2015-01-26 16:12:46

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ በጸናው መለያና በጋራ መከባበር ከምስልምና ሃይማኖት ጋር ውይይት


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. በ 1926 ዓ.ም. በልኡካነ ወንጌል ላፍሪቃ ማኅበር በቱዚያ አንድ በማለት የተነቃቃውና በሮማ ጳጳሳዊ የሥነ ምስልምና ሃይማኖት ተቋም በሚል መጠሪያ አገልግሎት መስጠት የጀመረበት ዝክረ 50 ዓመት ምክንያት ወደ ተዘጋጀው ዓውደ ጉባኤ፦ “የምስልምና ሃይማኖትና የክርስትና እምነት መካከል መገናኘትና መደማመጥ ማእከል ባደረገ የጋራ ውይይት አማካኝት ለሚታየው ዓመጽ ተገቢ መልስ ለመስጠት ለመተዋወቅና ሌላውን ለመረዳት እንዲሁም የእያናንዳዱ የመለያ ልዩነት ለማክበርና ለመቀባበል የሚያበቃ ሕንጸት እጅግ አስፈላጊ ነው” በሚል ቅዉም ሃሳብ ዙሪያ መልእክት ማስተላለፋቸው የተካሄደው ዓውደ ጉባኤ የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይላኒ አስታወቁ።
“ልዩነቶችን መቀበል ለዓመጽ ማርከሻ ነው” ቅዱስ አባታችን በአሁዱ አምላክ እምነታቸውን ለሚያጸኑ ሃይማኖቶች መንፈሳዊ አባት አብርሃም መሆኑ እውቅና የሚሰጡ ሃይማኖቶች መካከል መለያቸውና የሚለያያቸው የሚያከብር የጋራ ውይይት ለእርስ በእርስ በቀባበል አቢይ ደገፍ መሆኑ በማብራራት፣ ልዩነቶችን ማክበርና መቀበል፣ ሃብትና ፍሪያማነትን ያጎናጽፋል፣ ቅዱስት ቤተ ክርስቲያን ድኅረ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ከምስልምና ሃይማኖት ጋር መወያየት ያለው አስፈልጊነት ዳግም በማስተጋባት፣ ሁለቱ ሃይማንቶች ያለባቸው አቢይ ኃላፊነት ጠቅሰው ውይይት ከምን ጊዜ በበለጠ ዛሬ በሁለቱ ሃይማኖት መካከል ያለው አስፈላጊነት የተረጋገጠ በመሆኑ የሥነ ውይይት ባለ ሙያዎች ሕንጸት እጅግ አስፈላጊ መሆኑና የዚህ ዓይነተ ሕንጸት መስጫ ተቋም ያለው አስገላጊነት የማያወላውል መሆኑ የሚመሰክር እውነት ነው እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ አክለው፦ “የምስልምና ሃይማኖትና የክርስትና እምነት መካከል የሚካሄደው የጋራው ውይይት በትዕግሥትና በትህትና የሚሸኝ እንጂ በአጋጣሚ ሳይታሰብ በማጠጋጋት የሚከወን መሆን የለበትም፣ በጋጣሚ የሚከናወን ግኑኝነት ሲሆን ግፋትና ማፈሪያ ነው የሚሆነው። ስለዚህ በተለያየ ወቅትና ሁነት ካለ መዘጋጀት በአጋጣሚዎች ተገዶ ከመገናኘት ይልቅ ቀጣይ የጋራ ውይይት አስፈላጊ ነው” እንዳሉ አስታውቀዋል።
ለእርስ በእርስ እሴቶች እውቅና መሰጣጠት፦ ምንም’ኳ አለ መግባባትና ችግር የታየ ቢሆንም ቅሉ ባለፉት የመጨረሻዎች አመታት በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የሚካሄደው የጋራው ውይይት እንዲሁም ከምስልምና ሃይማኖት ጋርም አወንታዊ ውጤት ማስጨበጡ የጠቀሱት ቅዱስ አባታችን ወንጌላዊ ኃሴት ሐዋርያዊ ምዕዳን ጠቅሰው፦ መደማመጥ ማሰልጠን ወሳኝ ነው፣ ምክንያቱን መደማመጥ ለእስርስ በእርስ መግባባትና ለሰላማዊ የጋራ ኑሮ ብቻ ሳይሆን በእያንዳንዱ ሃይማኖት ዘንድ የሚኖሩት እሴቶች ጭምር የጋራ እውቅና በመሰጠትና በማክበር በእሴቶች ላይ የጸና ሰላማዊ የጋራ ኑሮ ዘላቂነት እንዲኖረው ያደርጋል። ስለዚህ መለያና የሚለያየውን ለተመሳቀለ ድብልቆሽ ማጋለጥ ማለት ሳይሆን፣ እያንዳንዱ የገዛ እራሱ መለያ ማጽናት ለጋራ መተዋወቅ ቅድመ ሁነት መሆኑ የሚያረጋግጥ ነው። የመለያ ጽናት ከሌለ አልቦ እሴት ለሆነው ለአምባገነናዊና ፈላጭ ቆራጭ ዓለማዊነት መጋለጥ ይሆናል” እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ አመለከቱ።
ጅምላዊ ቅድመ ፍርድ ማስወገድ፦ ቅሱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባስተላለፉት መልእክት “እምነቱ በቃልና በሕይወት የሚኖር እውነተኛ አማኝ እማኔው ዙሪያ የሚሰጠው ምስክርነት እያንዳንዳችን ለምንኖረው ሃይማኖትና እምነት ጥያቄ ነው የሚሆነው” ብለው፦ “በውይይት ግኑኝነት አለ፣ በግኑኝነት መተዋወቅ ይረጋገጣል፣ ሁሉም የሰብአዊ ፍጡር አንድ ቤተሰብ መሆኑ ካለው ቅድመ ግንዛቤ ከተንደረደረ፣ ማንኛውም ዓይነት ጅምላዊ ቅድመ ፍርድና አስመሳይነትን ያገላል፣ ስለዚህ በዚህ ዓይነቱ መንገድም ሌላውን በአንድ አዲስ አወንታዊ ቅድመ ግንዛቤ ለመመልከት ይቻላል” ብለው የእርስ በእርስ መከባበር የሚለው ሃሳብ ጳጳሳዊ የሥነ ምስልምና ጥናት ተቋም ታሪክ እንደሚያመለክተውም የተለየው በዘልማድ መቀበል የሚለው ቅድመ እሳቤ መሠረት በደፈናው የመግለጡ ዓይነት ሂደት አግሎ በተዋጣለት የእያንዳንዱ መሠረት በማወቅ ሥነ ትርጉሙ ባካተተ ሂደት ጭምር ተጢኖ ተገቢ የውይይት ሥነ ትንተና መኖር ያለው አስፈላጊነት ያስገነዝባል፣ ስለዚህ በአግሮሞትና በመደነቅ መንፈስ የተመራ ሥነ ምርምር መሠረት የእርስ መእርስ መተዋወቅ ማረጋገጥ፣ ለእርስ በእርስ መከባበር ብሶል ነው። እንዲህ ባለ መንገድም ግልጽ በሆነው የእርስ በእርስ መለያ ላይ የጸና የጋራ ውይይት ያለው አስፈላጊነት በጥልቀት እንዲስተዋል ያግዛል፣ ስለዚህ ባህልና ሕንጸት ለጋራ ውይይት አጅግ አስፈላጊ ናቸው፣ ለመቀራረብ ሌላውን በጥልቀት ለማወቅ ገዛ እራስ ለማስተዋወቅ ይደግፋል፣ የካቶሊክ ትምህርት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር በሚሰጠው መመሪያ መሠረት በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል በሚደረገው የጋራው ውይይት ቤተ ርስቲያንን የሚወክሉ አካላት በባህልና በሕጽነት የተደገፉ መሆን ይጠበቅባቸዋል። እውነት ለማወቅ በሚደረገው ጉዞ የሰው ልጅ መብትና ክብር በማክበር መቼም ቢሆን እንዳይዘነጋና ይኽ ደግሞ የሚለያየው የገዛ እራስ መለያ በማክበር መደማመጥና መወያየትን ያስከተለ ትእግሥት የተካነው በእያናንዱ ሰው ዘንድ በኑባሬ ፈጣሪ ያኖረው ሃይማኖተኛነት በማክበር የእውነት ጽኑነትና ውበትን ለመለየት የሚያበቃ ግኑኝነት እንዲኖር ይደግፋል” በማለት ያስተላለፉት መልእክት እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.