2015-02-02 15:52:50

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ መሬት እናት ነች


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ጥር 31 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ዝክረ 70ኛ ዓመት ምሥረታው እያከበረ ያለው የኢጣሊያ የቀጥተኛ የእርሻ ምርት አምራች ገበሬዎች ፈደራላዊ ማኅበር አባላት ተቀብለው መሪ ቃል መለገሣቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።
የግብርና ምርት ለከፋ አደጋ የሚያጋልጠው አሰናካይ ተግባር ሁሉ እርሱም በመሬት ላይ የሚሰነዘረው የአካባቢ ተፈጥሮ ጤንነት ግድ የማይለው ሥነ ምኅዳር የሚጎዳው ቅጥ የለሽ ብዝበዛ ማስወገድ ያለው አስፈላጊነት በሃይለ ቃል ያሳሰቡት ቅዱስ አባታችን፣ ምድርን መሸጥና መለወጥ በሚል አስተሳሰብ ሃብት ማደለብ የተሰኘው ማንኛውም የሕይወት ደመ ሥር ለአደጋ የሚያጋልጥ ባህርያዊ የሥነ ሕይወት ተኪዶ የሚያናጋ ሥልት በመከተል የተፈለገው የገንዘብ ሃብት ከተጨበጠ በኋላ ያንን የተበዘበዘው መሬት የተፈጥሮሃብቱና ውበቱ እራቁቶ በመተው፣ ሌላ ድንግል መሬት ለመፈለግ የገበሬዎች መብትና ክብር በመጣስ የሚደረገው ውደራ እያስከተለው ያለው አደጋ ምን ተመስሎው አብራርተው፣ መሬት እናት ነች፣ እናት ስለ ሆነችም እናትነትዋ በሚያከብር ሥልት መጠቀም ያስፈልጋል፣ መሬት ለግብርና ምርት ብቻ ሳትሆን ለሕይወት ጭምር መሠረት ነች እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ አያይዘው፦ “አለ ግብርና ማኅበረሰብ አይኖርም” በማለት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የግብርና ሥራ በክርስቲያናዊ ራእይ በመመልከት እርሱም በክርስቲያናዊ ሥነ ምግበር ላይ አስተንፍሶ አማካኝነት፦ “የሰብአዊነት መልክ ያለው ማኅበራዊ ግብርና፣ እርሱም በጽኑ የግኑኝነት ባህል በመሬትና በሰው መካከል ያለው ከሕይወት ጋር የተቆራኘው ግኑኝነት የሚያነቃቃ ነው። አለ መሬት ሰብአዊነት የለም፣ አለ ምግብ ሕይወት የለም፣ መሬት ለሰው ልጅ ሕይወት የሚያስፈልገው ምርት ታቀርባለች፣ ስለዚህ መሬት ሊከበርና ካለው ክብር ጋር የተሰተካከለ ግኑኝነት ያስፈልገዋል። ይኸንን ክብር የሚያከብር የግብርናና የኤኮኖሚ ፖለቲካ እግብር ላይ ማዋል ወሳኝ ነው” ብለው “መሬት ተጠቅሞ መጣል በሚለው የገንዘብ ሃብት አምላኪው ባህል የተጠቃ በመሆኑ፣ የተበዘበዘው መሬት ለምነቱ በማኮላሸት እንደ ጥራጊ በመጣል ሌላ ለም መሬት ለመፈለግ የሚደረገው ሩጫ ለም መሬት ለገንዘብ ሃብት ማደለቢያ ዓላማ ብቻ እንዲውልና ከገበሬው መሬት በተለያየ አስባብ በመንጠቅ መሬትንና ገበሬውን ለአደጋ የሚያጋልጥ ሥልት በዓለማችን እየተስፋፋ ነው። ገንዘብ እንደ ጣዖት ማምለክ እናት መሬትን ለመሸጥ አደጋ ያጋልጣል” እንዳሉ ደ ካሪሊስ አስታወቁ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እንጀራ ውፉይ ነው ማለትም የተባረከ ነው። መሬት የሁሉም ነው” በሚለው መሠረት ሃሳብ ላይ በማተኮር “የተፈጥሮ ሃብት ለሁሉም ነው። ለሁሉም የተገባ ሆኖ እያለ ነገር ግን ዓለማችን የሚከተለው በዝባዥ የኤኮኖሚ ሥልት ድኽነት እና እርሃብ እያስፋፋ መሬት ለሁሉም የሁሉም የተፈጥሮ ሃብት የሁሉም ለሁሉም የሚለው ራእይ በማናጋት ብዙ ሕዝብ መሬት ከሚሰጠው ሃብት ተገሎ እንዲኖር እያስገደደ ነው። ፍትህ ተጓድሏል፣ ቅድመ አያቶቻችን እንዳስተማሩንም ምግብ የምትሰጠውን ማሬት ማክበር ይገባናል፣ ይኸንን ባህል መልሰን ሕያው ካላደረግን እርሃብና የምግብ እጥረት እንዲቀረፍ የሚደረገው ጥረት ውጤት አይኖረውም። መሬት የሚሸጥና የሚለውጥ ለገንዘብ ሃብት ድለባ መገልገያ ሳይሆን መታቀብ የሚገባው ጸጋ ነው። ሥነ ምኅዳር ለአደጋ የማያጋልጥ ሰብአዊነት ማእከል ያደረገ ሰብአዊነት ሚዛን ያለው የግብርና ሥልት ዳግም መጎናጸፍ ይኖርብናል፣ እግዚአብሔር መሬት ለሁሉ ሰጥተዋል፣ ለሁሉ ሰው ዘር ነው። በክብር እግዝአብሔር የሰጠንን መሬት ስናቅብ ሰው ማእከል ያደረገ ሥልት በማረጋገጥ መሬት ልንገለገልበት እንችላለን” ብለው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.