2015-01-19 14:37:17

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ኢየሱስ ሕፃን ሁላችን የአንድ እግዚአብሔር ልጆች ናችሁ ይለናል


RealAudioMP3 ሕፃን ተወልዶልናል ወንድ ልጅች ተሰጥቶናል” (ኢሳ. 5.9) ቅዱስ ሕፃን በሚከበርበት ዕለት ከናንተ ጋር ሆኜ በዓሉን ሳከብር እጅግ ልቤ በደስታ ይሞላዋል፣ የቅዱስ ሕፃን ምስል በዚሕች አገር ወንጌል በማስፋፋት የተመለከተ የተመሰከረ ነው…. ይኽ ሕፃን በቀጣይነት በጌታ መንግሥትና የሕፃን መንፍሳዊነት ምስጢር መካከል ያለው ጥልቅ ትሥሥር ያስታውሰናል፣ “… የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀበላት ሁሉ ከቶ መንግሥተ ሰማይ ኣይገባም…(ማር. 10.15) ይኽ ቅዱስ ሕፃን አሁንም በዚያ በጨለማና በድንግርግር ይኖር ወደ ነበረው ዓለም አዲስ የብሥራት ቃል በማምጣት በእግዚአብሔር የብርሃን ጸጋ ቦግ እንዲል አደረገ። ይኽ ደግሞ እኛም በዓለም የእግዚአብሔር መንግሥት ለማስፋፋት መጠራታችህን ያስታውሰናል።
ፊሊፒንስን ለመጎብኘት እዚህ ከተገኘሁነት ዕለት ጀምሮ “የእግዚአብሔር ልጆች ነን” የተሰየመው መዝሙር ስታዜሙ እሰማለሁ፣ ቅዱስ ሕፃንም ይኸንን ነው የሚያስተምረን፣ ይኸንን የውሉድነት ጸጋ ሊያሰጠን ነው የመጣው። እንዲህ በማድረግም የእሁላችን ጥልቅ ማንነት ገልጦልናል፣ ሁላችን የእግዚአብሔር ልጆች የአንድ ቤተሰብ አባላት ነን፣ በዕለቱ በአንደኛው ምንባብ ቅዱስ ጳውሎስ፦ “በክርስቶስ የእግዚአብሄር ልጆች ሆንን…የርክስቶስ ወንድሞችና እህቶች ለመሆን በቃን” ይለናንል። ይኽ ደግሞ ማንነታችን ይገልጥልናል፣ ማን መሆናችንን ይገልጥልናል፣ መለያችን እርሱ ነው “… ዓለም ሳይፈጠር በፊቱ በቅዱሳን ነውር የሌለን በፍቅሩ እንሆን ዘንድ በርክርስቶስ መረጠን” (ኤፈ. 1,3) ይኽ መልእክት በዚህች በፊሊፒንስ አገር የሚያስተጋባ ነው። በእስያ የካቶሊክ እምነት የተቀበለች የመጀመሪያ አገር በመሆንዋም ነው። ይኽ ልዩ የእግዚአብሔር ጸጋና ሃላፊነት ጥሪም ነው። የፊሊፒንስ ዜጎች በእስያ ልኡካነ ወንጌል ይሆኑ ዘንድ ተጠርተዋል።
እግዚአብሔር የመረጠንና የባረከንም በዓይኖቹ ፊት ቅዱሳንና እንከን የሌላቸው ሆነን እንገኝ ዘንድ ነው (ኤፈ. 1.4) እያንዳንዳችንን የመረጠንም በዚህ ዓለም የእርሱ እውነትና ፍትሓዊነትን እንመሰክር ዘንድ ነው። ዓለምን እንደ አንድ የተዋበ የአታክልት ሥፍራ አድርጎ በመፍጠርን እንንከባከበውም ዘንድ በአደራ ሰጠን። ሆኖም ግን ሰው በኃጢአቱ የተፈጥሮ ውበትን በከለ በኃጢአትም ድኽነት መሃይማነትና ምግባረ ብልሽት ቀጣይ እንዲሆን የሚያደርግ ማኅበራዊ ቅርጽ በማኖር የሰብአዊ ቤተሰብን አንድነትንና ውበትን አናጋ አወደመ።
