጥ ስለማይገኙ አባቶች ተናግረናል! ዛሬ ግን ስለ መልካሙ የአባት ክፍል እንማራለን፣ ቅዱስ ዮሴፍ እንኳ ሳይቀር እመቤታችን ድንግል ማርያምን ጸንሳ ባገኛት ጊዜ ሊተዋት አስቦ እንደነበረና የእግዚአብሔር መልአክ የእግዚአብሔር ዕቅድን በገለጠለት እና የኢየሱስ የእንጀራ አባት መሆን እንዳለበት በነገረበት ጊዜ ዮሴፍ ጻድቅ ሰው ስለነበር እመቤታችን ድንግል ማርያምን “ባለቤቱ እንድትሆን ዘንድ ከእርሱ ጋር ወሰዳት” (ማቴ 1፡24) በዚህም የናዝሬቲቱ ቤተሰብ አባት እንደሆነ ተመልክቷል፣
እያንዳንዱ ቤተሰብ አባት ያስፈልገዋል፣ ዛሬ አባት ለቤተሰብ የሚያበረክተውን እንመለከታለን፣ ለዚህ እንዲረዳን ደግሞ በመጽሓፈ ምሳሌ አንድ አባት ለልጆቹ የሚናገራቸውን ቃላት በመጥቀስ ለመጀመር እወዳለሁ፣ “ልጄ ሆይ፥ ልብህ ጠቢብ ቢሆን ልቤ ደግሞ ደስ ይለዋል፤
ከንፈሮችህም በቅን ቢናገሩ ኵላሊቶቼ ደስ ይላቸዋል።” (ምሳ 23፤15-16) ይላል፣ አንድ አባት ለልጁ ለሕይወት የሚያስፈልገውን ዕሴት ያወረሰና ጥበበኛ ልብ የሰጠ እንደሆነ ታላቅ እርካታና ፍቅር ይሰማዋል፣ የዚህ ዓይነት አባት “እንደኔ ጀግና ስለሆንክ ደስ ይለኛል፣ ምክንያቱም እኔን የምላቸውንና የማደርጋቸውን ነገሮች ትደግማለህና” የሚል አይደለም፣ ከዚህ እጅግ የላቀ ነገር ነው የሚነግረው፣ ስንተረጕመው “በጥበብ ስትሠራና ስትራመድ ሳይህ ደስ አለኝ ፤ በልበ ቅኑነት ስትናገር በሰማሁህ ጊዜም ልቤ ባንተ ሊረካ ነው፣ ይህ ማለትም ነጻ ሆነህ በጥበብና በቅንነት እንድትናገርና እንድትፈርድ ሁሉም ያንተ ሥራ እንዲሆን ብቻህን ነጻ ሆነህ እንድትራመድ ወሰንኩ፣ አንተ እንዲህ እንድትሆን ዘንድም የማታውቃቸውን ነገሮች አስተማርኩህ የማታያቸውን ስህተቶች ስትፈጽምም እርማት አደረግኩልህ፣ ገና ወጣት ሳለህና እርግጠኛነት በማይሰማህ ጊዜ በሙላት ልታውቃቸው ያልቻልካቸው ጥልቅ ፍቅር እንዲሰማህ አደረግኩህ፣ ምናልባት ያኔ ልትረዳው ያልቻልከው የእምነትና የጽናት ምስክርነት ሰጠሁህ፤ ያኔ እንድተባበርህና እንድከላከልልህ ትፈልግ ነበር፣ ግን ይህንን ላንተ ከማስተማሬ በፊት ልቦና እንዲኖረኝና መጠን ካለፈና ከሚያጸጽት ነገር ራሴን ለመጠበቅ እንዲሁም ከሰዎች ጋር የሚያግባቡኝና እንዲረዱኝ ትክክለኛ ቃሎችን ለማግኘት እታገል ነበር፣ አሁን አንተ እነኚህኝ ነገሮች ለልጆችህና ለሌሎች ለማስተማር ስትታገል ሳይህ ጥልቅ ስሜት ይፈጥርብኛል፣ አባትህ በመሆኔ ደስ ይለኛል” ይለዋል ለማለት ያህል ነው፣ ጥበበኛና የበሰለ አባት እንዲህ ነው ማለት ያለበት፣
ይህንን ለማውረስ ምን ያህል ከባድ መሆኑን አንድ አባት ያውቃል፤ ማለት ለልጆችህ ምንኛ ያህል ቅርብ መሆን እንዳለብህና ምን ያህል ጣፋጭና ጽኑ መሆን እንዳለብህ ታውቃለህ፣ ነገር ግን ልጆቹ ይህንን ውርሻ አክብረውት እተግባር ላይ ሲያውሉት ማየት ምንኛ ደስ ያሰኛል፣ ከዚህ የበለጠ ካሳ የለም፣ ይህ ደስታ ልፋቱንና ድካሙን የሚከፍል ማንኛውንም አለመግባባት ተሻግሮ የሚያልፍና ማንኛውንም ቍስል የሚፈውስ ነው፣
