2015-01-28 16:41:31

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፣


RealAudioMP3 ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ!
ስለቤተሰብ የጀመርነውን ትምህርተ ክርስቶስ እንቀጥላለን፣ ዛሬ እንደመሪ ቃል የምንወስደው “አባት” የሚለውን ቃል ነው፣ ይህች ቃል ለእኛ ክርስትያኖች እጅግ ተወዳጅ ናት ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔርን አባት ብለን እንድንጠራው ስላስተማረን ነው፣ የዚች ቃል ትርጉም ጥልቀት ያገኘውም ጌታ ኢየሱስ እግዚአብሔርን አባቴ ብሎ መጠራት ከጀመረበትና ከእርሱ ጋር ያለውን ልዩ ግኑኝነት ለመግለጥ ከተጠቀመበት ወቅት ጀምሮ ነው፣ የታላቁ ምሥጢረ ቅድስት ሥላሴ የአብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ጥልቅ ግኑኘት የክርስትና እምነታችን አንኳር መሆኑም ጌታ ኢየሱስ ግለጦልናል፣
አባት የሚለው ቃል ሁላችን የምንረዳው ዓለም አቀፍ ቃል ነው፣ መሠረታዊ ግኑኝነት የምትገልጽ ልክ እንደ የሰው ልጅ ታሪክ ጥንታዊት ናት፣ ይሰውረን እንጂ ዛሬ ኅብረተሰባችን አባት የለሽ ማኅበረሰብ ሆነዋል፣ በሌላ አነጋገር በም ዕራባዊው ባህል የአባት ቦታ ባዶ ቀርተዋል! እንደሌለ ሆነዋል፣ በመጀመርያ ይህ ሂደት ሕግ ከሚያስከብና ገዢ ከሆነው አባት እንዲያው ከበስተውጭ ከመጣ ጭቖና ነጻ እንደመውጣት እና ወጣቶች አለምንም ገደብ ለመራመድ የሚረዳ ሆኖ እየታየ ነው፣ ባለፉት ግዝያት በአንዳንድ ቤተሰቦች ወላጆች እንደገዢዎች ልጆቻቸውን እንደባሮች የሚጨቁኑ የልጅነት መብታቸውን የሚጥሱ ሆነው ልጆች ራሳቸውን ለመቻልና ለእድገት እንዳይራመዱ የሚከለክሉ ዓይነት አባቶች ነበሩ፤ ይሁን እንጂ ልጅህን በነጻነት ለማሳደግም ቀላል አልነበረም፤ ስለሆነም ልጆች መጻኢያቸውን እንዲሁም የማኅበረሰባቸውን መጻኢ በነጻነት እንዲገነቡ አይረድዋቸውም ነበር፣
እርግጥ ነው ይህ ጥሩ አካሄድ አይደለም፤ ነገር ግን ዘወትር እንደሚያጋጥመው ካንዱ ሁኔታ ወደ ሌላው ተቃራኒ ሁኔታ መሻገርም አለ፣ የዘመናችን ችግር የጨቋኝ አባቶች መኖር ወይንም አለመኖራቸው አይደለም፣ ዋነኛው ችግሩ የዘመናችን አባቶች በሥራ ተጠምደው የገዛ ራሳቸውን ጉዳዮች ለመፈጸም ሲሯሯጡ ቤተሰብን እስከመርሳት መድረሳቸው ነው፣ በዚህም ትናንሽ እና ወጣት ልጆቻቸውን ብቻቸውን ይተውዋቸዋል፣ ገና የቦነስ አየርስ ጳጳስ በነበርኩበት በአርጀንቲና በዘመናችን ጎልቶ ከሚታየው እጓለማውታነት መጠንቀቅ እንዳለብን አሳስብ ነበርኩኝ፣ አብዛኛውን ጊዜ አባቶችን ባገኘሁበት ወቅት ከልጆቻቸው ጋር የሚጫወቱና ከልጆቻቸው ጋር በፍቅር ጊዜ ለማሳለፍ የቆረጡ እንደሆነ እጠይቃቸው ነበርሁኝ፣ መልሱ እጅግ አሳዛኝ ነበር አብዛኛዎቹ “አባ ይህንን ለማድረግ አልችልም ብዙ ሥራ አለኝ” በማለት ይመልሱልኝ ነበር፣ ስለዚህ ልጁ ሲያድግ አባት የለም፤ ከልጁ ጋር የሚጫወት ከልጁ ጋር ጊዜ የሚያሳልፍ አባት የለም፣
