2015-02-02 16:04:43

በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የውሁድ ስምምነትና ውይይት ሳምንት


RealAudioMP3 ዘንድሮ አምስተኛው ዓለም አቀፍ የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የውሁድ ስምምነትና ውይይት ሳምንት እ.ኤ.አ. እስከ የካቲት 7 ቀን የሚዘልቀው መርሃ ግብር የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም. መጀመሩ ሲገለጥ፣ ይኽ እ.ኤ.አ. በ 2010 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ አማካኝነት የተነቃቃው የሁሉም ሃይማኖቶች የጋራው ግኑንነትና ውሁድ ስምምነት ሳምንት እ.ኤ.አ. በ2010 ዓ.ም. የዮርዳኖሱ ንጉስ አቡዱላህ ሁለተኛ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተገኝተው ባስደመጡት ንግግር “ሁሉም ሃይማኖቶች በሁሉም እንዲሰፍን አልመው የሚያስተምሩት ሰላም በሃይማኖት የእርስ በእርስ መቀባበልና እርስ በእርስ በመካባበር የሚገለጥ መሆን አለበት” በሚል ጥልቅ ሃሳብ አማካኝነት የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራው ግኑኝነት ያለው አስፈላጊነት እንዳሰመሩበት የሚታወውስ ሲሆን፣ በዚህ በአሁኑ ወቅት በዓለማችን የሚታየው ውጥረትና ግጭት የሁሉም ሃይማኖት መቀራረብና መተዋወቅ እጅግ አስፍፈላጊ መሆኑ የሚያስገነዝብ ከመሆኑም ባሻገር ሁሉም ሃይማኖት ማንኛውም ዓይነት ጸረ ሰብአዊ ድርጊት እንዲቃወሙ ብሎም ሁሉም ሃይማኖቶች የሰላምና የውሁድ ስምንነት አብሳሪያን እንዲሆኑ የሚያነቃቃ ሳምንት ሲሆን፣ በዚህ መርሃ ግብር መሠረት በተለያዩ አገሮች የተለያዩ ሃይማኖት የጋራ ውይይትና ግኑኝነት አውደ ጉባኤ ያካተቱ ዝክረ ነገሮች የሚፈጸምበት ሳምንት ሲሆን የተለያዩ ሃይማኖት መንፍሳዊ መሪዎች በተለያዩ ወህኒ ቤቶች ጉብኝት በማካሄድ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚያከናውኑበትና የሁሉም ሃይማኖቶች ሰላማዊ ግኑኝነት ለሰላም መሠረት መሆኑም በተለያየ መልኩ የሚመሰከርበት ሳምንት እንደሚሆን ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.