2015-01-19 14:31:41

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ለወጣቶች፦ ማንባትንና ማፍቀርን ተማሩ


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በፊሊፒንስ ርእሰ ከተማ ማኒላ በሚገኘው ቅዱስ ቶማስ ዘአኵይኖ መንበረ ጥበብ በሚገኘው የስፖርት ሜዳ ከሳላሳ ሺሕ በላይ በሚገመቱ ወጣቶች አቀባበል ተደርጎላቸው የአንዳንድ ወጣቶች የምስክርነት ቃል ከማዳመጣቸው ቀደም በማድረግ በታክሎባን መሥዋዕተ ቅዳሴ ከማሳረጋቸው በፊት በክልሉ የነበረው የሕንፃ መቆሚያ ተድርሞሶ በደረሰው አደጋ ሳቢያ በቅዳሴው ለመሳተፍ ከተገኙት ውስጥ የሞት አደጋ ስለ ደረሰባት የ 27 ዓመት ዕድሜ ወጣት ክርይስተል እንዲጸልዩ አደራ እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎ ሞናኮ ገለጡ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ከወጣቶች ለቀረበላቸው ቃለ ምስክርነትና ያሳለፉት አሳዛንኛ አደገኛ ሕይወት ካዳመጡ በኋላ በተለይ ደግሞ አንዲት ታዳጊ ወጣት የጎዳና ተዳዳሪ ለመሆን ተገዳ ያሳለፈቸው አሳዛኝ ሕይወት አስደምጣ እንዳበቃች፦ “ለምን ይኽ ሁሉ ስቓይና መከራ ለሕፃናት ያጋጥማል፣ ሕፃናት ለምን ለስቃይ ይዳረጋሉ፣ ለምንስ ይሰቃያሉ?” በማለት ያቀረበቸው ጥያቄ እጅግ ልባቸው የተነካው ቅዱስ አባታችን ታዳጊ ወጣትዋን አቅፈው በመሳም ሲያነቡ መታየታቸውና ያቀረበችው ጥያቄና ያስደመጠቸው የሕይወቷ ታሪክ ምክንያትም ሊያስደምጡት በወረቀት ጽፈው ያዘጋጁት መልእክት ወደ ጎን በማድረግ ወጣቶችን በመመልከት ወጣቶቹ ካስደመጡት የሕይወት ተመክሮ በመንደርደር አለ ምንም ቅድመ ዝጅግት ወዲያውኑ ከልባቸው የመነጨ ምዕዳን ሲለግሱ፦ ሴት ልጅ ወንድ ልጅ ሊረዳው ሊያገናዝበው የማይቻልው ጥያቄ የማቅረብ ብቃት አላት፣ ሴት ልጅ ነገሮችንና ሁነትን የማስተዋልና የማገንዛብ ብቃት አላት፣ ውዶቼ ተጨባጩ ሁኔት ከእሳቤ በላይ ነው። ማልቀስን ማንባትን ተማሩ፣ ልብ ገዛ እራሱን ለመጠየቅና ለማንባት ዝግጁ ሲሆን፣ በሩቅ የሚገለጠው ዓለማዊ ሓዘኔታ እርባና የለውም፣ ስለዚህ ማንባትን እንማር፣ ዓለማዊ ሐዘኔታ ከማሳየት ይልቅ በሚታየው ሐዘን እጅግ ተነክቶ የስቃዩና የሐዘኑ እውነተኛ ተካፋይ የመሆን ተግባር ለማሳየት ማንባትን መማር፣ በእውነቱ ይኽ የማንባት መንፈስ ዓለማችን የጎደለው ነው የሚመስለው። የተናቁት የተነጠሉት ያነባሉ፣ በተደላደለ ሕይወት የሚኖር ማንባትን አያወቁም፣ አንዳንድ የሕይወት ተጨባጭ ሁነት የምንረዳው በእንባ በታጠበ አይኖች አማካኝነት ስንመለከት ነው” ብለው እስቲ ሁላችን ገዛ እራሳችንን ማንባትን ተምሪያለሁ ወይ፣ የተራበ በእርሃብ የሚሰቃይ ሕፃን ሳይ አነባለሁ ወይ፣ አንድ የአደንዛ|ዥ እጸዋት ተጠቃሚ ሱሰኛ ሕፃን ሳይ ሁኔታው ነክቶኝ አነባለሁ ወይ፣ አለ መጠለያና ቤት የሚኖር ለገዛ እራሱ የተተወ ለተለያየ አመጽ ሰለባ የሆነ በሕብረተብ የሚበዘበዝ ሕፃን ሳይ አነባለሁ ወይ የተሰኙት ጥያቄዎች ያቀረቡት ቅዱስ አባታችን፦ “ኢየሱስ በተለያየ የሕይወቱ ታሪክ አጋጣሚ ማንባቱና በተለይ ደግሞ ከልቡ እንዳነባ እናነባለን። እንዴት እንደሚነባ የሌላው ስቃይና መከራ ተካፋይ ለመሆን ካልተማራችሁ መልካም ክርስቲያኖች ለመሆን አትችሉም” እንዳሉ ሎ ሞናኮ ገለጡ።