በቤተሰብ ውስጥ የሚኖር አባት ዋነኛ አስፈላጊነትም ለዚህ ነው፣ ለባለቤቱ ቅርብ በመሆን ደስታውንና ስቃዩን ልፋቱንና ተስፋውን ማካፈል ነው፣ ልጆቹ ሲያድጉም በጨዋታ ይሁን በትህምርት ጥሩ ውጤት ለማምጣት ሲጥሩ እንዲሁም ደስ ሲላቸውና ሲያዝኑ ወይንም በፍርሃትና በጭንቀት ሲወጠሩ ዝም ቢሉ በእድገታቸው የሚጋዙት መንገድ የተሳሳተ ይሁን ትክክለኛ መንገድ አባት ምንግዜም አጠገባቸው በመገኘት በማንኛውም ሁኔታ እጎናቸው በመሆን ለእድገታቸው ሊረዳቸው ያስፈልጋል ይህ ማለትም የሚያደርጉትንም በሙሉ እንደ ፖሊስ መቆጣጠር ማለት አይደለም ምክንያቱም ልጆቻቸውን በጣም መቆጣጠር የሚሞክሩ አባቶች ልጆቻቸውን ያጠፋቸዋል ልጆቹ እንዲያድጉ አይረዳቸውም፣
በመጽሃፈ ወንጌል እየሱስ በሰማይ ስለሚገኘው አባት ሲናገር እሱ በእውነት መልካም ሰው ተብሎ ሊጠራ እንደሚችል ይገልጻል (ማር 10፡11) ሁላችንም በሉቃስ ወንጌል (15፤11-32) የተጻፈውን ሁለት ልጆች ስላሉት ሰውና የጠፋው ልጅ ታሪክና የአባቱን ፍቅርና ይቅር ባይነት ስንመለከት አባቱ የጠፋው ልጁ እስኪመለስ ሁልግዜ ሳይታክት በሩ ላይ ይጠብቀው ነበር አባቱም ሲመለስ ባየው ግዜ ልቡ በጣም በመራራት ልጁን ሮጦ አንገቱን አቅፎ ሳመው ይለናል፣ ስለዚህ አባቶች ምንግዜም ታጋሾች መሆን አለባቸው አብዛኛውን ግዜ በትዕግሥት በጸሎትና በፍቅርና በምህረት መጠበቅ አለብን ሌላ አማራጭ የለንም፣
ጥሩ አባት መጠበቅና ከልቡ ይቅር ማለትን ያውቃል እንዲሁም መቅጣትና ማስተካከልን ይችላል ደካማ ስሜታዊና በቀላሉ ተስፋ የሚቆርጥ አይደለም፣ አንድ አባት ተስፋ ሳይቆርጥ ልጁን የሚቀጣ ምንግዜም ለልጁ የሚንከባከብ አባት ነው አንድ ምሳሌ ልንገራችሁ አንድ ግዜ የትዳር ስብሰባ ላይ አንድ አባት እንዲህ አለ እኔ አንዳንድ ግዜ ልጄን መምታት አለብኝ ግን ፊቱን አልመታውም እልክ እንዳይዘው ደስ አይልም አባትየው ልጁን መቅጣት አለበት የሚቀጣውም በትክክለኛው መንገድ ነው እኔ በዚሁ ቀጥል እላለሁኝ፣
እየሱስ በሰማይ የምትኖር አባትችን ሆይ ብሎ ያስተማረንን ጸሎት የሚገልጽልኝ አለን? እየሱስ እባታችን ሆይ ሲል የአባትነትን ጸሎት በመጀመሪያ ያስተምረናል ያለ በሰማይ የሚኖር አባታችን ጸጋ አባቶች ተስፋቸውን ይቆርጣሉ እርሻቸውንም ይተዋሉ ልጆች ግን አባቶቻቸውን ማግኘት ይፈልጋሉ በተለይም ተስፋቸው ካልተሳካና ከወደቁበት ሲመለሱ የሚጠብቃቸውን አባት ማግኘት ይሻሉ፣ ልጆች የወደቁበትን ወይንም የተሳሳቱትን በፍጹም ማመንና መቀበል እንዲሁም እንዲታወቅባቸውም አይፈልጉም ዳሩግን የቤተሰብ እርዳታን ይፈልጋሉ ያንን ካላገኙ ያጋጠማቸውን የችግርና መከራ ቁስል መዳን አይችልም፣
ቤተክርስቲያን እናታችንም በሙሉ ሃይሏ የቤተሰብ አባቶችን ለመደገፍ ታጥቃ ስትሰማራ ምክንያቱም እነሱ የአዲሱና የመጪው ትውልድ ጠባቂዎችና ሊተኩ የማይችሉ የዕምነት አማላጆች የእግዚብሔርን ሕግ እንደ ቅዱስ ዮሴፍ የሚጠብቁ ናቸው፣








All the contents on this site are copyrighted ©.