2015-02-02 15:58:45

የከፈኑ ሰው


RealAudioMP3 የቶሪኖ ከፈን በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ጥንታዊው በፍታ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተገነዘበት ጨርቅ ተብሎ የሚነገርለት በኢጣሊያ የቶሪኖ ሰበካ የሚገኘው ቅዱስ ከፈን እ.ኤ.አ. ቅዱስ ዮሐንስ ቦስኮ የተወለደበት ዝክረ 200ኛው ዓመት ምክንያት እ.ኤ.አ. ከሚያዝያ 19 ቀን እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ለትርኢት እንደሚቀርብ ከቶሪኖ ሰበካ የተሰራጨው መግለጫ ሲያመለክት፣ ባለፉት ቀናት ስለዚሁ ቅዱስ ከፈን በተመለከተ ኢየሱስ ናዝራዊ እንዲስተነተን ስቃዩ በጎልጎታ በጥልቅ ጽሞና የተኖረው ፍቅር ተጨባጭ መግለጫ በሚል ርእስ ሥር እንዲስተነተን የከፈኑ ተጨባጭ ሁነት ዙሪያ በካስተል ጋንዶልፎ ጳጳሳዊ ሕንጻ ቁምስና ጳጳሳዊ የቅዱስ ቶማስ ዘቪላኖቫ ቤተ ክርስቲያን ባነቃቃው ዓውደ ጉባኤ አስተምህሮ የሰጡት የሥነ ቅዱስ ከፈን ተመራማሪና ሊቅ ፕሮፈሰር ጁዘፐ ባልዳኪኒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ በመጨረሻዎቹ ሁለት ዓመታት በቅዱስ ከፍን ዙሪያ የተደረገው የተራቀቀው ምርምር በከፈኑ ታትሞ የቀረው ምስል ልክ በሥነ ቅመማና የሥነ አካላዊ ምርምር እንደሚያረጋግጠው በአንድ ኃይለኛ መብረቃዊ ብርሃን ክስተት አማካኝነት የተነሣ ሊሆን ይችላል በማለት ይኽ ደግሞ የተካሄዱት የሥነ ምርምር ጥናቶች የሚያረጋግጡው እውነት መሆኑ በትክክል የተብራራበት ሲሆን። ስለዚህ የአንድ ሃይለኛ ብርሃን ብልጭታ ውጤት ነው የሚል አመለካከት በጥልቀት መብራራቱ ዘክረው ሆኖም በብልጭታ የሚታተመው ምስል ከብልጭታው የሚመነጭ አይደለም ስለዚህ ምስል ሊታተም ያ ምስል ያለው ሰው መኖር አለበት። ይኽ ቅዱስ ከፈን ለሥነ ምርምር አቢይ ተጋርጦ ነው። እንደ አማኝ መጠን ቅዱስ ከፈን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተገነዘበት ጨርቅ ነው ብየ አምናለሁ፣ ሆኖም ይኽ ያለኝ እምነት ከሥነ ምርምር ሙያየ ጋር ሳላጋጭ በዓይነ ተመራማሪ ቀርቤ እያጠናሁትም ነው። እስከ አሁን ድረስ የተከናወኑት የምርምር ጥናቶች እምነትን የሚያበረታታ እንጂ እምነት የሚጻረር ወጤት አላስገኙም። በከፈኑ ታትሞ የቀረው ምስል በወንጌል ከሚነገረው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማማት ስቃይና ሞት እውነት ጋር የሚገናኝ ያንን ስቃይና ሞት በትክክል የሚያወሳ ከፈን ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.