2015-02-02 15:56:41

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን፦ ሕግ ጽናት ብቻ ሳይሆን እኩልነትና እዝለ ልቦና የተካነ መሆን አለበት


RealAudioMP3 የቅድስት መንበር የበላይ ፍርድ ቤት እ.ኤ.አ. የ 2015 ዓ.ም. ሰማንያ ስድስተስኛ የሕግና ፍትህ ሥራ መክፈቻ ምክንያት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን በአገረ ቫቲካን አስተዳዳሪ ሕንጻ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ያረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው ባሰሙት ስብከት፦ ሕግ ጽኑ የማያወላውል የማያሻማ መሆን ይጠበቅበታል ሲባል እኩልነት ፍትህና እዝነ ልቦና የተካነው መሆን አለበት ማለት ነው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ አስታወቁ።
የተስተካከለ እዝነ ልቦና የተካነ ሕግ ብፁዕ ካሪዲናል ፓሮሊን ቅዱስ ዮሐንስ ቦስኮ ሕግ እንዳይጣስ መጨቆን ሳይሆን ወንጀል ቀድሞ መጠንቀቅ የሚያግዘው ባህል በማስፋፋት ለማረጋገጥ እንደሚቻል አስታውሰው፣ ይኽ የቅድስት መንበር የበላይ ፍርድ ቤት በዚህ እ.ኤ.አ. በተገባው 2015 ዓ.ም. የተመሠረተበት ዝክረ 200ኛ ዓመት እያከበረ መሆኑም ጠቅሰው፦ ሕግ ሁሉን ወደ መልካምነት የሚመራ መሣሪያ በመሆኑ ሕግ ለብቻው በቂ አይደለም፣ ስለዚህ የሕጋዊነት የፍትህ ባህል ማስፋፋት የሚደገፍ መሣሪያ መሆን አለበት፣ የሁሉም ሰብአዊ መብትና ክብር ማስጠበቂያ ሥርዓትና ለማኅበራዊ ሰላም ዋስትና ሊሆን ይገባዋል። ስለዚህ እዝነ ልቦና ያለው የሌላውን ሥቃይ የገዛ እራስ በሚያደርግ ፍቅር የሚመራ መሆን አለበት፣ ለፍርድ ተላልፎ የሚሰጠው ወንጀለኛ መጥላቻ ሳይሆን እንደ ገዛ እራስ በማፍቅር ለመልካም ተግባርና ጸባይ የሚያነጽ መሆን አለበት” እንዳሉ ፒሮ ገለጡ።
“ፍርድ መበየን ማለት ቂም በቀል መወጣት ማለት አይደለም፣ ስለዚህ ብቀላና ሕዝባዊ ፍርድ ማእከል የሚያደርግ መሆን የለበት። ብቀላና የአደባባይ ማርኪያ መሆን አይገባውም፣ የብቀላ የጭቆና መሣሪያ አይደለም፣ ዶን ቦስኮ ሕግ የሚያፈቅር ያስፈራኛል፣ ምክንይቱም የሚሳሳት ሁሉ ይሰቀል የሚል ነውና። ሕግ የሚያፈቅር የበደለውን ሰው የሚጠላ የሕግ ጽናትና ኃያልነት ወንጀል ያጠፋል ብሎ የሚያምን ነው። ወንጀል የሚያጠፋው ሕግ ሳይሆን ፍቅርና የሌላው ድህነትና ደህንነት ማሰብና የትብብርና የወንድማማችነት ባህል ነው” ብለው፦ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በተለያየ ወቅት ሕግ የብቀላና ያደባባይ ማርኪያ መሆን አይገባውም እንዳሉት፣ ሕግ ሰብአዊነት ማእከል ያደረገ መሆን አለበት” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ አያይዘው፦ “ሕግ ሁሉም ለመልካምነትና ለወንድማማችን የሚያነቃቃ ሁሉም የእያንዳንዱ ተጠያቂ መሆኑ የሚያንጽና የሚያስግሰነዝብ ሁሉም ስለ ሁሉም እያንዳንዱ ስለ ሁሉም፣ ሁሉም ስለ እያንዳንዱ ያስብ ለሚለው የፍቅር ባህል የሚያንጽ መሆን አለበት” በማለት ያስደመጡት ስብከት እንዳጠቃለሉ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.