2015-01-26 18:20:28

ጌታ ኢየሱስ ክርስትያኖች አንድ እንዲሆኑ ይፈልጋል፣


RealAudioMP3 ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና እኩለ ቀን ላይ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ከተገኙ ምእመናን እና በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ነጋድያን ጋር የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገዋል፣
ቅድስነታቸው የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት ትናንትና የተጠናቀቀውን ስለ ክርትስያን አንድነት የተካሄደው የአንድ ሳምንት ጸሎት ዘክረው ስለ ክርስትያን አንድነት ጸሎት እንዲቀጥል አሳስበዋል፣
በማያያዝም ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የክርስትያን ሕብረት እንደሚፈልግ ገልጠው በዕለቱ ከቀትር በኋላ በሮም በሚገኘው የቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ ስለ ክርትያን አንድነት ሲካሄድ የሰነበተው ሳምንተ ጸሎት መጠቃለያ ሥርዓተ ቅዳሴ በመሪነታቸው እንደሚከናወን ምእመናኑን አሳስበዋል፣
ቅድስነታቸው ንግግራቸውን በመቀጠል “የክርስትያኖች መከፋፈል ኢየሱስ ክርስቶስን ያሚያሳዝን ተግባር እንደሆነ ታሪካችን እና ሐጢአታችን ነው የለያየን መንፈስ ቅዱስ አንድ እንዲያደርገን በርትተን እንጸልይ” ብለዋል፣
ዲያብሎስ የመለያየት ባለ ቤት ነው ያሉት ቅድስነታቸው ዲያብሎስ በጸሎት እንደሚሸፍም አመልክተዋል፣
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ከመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ፍጽሜ በኃላ በምስራቃዊ ዩክሬይን እየተካሄደ ያለውን ውዝግብ በቅርብ እየተከታተሉት መሆናቸው ጠቁመው ግጭቱ እንዲገታ አጽንኦት ሰጥተው አሳስበዋል። በዚሁ ግጭት ሳቢያ እየተሰቃዩ ስለ ሚገኙ የክልሉ ህዝቦች እንደሚጸልዩም አስገንዝበዋል።
ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ሰላም ነው እና ሰላሙ ይስጠን ሰላሙ ያውርድልን፤ ግጭት የሰው ሕይወት ጥፋት የንብረት ብርሰት ያስከትላል፤ የሰው ልጅ ልዩነቱ ለማስወገድ መወያየት መፈቃቀድ እንደሚያስፈልግም ገልጠዋል፣

ትናትና ዓለም አቀፍ የለምፅ ወይም የስጋ ደዌ በሽተኞች ተስታውሶ የሚውልበት ቀን መሆኑ ዘክረውም በዚሁ ሕመም ለሚሰቃዩ ሰዎች ቅርበታቸውን በማመልከት በጸሎት እንደሚያስብዋቸው አረጋግጠዋል፣

በዕለቱ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ለተገኙ የካቶሊካዊ ተግባር ድርጅት (አዝዮነ ካቶሊካ) አባልት አመስግነው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር እንዲራመዱ አደራ በማለት ሓዋርያዊ ቡራኬ በመልገስና መልካም ምሳ በመመኘት ምእመናኑን ሸኝተዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.