ዛሬ በዚሁ ስለቤተሰብ በምናደርገው አስተንትኖ ለሁላቸውም ማኅበረ ክርስትያኖች ለስጠንቀቅ የምፈልገው፤ “በቤተሰብ ውስጥ በሕጻናቱ እድገትና በወጣቶቹ ጕርምስና አባት የሌለ እንደሆነ ብዙ ይጐድላል እጅግ አስቸጋሪ የሆኑ ቍስሎችም ሊከሰቱ ይችላሉ፣ እንዲያው አብዛኞዎቹ የሕጻናትና የወጣቶች ጕድለቶች ከዚህ የተነሱ ሊሆኑ ይችላሉ፣ የአባት ፍቅርና መሪነት የጐደለው ሕይወት ሁሌ ጐደሎ ነው፣ ይህ ሁኔታ ከአባትየልሽነት የባሰ እጓለማውታነት ነው፣ በእንዲህ ሁኔታ የሚያድጉ ወጣቶች እውነትም እጓለማውታ ናቸው ምክንያቱም አባቶቻቸው በቤት ውስጥ አይገኙም በአካል ብቻ ሳይሆን በአካል ቤት ውስጥ ሳሉም ከልጆቻቸው የማይናገሩና የአባትነት ኃላፊነታቸውን አይወጡምና፣ ከአባታቸው የሚያገኙት አርአያነት ወይንም የሚወርሱት ዕሴት የላቸውም፣ እነኚህ ነገሮች ግን ለአንድ ሕጻን መንፈሳዊና አእምሮአዊ ግንባት ከምግብ በላይ ያስፍልጉታል፣ እነኚህ ከአባት ሊገኙ የሚገባቸው ነገሮች አባታቸው ሰርቶና ለፍቶ እንዲሁም ከቤተሰብ ርቆ ከሚያስገኝላቸው የዕለት እንጀራ እኩል ያስፈልግዋቸዋል፣ አንዳንዴ አባቶች በቤተሰብ ውስጥ የትኛውን ቦታ እንደሚይዙና ልጆቻቸውን እንዴት ማስተማር እንዳለባቸውም ግራ ይገባቸዋል፣ ግራ ከተጋቡ በኋላ ያንፈገፍጋሉ ከኃላፊነታቸውም ይሸሻሉ እና ከልጆቻቸው ጋር እኩል ለእኩል በመሆን ሥነ ሥር ዓት የሚያዝይዝ ይጠፋል፣ እውነት ነው እንደአባት መጠን የልጆች ጓደኛ መሆን ያስፈልጋል ነገር ግን አባት መሆንህን መዘንጋት የለብህም፣ የዚህ ችግር ሁኔታ በማኅበራዊ መዋቅሮቻችንም እንመለከተዋለን፣ እንደእውነቱ ከሆነ ማኅበረሰባዊ መዋቅሮቻችን እያንዳንዱ ግለሰው በተለይ ወጣቶች በሚገባ እንዲኖሩ ለመጠበቅ ኃላፊነት አላቸው ነገር ግን እነኚህም ልክ በወላጅ አባቶች ላይ እንዳልነው ቸል በማለት ሌላ የእጓለማውታነት ሁኔታ ይፈጥራሉ፣ በአንድ ማኅበረሰብ የሚያድጉ ወጣቶች ለመልካም ኑሮ ለመጻኢ ለደስታ ለመዝናናት ሰርቶ ራስን ለመቻል ብዙ ሕልምና ጉጕት ሲኖራቸው በማኅበረሰብ ጐልተው የሚታዩ ችግሮች ሥራ አጥነት ሁሉን ያከሽፈዋል፣ ገንዝብን ማምለክ ይጀምራሉ እውነተኛ ሃብትና ዕሴት ግን ይነፈግላቸዋል አይሰጣቸውም፣
ስለዚህ ለሁላችን ሊያደስትና ለአባቶችና ለልጆች መጽናናት ሊሰጥ የሚችለው ጌታ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ያለውን እናዳምጥ “እናትና አባት እንደሌላቸው ልጆች ብቻችሁንን አልተዋችሁም፤ ተመልሼ ወደ እናንተ እመጣለሁ” (ዮሐ 14፡18) ይላል፣ ስለዚህ መኬድ የሚገባው እውነተኛ መንገድ ጸጥ በማለት መደመጥ ያለበት አስተማሪ ዓለምን መለወጥ የሚችል ተስፋ ጥላቻን የሚያሸንፍ ፍቅር እና ለሁላችን የወንድማማችነትና የሰላም መጻኢ ሊሆነን የሚችል ጌታ ኢየሱስ ብቻ ነው፣ ምናልባት ከእናንተ መካከል “እሺ አባ! ነገር ግን ዛሬ በአባቶች ላይ ጨክነሃል መጥፎ መጥፎውን ተናግረሃል፤ የአባት በቤተሰብ ውስጥ አለመኖርና ለልጆቹ ቅርብ አለመሆንን አስመልክተህ ብቻ ተናግረሃል” ልትሉኝ ትችላላችሁ፣ እውነት ነው ዛሬ ይህንን ነገር ብቻ ለማብራት ፈልግሁ እፊታችን ዕለተ ሮብ በዚሁ ር እስ እንደገና እንነጋገራለን፣ ያኔ የአባትነት መልካምነትን አበራለሁ፣ ስለዚህ በጨለማው በመጀመር ወደ ብርሃን ለመድረስ ስለፈለግሁ ነው፣ ጌታ እነኚህን ነገሮች እንድንረዳ ማስተዋሉን ይስጠን፣ አመሰግናለሁ፣








All the contents on this site are copyrighted ©.