2015-02-04 16:32:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ውፉያን ኃሴትና የፈጠረ ችሎታ የተካኑ


RealAudioMP3 የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እ.ኤ.አ. የካቲት 2 ቀን 2015 ዓ.ም. በዓለ አስተርእዮ ዘእግዚእነ አቢይ በዓል ማክበሯ የሚዘከር ሲሆን፣ በዚህ ዓቢይ በዓልና ከበዓሉ ጋር ተያይዞ የሚዘከረው የውፉያን ቀን ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኋላ 11 ሰዓት ተኩል በሮማ የሚገኙት የተለያዩ የውፉያን ማኅበራት አባላት የተሳተፉበት መሥዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጃንካርሎ ላ ቨላ አስታወቁ።
በዓለ አስተርእዮ ዘእግዚእነ የዘንድሮው 19ኛው ዓለም አቀፍ የፉያን ቀን እ.ኤ.አ. 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ካወጁት የፉያን ዓመት ጋር የተገናኘ በመሆኑ በዓሉ ከወትሮው ለየት ያለ ጥልቅና ሰፊ ትርጉም እንዲኖረው ማድረጉንም ሲገለጥ፣ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ቅዱስነታቸው ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት፦ ውፉያን “ተአዝዞና ተስፋ፣ በኃሴትና በፈጠራ ችሎታ” መሠረት ሲኖሩ በእውነቱ የሚሰጡት የቃል ብቻ ሳይሆን የሕይወት ምስክርነት ተጨባጭና አሳማኝ እንደሚሆን በማብራራት “ስለዚህ በጌታችን ኢየሱስ ትመሩ ዘንድ ገዛ እራሳችሁን ለእርሱ ስጡ በእርሱ ትመሩ ዘንድም ፍቀዱለት’ እንዳሉ ላ ቨላ ገለጡ።
ቀኑ ማርያም ሕፃን ኢየሱስን ታቅፋ ከሕዝቡ ጋር እንዲገናኝ በመሻት በቤተ መቅደስ እርሱን ያቀረበችበት ዕለት የሚከበርበት መሆኑ ቅዱስ አባታችን ባስደመጡት ስብከት በማስታወስ ከዚህ ጋር በማያያዝም፣ የውፉይ ሕይወት ጥልቅ ትርጉም ከዚህ ዓቢይ በዓል ጋር የተቆራኘ መሆኑና፣ ማርያም ያንን ወደ እኛ የሚጓዘው ጌታችን የሆነው ልጅዋን ወደ ቤተ መቅደስ ስታቀርብ ይኽ አቅርቦት እኛ ወደ ጌታ ለምናደርገው ጉዞ ምክንያት መሆኑ የሚያወሳው ወንጌላዊ ቃል ላይ በማነጣጠር፦ “ኢየሱስ የእኛን ሰብአዊ ጉዞ በመጓዝ የምንጓዝበተ አዲስ ጎዳና ገልጦልናል፣ ይኽ አዲስና ህያው መንገድ ደግሞ ገዛ እራሱ ነው። ኢየሱስ አዲስና ህያው መንገድ ነው። ለውፉያን ይኽ አዲስና ህያው መንገድ; የማያሻማ አማራጭ የሌለው ብቸኛው መንገድ ነው፣ ኢየሱስ ባመለከተው መንገድ በኃሴትና በተስፋ ተሸኝቶ መገጓዝ ይገባል” ያሉት ቅዱስ አባታችን አያይዘውም ይኽ መንገድ በተአዝዞ መንገድ የሚገለጥ መሆኑ ሲያብራሩ፦ ኢየሱስ የገዛ እራሱ ፈቃድ ሳይሆን የላከው የአባቱን ፈቃድ ለመፈጸም ነው የመጣው፣ ስለዚህ ኢየሱስን የሚከተል በተአዝዞ ጎዳና ገዛ እራሱን ያራምዳል፣ የሚራመደውም ገዛ እራሱ ዝቅ በማድረግ እንደ ኢየሱስ የገዛእ እራስ ክብር ትቶ አገልጋይ ለመሆን በመሻት ታዛዥ በትህትና ገዛ እርስ ገዛ ዝቅ በማድረግ የአብ ፈቃድ የገዛ እራስ ፍቃድ በማድረግ ነው፣ የአገልጋዮች አገልጋይ መሆን” ውፉያን በዚህ መንገድም ኢየሱስን ለመምሰል ሲመሩ፦ “እውነተኛውን ተስፋ ይጎናጸፋሉ…ለአንድ ውፉያ ማደግ ከፍ ከፍ ማለት በትህትና ለአገልግሎት ዝቅ ማለት ነው። ባጭሩ የኢየሱስ መንገድ መከተል ማለት ነው፣ የጥሪው ጸጋ አዳይ መንፈስ ቅዱስ ነው፣ ምልክቱም ኃሴት ነው። ኃሴት የውፉይ ሕይወት ምልክት ነው” እንዳሉ ላ ቨላ አስታወቁ።
ቅዱስ አባታችን በበዓለ አስተርእዮ ዘእግዚእነ ማርያም ዮሴፍና ሕፃን ኢየሱስን የተቀበሉት አረጋውያን ስምዖንና ሃና አስታውሰው፦ “ኢየሱስን ይቀበላሉ፣ ለጌታ ፈቃድ በመታዘዝና ሕግን በማክበር ሕፃን ኢየሱስን ይዘው ይጓዛሉ፣ በዚህ ጉዞ የሚመራቸው ኢየሱስን በመምራት በእርሱ ተመርተው በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ያ በኢየሱስ ተአዝዞና ተስፋ ሆኖ የመጣው እግዚአብሔር በመቀበል ተአዝዞ ኃሴትና ተስፋ ይመሰክራሉ” ብለው በተአዝዞ በመጽናት የሚደረግ ጉዞ የግልና የማኅበራዊ ብስለትና ጥበብ ይሞላል፣ ስለዚህ በዚህ ሁነት የሚገኝ ውፉይ ያ ለመንፈስ ቅዱስ ገዛ እራሱ ምቹ በማድረግና በተአዝዞ የተገኘው የማኅበሩ ደንብ ወቅታዊነት በማልበስ ለማቀብና ለመኖር አያዳግተውም። “አንድ ውፉይ ሕይወት ህዳሴና ወጣትነት መንፈስ የሚጎናጸፈው ለማኅበሩ ሕግ ካለው ፍቅርና የማኅበሩ አረጋውያን አባላት ጥበብ በጥልቅ ከማዳመጥ ነው። እንዲህ ካልሆነ በውፉይ ጉዞ የውፉይ ሕይወታችን በቸልተኛነትና አግርሞትና መደነቅ በሌለው መንፈስ፣ ልክ የአእምሮ ብቃትና የእውቀት ውጤት በሚያስመስለው በትህትና ገዛ እራስ ዝቅ በማድረግ አገልጋይ ሳይኰን ግኑኝነት የማይኖረው ጸሎት በመኖር፣ ወድማማችነት አለ ሱታፌ ተአዝዞ አለ እማኔ ወደ ላይ ያላቀና ግብረ ሠናይ እርሱም ፍቅር በሆነው እግዚአብሔር ላይ ያልጸና ፍቅር የሚኖርበት ይሆናል፣ ሌሎችን ወደ ኢየሱስ ለመምራት በኢየሱስ የምንመራ ስንሆን ብቻ ነውና በእርሱ እንምራ ዘንድ ገዛ እራሳችን ለእርሱ እንተው፣ አዎ የተመሩ መሪዎች በኢየሱስ ተመርተው ወደ ኢየሱስ የሚመሩ” በማለት ያስደመጡት ስብከት እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጃንካርሎ ላ ቨላ ገለጡ።







All the contents on this site are copyrighted ©.