“በእግዚአብሔር ለመደንቅ ገዛ እራሳችንን እንፍቀድ፣ በአሁኑ ወቅት የመገናኛ ብዙሃንና የድረ ገጽ የሥነ ልቦና ጉዳይ ሁሉን ነገር እንደምናውቅ የሚያስመስል መንፈስ ያኖርብናል፣ በድረ ገጽ ሁሉ ነገር ይቀርባል ሆኖም ግን የሚያስደንቅ አይሆንም እግዚአብሔር ግን በአግርሞት ይገለጣል። የእርሱ መገለጥ ያስደንቃል፣ በእርሱ ለመደነቅ አደራ ገዛ እራሳችሁ ተዉ ቅዱስ ፍራንቸስኮስ ዘአሲዚ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ በኪሱ አንድ ሳንቲ አልነበረውም ልቡ ግን ሙሉ ነበር” ብለው እዚያ ሥልጣናዊ ምዕዳናቸውን ለማዳመጥ ለተሰበሰቡት ወጣቶች አያይዘው፦ መለመንን ተማሩ፣ ለምትሰጡዋቸው ተመልሳችሁ መለመን እወቁ። በርግጥ ይህ ሃሳብ ለመረዳቱ ያዳግት ይሆናል፣ በትህትና ድጋፍ ከሚያቀርቡልን በትህትና መቀበልን እንማር፣ እንወቅ፣ በድኾች ለመሰበክ ዝግጅዎች ሁኑ፣ ድኾች የላቁ የአስፍሆተ ወንጌል ልኡካን ናቸው፣ አገራችሁ ለማነጽና ለመደገፍም ግብረ ገብ የተካነ ጽኑና ሙሉ ሕይወት ይኑራችሁ፣ የተፈጥሮ አካባቢ ተንከባከቡ፣ ድኾችን ተንከባከቡ፣ እንዲህ ባለ መንገድም ኃሴት የተምላችሁ የእግዚአብሔር ፍቅር መስካሪያን ትሆናላችሁ” እንዳሉ ሎ ሞናኰ ገለጡ”።
“በግብረ ገብ የተካነ ሙሉእ ሕይወት አቢይ ተጋርጦ ያጋጥመዋል። በመሆኑም ከጥልቅ እምነት የመነጨ ጽኑ ነቢያዊነት የተካነ ምስክርነት ለማቅርብ ብርቱዎች ሆኑ፣ ይኸንን ተጋርጦ አታግሉ፣ ከዚህ ተጋርጦ አትሽሹ፣ ለወጣቱ የተደቀነበተ አቢይ ተጋርጦም ማፍቅር ነው። ለማፍቅር አትፍሩ፣ በማፍቀር ግብረ ገብ በተካነው ሕይወታችሁ ጽኑ፣ እዎ ተፈጥሮን ተንከባከቡ፣ ተፈጥሮን በመንከባከብ፣ የፈጣሪ ፍጥረት ሁሉ ለመንከባከብ መጠራታችሁ ትመሰክራላችሁ፣ ኃላፊነት ለበስ ዜጎች ትሆናላችሁ፣ በዚህ ተግባርም የክርስቶስ ተከታዮች መሆናችሁ ታረጋግጣላችሁ፣ የተፈጥሮ አስተዳዳሪዎች እንደ መሆናችሁ መጠን የምንኖርባት መሬት ለመላ ሰብአዊ ቤተሰብ የተዋበ የአታክልት ሥፍራ እንዲሆን ታደርጋላችሁ። ድኾችን መንከባከብ፣ ድኾችን በመንከባከብ አቢይ አስተዋጽዖ እንሰጣለን፣ መንፈሳዊ ቁሳዊ ሥነ ልቦናዊ ድኽነት የተጠቃ አይጠፋም፣ እናንተ በተለይ ደግሞ እነዚያ በድኽነት ለተጠቃው ሁሉ ብዙ ነገር ማድረግ የሚችሉት አደራ እባካችሁ ደጋፍያን ሁኑ፣ ብዙ ነገር ማድረግ የምትችሉ ብዙ ነገር አድርጉ። ብቃታችሁ ጊዚያችሁ ሃብታችሁ በድኽነት ለተጠቁት ለተነጠሉት አካፍሉ፣ እንዲህ በማድረግ በእውነቱ የላቀ ምስክርነት ታቀርባላችሁ” እንዳሉ ልኡክ ጋዜጠኛ ሎ ሞናኰ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.