2015-01-26 16:16:39

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ይፈታ ብሎ ለመበየን ፈጣን ሂደትና ግብረ ገባዊ እርግጠኛነት ያስፈልጋል


RealAudioMP3 በቃል ኪዳን ክብር ዙሪያ በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ሕገ ቀኖና ሥር ምሥጢረ ተክሊል በተመለከተ የሠፈረው የሕግ አንቀጽ ቅዋሜው ዝክረ 10ኛው ዓመት ምክንያት ጳጳሳዊ ግረጎሪያና መንበረ ጥበብ ወደ አዘጋጀው ዓውደ ጥናት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስተላለፉት መልእክት፦ ግብረ ገባዊ እርግጠኛነትና እንዲሁም ሚሥጢረ ተክሊል ይፈታልኝ የሚለው ጥያቄ በጥልቀት ለመምርመር፣ በአሁኑ ወቅት የሚፈጀው የጊዜ ገደብ እንዲሻሻልና አሠራሩ ፈጣን ሊሆን ይገባዋል በማለት ማሳሰባቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አመለከቱ።
የይፈታልኝ ጥይቄ በጥልቀት ለማጤን የሚደረገው አሠራር የተገባ መፍትሄ የሚያሰጥ መሆን እየተገባው ነገር ግን የቀረበው ጥያቄ ለማጤን ለመመርመር ቃላት በመሰንጠቅ ትርጉሞች በማብዛት ከሚድረገው መንዛዛትና ዓመታት እንዲፈጅ ከማድረጉ ፈተና የተላቀቀ መሆን ይገባዋል። ምክንያቱም የይፈታልኝ ጥያቄ አቅራቢው ሰው ነው። ስለዚህ የሚሰጠው ተገቢ መልስ ማንዛዛት ለስቃይ ምክንያት ይሆናል እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ አያይዘው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባስተላለፉት መልእክት፦ የተሠራው ምሥጢረ ተክሊል ይፈታ በማለት ውሳኔ ለመስጠት ለይፈታልኝ የሚሰጠው መሠረታዊ ምክንያትና ግብረ ገባዊ እርግጠኛነቱ የመለየት ብቃትን ይጠይቃል፣ ይኽ የትዳር ክብር የተሰየመው ሕግ መሠረት የሮማዊት ቤተ ክርስቲያን ፍርድ ቤት ችሎት የተንዛዛ መሆን የለበትን፣ ሕጉ በሚገባ ማወቅ ያስፈልጋል፣ ሕጉን በሚገባ ማወቅ ከተንዛዛው አሥራር ያድናል፣ ሚሥጢረ ተክሊል የሚመለከተው ፍርድ ቤት የሚከታተለው የይፈታልኝ ጥያቄ ችሎት የተክሊሉ ተከላካይ ጠበቃ ሚና ተመልክቶ ይገኛል አገልግሎቱ አቢይ መሆኑ የጸናው ሕግ ያመለክተዋል። እጅግ አሰፈላጊም ነው፣ ይኽ ማለት ደግሞ የበላይ ዳኛ በሚሰጡት ፍርድ ላይ ተጽኦኖ የሚያሳድር ሚና ያለው ሳይሆን፣ ዳኛው በተለያየ ምክንያት የተዛባ ፍርድ ላለ መስጠት የሚደገፍ ለማንም የማያዳላ ትክክለኛ ፍርድ የሚሰጥ እንዲሆን የሚደገፍ ነው” እንዳሉ ገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.