ችግሮችን የሚታዩት ኢፍትሐዊነት የመሳሰሉት ተጋርጦዎች ስናይ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርገን ለመተው ይቃጣናል፣ ይኽ ሁሉ ውጣ ውረድ ወንጌል የገባው ቃል ለማረጋገጥ የማይቻል ያስመስለዋል፣ እንዲህ ከሆነ ደግሞ ወንጌል የማይጨበጥ ሃሳብ ነው ማለት ነው። የእግዚአብሔር እቅድ አሰናካዩ ጠላት የሐሰት መንፈስ መሆኑ ቅዱስ መጽሐፍ ይገልጥልናል፣ ዲያቢሎስ የሐሰት አባት ነው። ዲያብሎስ ብዙውን ጊዜ በላቀው ጊዚያዊነት በተመሰለው በተራቀቀ መሠረት በሌላቸው እፍታ በሆኑት የደስታና አርኪ ተምሳይ ሁኔታዎች አማካኝነት በስውር ይገለጣል፣ እኛም ከንቱ በሆኑ እፍታ የሆኑትን ምርጫዎች በመከተል እርሱም የመጠጥ ሱሰኝነት፣ በተለያዩ ሃብት አባካኝ መዝናኛ ተብለው በሚገለጡት ምርጫዎች በመሳሰሉት ተግባር ሁሉ የተሰጠን ጸጋ እናባክናለን፣ ጸጋው በገዛ እራሳችን ውስጥ እንዲቆለፍ እናደርጋለን፣ ዘወትር የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችን በመዘንጋት ሕፃን ሆነን ለመኖር እንሻለን፣ አዎ ዘወትር ሕፃን ነገር ግን የእግዚአብሔር ልጅ መሆን የሚኖር ሕፃንነት መኖር ማለት ነው። ጌታችን እንደሚያስተምረውን ሕፃናት የዓለም ሳይሆን የገዛ እራሳችው ጥበብ አላቸው… ቅዱስ ሕፃን እውነተኛው መለያችንና ማንነታችን ይገልጥልናል። የእግዚአብሔር ቤተሰቦች መሆናችን ይመሰክርልናል።
ይኽ መለያችን እንንከባከብና እንከላከል ዘንድ ቅዱስ ሕፃን ያሳስበናል….ሕፃነ ክርስቶስ የዚህች ታላቅ አገር ጠባቂ ቅዱስ ነው፣ ወደ ዓለም በመጣ ጊዜ በአንድ ምድራዊ ንጉሥ ሕልውናው ለአደጋ ተጋልጦ ነበር፣ እንደ ሰው ኖረ፣ በቅዱስ ዮሴፍ ከለላ ሥር ኖረ፣ በዚህ ምድር ቤተሰብ ነበረው፣ የናዝሬቱ ቅድስት ቤተሰብ፣ ይኽ ደግሞ ሰብአዊ ቤተሰባችን የእግዚአብሔር ቤተሰብ ቤተክርስቲያናዊ ቤተሰብአዊነታችንን እንንከባከብ ዘንድ ያሳስበናል፣ ዓለምን የሰብአዊ ቤተሰብ መኖርያ በመሆኑም እንንከባከበውም ዘንድም ያሳሰበናል….።
የኢየሱስ ወንጌል ሕፃናትን የሚቀበል የሚያስተናግድ ነው። በእቅፉ ያኖራቸዋል ይባርካቸዋልም፣ እዎ እኛም እንደ እርሱ ሕፃናትንና ወጣቶችን ለዚያ መንፈሳዊና ባህላዊ ሃብቱና ቅርሱ የተገባ ማኅበርሰብ እንዲገነባ እንንከባከበውም ዘንድ ኃላፊነት አለብን…በተጨባጭ አነጋገር ይኽ ማለት ደግሞ እያንዳንዱ የሚወለደው ሕፃን ጸጋ መሆኑ አውቀን መቀበል ማፍቀርና መንከባከብ አለብን ማለት ነው። ወጣቶችን መንከባከብ መጻኢ ተሰርቆባቸው የጎዳና ተዳዳሪ ይሆኑ ዘንድ አንፍቀድ። መጻኢነታቸውን እንንከባከብ።
በቀላሉ ሊጎዳ የሚችል ሕፃን ያ የምህረት የፍትህ የሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ ዓለም አመጣ። ከኃጢአት የሚወረሱ ሁሉ ቅጥፈትን ቅንነት አልቦነትን ምግባረ ብልሽት ተቋቋመ። በመስቀል ኃይል ድል ነሣ። አሁን በዚህ የፊሊፒንስ ሐዋርያዊ ጉብኝቴን በማጠናቅቅበት ወቅት እናንተን በመካከላችሁ ለሚመጣው ሕፃነ ኢየሱስ አወክፋችኋለሁ፣ የዚህ ለተፈቀረው የአገረ ፊሊፒንስ ሕዝብ ከቤተሰብና ከማኅበረሰብ በመጀመር የፍትህ የቅንነት የሰላም መሣሪያ ለመሆን ጥሪው ለአንድነት እንዲነቃ እርስ በእርሱ በመተሳሰብ በመንከባከብ እንዲኖር ያድርግ። ቅዱስ ሕፃን ለፊሊፒንስን ቡራኬው ቀጣይ ነው። የዚህች አገር ክርስቲያን በእስያን በዓለም የወንጌል ኃሴት መስካሪ ልኡክ የመሆን ጥሪው ይንከባከባል ያበረታታልም።
አደራ ስለ እኔ ዘወትር ጸልዩ፣ እግዚአብሔር ይባርካችሁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.