2015-01-19 18:00:17

ሰባተኛ ሐዋርያዊ ዑደት ር.ሊ.ጳ. ፍራንሲስ ተጠቃልለዋል ፡
ቅድስነታቸው በማኒላ በሪዛል ፓርክ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅድሴ
7 ሚልዮን ህዝብ ተሳታፊ ሁነዋል ።



ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በኤስያ ክፍለ ዓለም በስሪላንካ እና ፍሊፒን ያካሄዱት ሐዋርያዊ ዑደቶች ዛሬ ተጠቃልለዋል ፡ አሁን ዝግጅታችን በሚሰራጨበት ግዜ ከፍሊፒን ርእሰ ከተማ ማኒላ ሮም ለኦናርዶ ዳ ቪንቺ ሀገራት አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ገብተዋል።ትናንት እሁድ ረፋድ ላይ ካረፉበት ከቤተ ሊቀ ጳጳሳት ማኒላ ከተማይቱ ውስጥ ወደ ሚገኘው ጥንታዊ ዩኒቨርሲቲ ቅዱስ ቶማስ ተጉዘው ከየሃያማኖት አባቶች ጋር ተገኛኝተዋል።የማኒላ ቅዱስ ቶምስ ዩኒቨርሲቲ ከአራት ዓመታት በፊት የተቆረቆረ 45 ሺ ተማሪዎች የሚያስተናግድ ዩኒቨርሲቲ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እና ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቅዱስ ቶምስ ዩኒቨርሲቲ እንደ ደረሱ የዩኒቨርስቲው የበላይ ሐላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል ።በዚሁ የቅዱስ ቶማስ ዩኒቨርሲቲ የቡድሃ ይሁዲ ወንጌላዋያን የኦርቶዶክድ ተዋህዶ እና የእስላስም ሃይማኖኖቶች አባቶች ተገኝተው ነበር ።ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ከየሃይማኖት አባቶች ከትገናኙ በኃላ በየዩኒቨርሲቲ ካምፓስ ቅጥር ግቢ ከተሰበሰቡ ወደ ሳላሳ ሺ ከሚጠጉ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ተገናኝተዋል።ከተማሪዎቹ እሁዳዊ መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከደገሙ በኃላ ተማሪዎቹ ለቅድስነታቸው የእንኳን ደህና መጡ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ፡ እሳቸውም ለወጣቶቹ ንግግር አድርገዋል፡ የተወደዳችሁ ወጣት ጓደኞች ዛሬ እዚህ ከናንተ ጋር ሲገኛኝ ደስታ ይሰማኛል።ዚህ ፍሊፒን ላይ ሐውሳርያዊ ጉብኝት በማካሄድበት ግዜ ከናንተ ጋር በመገናኘት ላዳምጣችሁ እና ከናንተ ጋር ለመነጋገር ፈለኩኝ ቤተ ክርስትያን ለናንተ ያላትን ፍቅር እና ተስፋ ለመግለጥ እሻለሁኛ ያሉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሕብረተ ሰቡ ለማሳደስ የበኩላችሁ አስተዋጽኦ እንድታደርጉ እጠይቃለሁኝ ብለዋል። የፍሊፒን ወጣቶች ከቤተ ክርስትያን አገልጋዮች ተባብረው እንዲሰሩ የYአየቁት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ክርስትያናዊ ሕይወት እንዲኖሩ ፈሪሀ እግዚአብሔር እንዲኖራቸው ከድሃ ሕብረተ ሰቦች ከአረጋውያን እና ችግር ላይ ከሚገኙ እንዲተባበሩ አሳስበዋል።የሞራል ሙሉእንት አርአያ እንዲሆኑ ጠይቀው የሚያጋጥማችሁ እንቅፋት እና ወቀሳ ሁሉ በመሻገር የክርስትያናዊ ሕይወት አረአያዎች እንዲሆኑ ጠይቀው ወጦች የመጻኢ ትውልድ ተስፋ ም አሆናቸው አመልክተዋል።የሀገሪቱ ጳጳሳት ቀደም ሲል የአየር ንበረት ትኩረት የሰጠ ሐዋርያዊ መልዕክት ማስተላለፋቸው አስታውሰው ህዝብ የሕወቱ ዘይቤ እንዲያስተካክል አከባብን የመንከባከብ ባህል እንድያዳብር መጥራታቸው ጠቅሰው የፍሊፒን ወጣቶች ተፈጥሮአዊ ሀብት እንዲጠብቁ አሳስበዋል ።ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ለወጣቶቹ ያደረጉት ንግግር በመቀጠል ከሃያ ዓመታት በፊት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እዚህ በንገኝበት ቦታ ተገኝተው ዓለማችን ቅኑ እና ሐላፊነት የሚሸከሙ ወጣቶች ያስፈግዋታል ያሉትን አስታውሰው ይህንን እንድገና ላስታውሳችሁ ብለዋል።በየማኒላ ቅዱስ ቶማስ ዩኒቨርሲቲ ከወጣቶች ጋር ያደረጉት ግንኙነት እንዳበቃም ወደ ቤተ ሊቃነ ጳጳሳት ተመልሰው ከብጹዓን ካርዲናላት ጳጳሳት እና ካህናት ለምሳ የትቀመጡ ሲሆን ከኣጭር ዕረፍት በኃላ Quirino Grandstand Rizal park ወደ ተባለ ሰፊ ሜዳ ተጉዘው ሥርዓተ ቅዳሴ መርተዋል። በዚሁ ሥርዓተ ቅዳሴ የሀገሪቱ መንግስት ባለ ስልጣናት ጨምሮ ሰባት ሚልዮን ህዝብ ተሳሳታፊ ሁነዋል።ቅድስነታቸው በዚሁ ሥርዓተ ቅዳሴ ባሳሙት ስብከት ፡ ከሥርዓተ ቅዳሴ ፍጻሚ በኃላ ወደ ቤተ ሊቀ ጳጳሳት ተመልሰዋል ፡ በዚህም ሰባተኛ ሀገራት አቀፍ ሐዋርያዊ ዑደታቸው ተጠቃልለዋል።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያሪክ ብጹዕ ወቅዱስ ማትያስ የግብጽ ኦትሮዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ ተወድሮስ ዳግማዊ ባደረጉላቸው ጥሪ መሰረት ግብጽን ለአንድ ሰሞን መጐብኘታቸው ተመልክተዋል። ኢትዮጵያዊ ፓትርያሪክ ብጹዕ ወቅዱስ ማትያስ በግብጽ ቆይታቸው ከየሀገሪቱ ፕረሲዳንት ዓብደል ፋታሕ አል ሲሲ እንዲሁም ከአልዛሀር ዓቢይ ኢማም አሕመድ አል ጣይብ ጋር መገናኘታቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት ዘግበዋል።በዚሁ የዜና አገልግሎት ዘገባ መሰረት ብጹዕ ወቅዱስ ማትያስ ከየግብጽ ኦርቶዶስክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን የበላይ ሐላፊዎች እና ከፕረሲዳንት አል ሲሲ ጋር በተገናኙበት ግዜ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ እና በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ትኩረት የሰጠ ውይይት አካሄደዋል።ኢትዮጵያ እና ግብጽ በየሕዳሴ ግድቡ ላይ ያላቸውን የተለያየ አመለካከት በሰላማዊ ውይይት ዘላቂ መፍትሔ እንድያገኝሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርታሪክ ብጹዕ ወቅዱስ ማትያስ ማሳሰባቸው የዜና አገልግሎቱ ገልጠዋል።በኢትዮጵያ እና ግብጽ አብያተ ክርስትያናት መካከል ተከስቶ ስለ ነበረው አለመጣጣም የሁለቱ ሀገራት ፓትርያርካት መወያያ ርእስ መኖሩም ፊደስ የዜና አገልግሎት አመልክተዋል።በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ በአባ ዱላ ገመዳ የተመራ የኢትዮጵያየ የህዝብ ዲፖሎማሲ በግብጽ ይፋ ጉብኝት ማድረጉ እና ከተለያዩ አካላት ጋር በመገናኘት የኢትዮጵያ ህዝብ በአባይ ወንዝ እና በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ ያለውን አቋም ለግብጽ ህዝብ ገለጣ ማድረጉ ይታወሳል።








All the contents on this site are copyrighted ©.