2015-01-26 16:26:49

ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ አለ እውነተኛ መለወጥና ምህረት እውነተኛ ውኅደት አይኖርም


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ጥር 25 ቀን 2014 ዓ.ም. የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ውህደት የጸሎት ሳምንት መዝጊያ ምክንያት የውፉያንና የሐዋርያዊ አገልግሎት ማኅበራት ጉዳይ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ከተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን የተወጣጡ ውፉያን ገዳማውያን ስለ አቢያተ ክርስቲያን ውኅደት ርእስ ዙሪያ ባዘጋጀው አውደ ጉባኤ የተሳተፉትን ተቀብለው ባስደመጡት ምዕዳን፦ ለውህደት የሚደረገው የጋራው ውይይት መንፈሳዊነት የውህደት ተንከባካብያን እንቅስቃሴ መንፈስ መሆኑ በማብራራት፣ መናንያንና ውፉያን ለውህደት ባተኰረው ዓላማ የሚያገለግሉ በዚህ ለውህደት ባቀናው የጋራው ውይይት አቢይ አስተዋጽኦ የሰጡ ካህናት ገዳማውያን መናንያን እንዳለፉና አሁንም አቢይ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ እንዳሉ ገልጠው በዚህ ለውህደት የጸሎት ሳምንት የሚከናወነው የጋራው ግኑኝነት የእያንዳንዱ ውፉይ በጸሎትና በአስተንትኖ በሚከተለው መንፈሳዊ መርሆ መሠረት ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖረው ግኑኝነት ከማኅበሩ አባላት ጭምር ያለው ቤተሰብአዊ ግኑኝነት የጋራው ኑሮና የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ለአንድነትና ለውሁደት ለሚያደርጉት ጉዞ አቢይ ትርጉም ያለው ደግፍም ጭምር ነው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎ ሞናኰ አስታወቁ።
°አለ እውነተኛ የልብ መለወጥና ምህረት አንድነትና ውኅደት ሊኖር አይችልም፣ አንደትና ውኅደት የእኛ የግል ጥረት ውጤት ሳይሆን የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ነው፣ ስለዚህ የሚረጋገጠውም በአንድነት በመጓዝና በወንድማማችነት በፍቅር በአገልግሎት እርስ በእርስ በመቀባበል መንገድ አብሮ በመራመድ ነው። አለ መለወጥ አንድነት የለም፣ የውፉይ ሕይወት እንደሚያስታውሰንም ውፉይ ሕይወት ውኅደት መሻት ማለትና ለአንድነት የሚደረገው ጥረት ሁሉ የልብ መለወጥና እርስ በእርስ ይቅር መባባል የሚጠይቅ መሆኑ ያረጋግጥልናል፣ በግል እይታ ብቻ ሳይሆን በሌላው እይታና አስተያየት ነገሮችን ሁኔታዎች መመልከት የሚጠይቅ ነው። ። እርሱም በአቢያተ ክርስትያን ውስጥ ባለው የተለያየው ባህል በገዳማዊ ሕይወት ውስጥ የሚመለከት በመሆምኑ ለአንድነት ለሚደረገው ጥረት ድርብ ተጋርጦ ነው። ስለዚህ አንድነት የግል ራእይ መለወጥ ይጠይቃል፣ በመሆኑም አንዱ ሌላውን በእግዚአብሔር መመልከትና እራስህ በሌላው ቦታና ሁኔታ ማስቀመጥን ይጠይቃል” እንዳሉ ሎ ሞናኮ ገለጡ።
አለ ጸሎት ውኅደት የለም። ገዳማዊ ሕይወት የመናንያን ሕይወት የጸሎት ትምህርት ቤት ነው። ስለ ወኅደት ታልሞ የሚደረገው ጸሎት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ እንዲሆኑ ሲል ለጸለየው ጸሎት ልኡክ መሆን ማለት ነው። ስለዚህ የውኅደት መሠረት ጸሎት ነው። ገዳማት አለ እዩልኝ ለውኅደት የሚጸልዩ የጸላያን ቤት ነው። የአቢያተ ክርስትያን ለአንድነት ጸሎት ጀማሪ አባ ፓውል ኩቱሬር በገዳማዊ ሕይወትና ለውህደት በሚደረገው ጸሎት መካከል ያለው ግኑኝነት ሲያመለክቱ ሁሉም ለውህደት ስለ ሚጸልዩት የሚጸለይበት በጠቅላላ ስለ አንድነት ስለ ሚደረገው ጸሎት ጸላይ ማለት ነው። እንዲህ በመሆኑም ገዳማት የአቢያተ ክርስትያን የአንድነት ሥፍራ ነው። ውዶቼ እናንተ ገዳማውያን ተቀዳሚ የዚህ የማይታየው የአንድነት የጸሎት ሥፍራ አንቀሳቃሾች ናችሁ፣ ለክርስቲያኖች አንድነት ትጸልዩ ዘንድ አደራ እላለሁ። አለ ቅድስና አለ የተቀደሰ ሕይወት ውኅደት አይኖርም፣ ገዳማዊ ሕይወት ለሁላችን ምስጢረ ጥምቀት ለተቀበልነው ሁላችን ለዚያ ወደ ውኅደት ለሚመራው ጉዞ ብቸኛው መንገድ ለሆነው ለቅድስና ሕይወት መጠራታች የሚያስገነዝበን ነው” በማለት የሰጡት ምዕዳን ማጠቃለላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሎ ሞናኮ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.