2015-01-21 09:35:41

ሢሜተ ጵጵስና አዲስ ለቆመው የባህርዳርና ደሴ ኤጳርቅና


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኢትዮጳያ የአዲስ አበባ ሊቀ ጳጳሳት ረዳት በመሆን ሲያገለግሉ ለነበሩት ለብፁዕ አቡነ ሊሳነ ክርቶስ ማተዎስ ሰማሁን ባህርዳንና ደሴን የሚያጠቃልል ላቆሙት አዲስ ኤጳራቅና ጳጳስ እንዲሆኑ መሰየማቸው ከቅድስት መንበር የተሰራጨ ዜና አመለከተ።
በዚህ አዲስ በቆመው ኤጳርቅና የካፑቺን ወንድሞች ማህበር የሲታውያን ገዳማውያን ማኅበር፣ ኮምቦናውያን ልኡካነ ወንጌል፣ ላዛሪስትና የድኾች አገልጋዮች ልኡካን ማኅበር፣ የኢየሱሳውያን ልኡካን፣ የቅድስት ሃና ደናግል ማኅበር፣ የፍቅር ልጆች፣ ቀርመሌሳውያን በነዲክታውያን የቅድስት ንጽሕት ድንግል ማርያም፣ የፍቅር ልኡካን ማኅበር የአፍሪቃ ልኡካን ደናግል ማህበር በሐዋርያዊ አገልግሎት የተሰማሩበት ክልል መሆኑ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፦ 51 የትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎችና የተለያዩ የበጎ ፈቃድ ሐዋርያዊ ልኡካን ጭምር ተሰማርተው አገልግሎት የሚሰጡበት ኤጳርቅና መሆኑ ያመለክታል።
ብፁዕ አቡነ ልሳነ ክርስቶስ ማተዎስ ሰማሁን እ.ኤ.አ. ታህሳስ 19 ቀን 1959 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ጉራጌ ክልል የተወለዱ እ.ኤ.አ. ግንቦት 8 ቀን 1988 ዓ.ም. ማዕርገ ክህንት ተቀብለው እዚህ ሮማ በጳጳሳዊ ቅዱስ ቶማስ ዘአኵይኖ መንበረ ጥበብ በሥነ መንፈሳዊ ቲዮሎጊያ ተመርቀው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው የካቶሊክ ወጣቶች ማኅበር በኢትዮጵያ አበ ነፍስና ቆሞስ የአዲስ አበባ ሰበካ የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ሆነው በማገልገል ላይ እያሉ፣ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. በቅዱስነታቸወ ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በባህርዳር ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ልዩ ሐዋርያዊ ኃላፊነት የአዲስ አበባ ረዳት ሊቀ ጳጳሳት እንዲሆኑ ተሰይመው እንዲሁም ከኢትዮጵያ ውጭ ለሚገኙት የኢትዮጵያ ካቶሊካውን ስደተኞች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ሓላፊ ጭምር ሆነው በማገልገል ላይ እንደሚገኙ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ ብፁዕ አቡነ ልሳነ ክርስቶስ ማተዎስ ሰማሁን እንግሊዝኛ ጣልያንኛ ቋንቋና የኢትዮጵያ የሊጡርጊያ ቋንቋ ግእዝ ትግርኛና አማርኛ ቋንቋዎችንም ጭምር የሚያውቁ መሆናቸው ያመለክታል።









All the contents on this site are copyrighted ©.