2015-02-04 16:45:20

አገረ ቫቲካን፦ የሴቶች ባህል


RealAudioMP3 ጳጳሳዊ የባህል ጉዳይ የሚከታተለው ምክር ቤት እ.ኤ.አ. የካቲት 7 ቀን የሚጠቃለለው ዓለም አቀፍ የሴቶች ሥነ ባህል፦ “የሴቶች ባህል፣ በእኩልነትና ልዩነት (መሆናዊ መለያ)” በሚል ርእስ ሥር የተመራ ይፋዊ ጉባኤ አገረ ቫቲካን በሚገኘው የሲኖዶስ የጉባኤ አዳራሽ እ.ኤ.አ. የካቲት 4 ቀን 2015 ዓ.ም. መጀመሩ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፋቢዮ ኮላግራደ አስታወቁ።
በመካሄድ ላይ ስላለው ይፋዊ አውደ ጥናት አስመልክተው የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ጉባኤ ዓለማችን አካባቢያችን ሕይወት ባጠቃላይ ፍጥረትና ወቅታዊ የዓለማችን ሁኔት በሴቶች አይን እይታ ምን ተመስሎው የሚዳስስ መሆኑ ገልጠው፣ በዚህ አጋጣሚም የሥነ ሴት ባህል ጉዳይ የሚመለከት በዚህ በሳቸው በሚመራው የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሥር ቀዋሚ የጥናትና የምርምር ኮሚቴ ለማቆም ያላቸው ሃሳብ አስታውቀው ለዚህ ዓውደ ጥናት ማካሄጃ የሚሆን የጥናት ሰነድ ቀደም ተብሎ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በተለያየ ወቅት ሰብአዊ ፍጥሩና መሆናዊ መለያው በተመለከተ የሰጡት አስተምህሮ አስተንፍሶ መሠረት በማረግ የረቀቀ መሆኑ ገልጠው፣ ሴት በቤተ ክርስቲያን በማኅበረሰብ በኅብረ ረገድና ባጠቃላይ በተለያየ መስክ የምትኖረው መሆናዊ መለያዋ ላይ የሚያተኩር ዓውደ ጥናት ነው ብለዋል።
ሴት አካል ብቻ አድርጎ ለጾታዊ ስሜት መሥሪያ እያስመሰለ የሚያቀርባት አምባ ገነናዊ የሥነ ውበት መመዘኛ ሴቶች የማስታወቂያ መገልገያ መሣሪያ የሚያደርግ ባህል የሴት ልጅ አካል የሚሸጥና የሚለወጥ ነው የሚል፣ ከዚህ ባሻገር በሴቶች ላይ የሚፈጸመው አመጽና ጸያፍ ተግባር ሁሉ መንስኤው ለይቶ በሕግ ብቻ ሳይሆን በሥነ ባህል ደረጃ ጭምር መዋጋት ያለው አስፈላጊነት በሴቶች እይታ እንዴት መገለጥና እግብር ላይ መዋል እንዳለበት የሚወያይ ዓውደ ጥናት ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.